settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ከሞት በኃላ ምን ይሆናል?

መልስ፤


በክርስቲያን እምነት መሐከል ከሞት በኃላ የሚሆነውን ጉዳይ በተመለከተ በመጠን ጎላ ያለ መደናገር አለ፡፡ ጥቂቶች ከሞት በኃላ እያንዳንዱ ሰው እስከ መጨረሻው ፍርድ ድረስ ያም እያንዳንዱ ሰው ወደ መንግሥተ-ሰማይ ወይም ገሃነም እስከሚላክ ድረስ ይተኛል የሚለውን ይዘዋል፡፡ ሌሎች በሞት ጊዜ ሰዎች ወዲያው ተፈርዶባቸው ወደ ዘላለማዊ መዳረሻዎቻቸው እንደሚላኩ ያምናሉ፡፡ ሌሎች አሁንም ድረስ ሰዎች በሚሞቱበት ጊዜ ነፍሳቸው/መንፈሳቸው የመጨረሻውን ትንሳኤ ፤የመጨረሻውን ፍርድ፤ እና ከዚያም የዘላለማዊ መዳረሻቸው ለመጠበቅ ወደ “ጊዜያዊ” መንግሥተ-ሰማይ ወይም ገሃነም ይላካሉ ይላሉ፡፡ ስለዚህ በትክክል መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ነገር ከሞት በኃላ ይከሰታል? መጀመሪያ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነ አማኝ ከሞት በኃላ የአማኞች ነፍስ/መንፈስ ወደ መንግሥተ-ሰማያት እንደሚወሰዱ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ምክንያቱም ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ በመቀበላቸው ኃጥአቶቻቸው ይቅር ተብለዋል፡፡(የዮሐንስ ወንጌል 3፤16፣18፤36) ለአማኞች ሞት “ከሥጋ ተለይተው ከጌታ ጋር መኖር ነው” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፤6-8፤ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፤23)፡፡ ሆኖም ግን እንደ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፤50-54 እና 1ኛ ተሰሎንቄ 4፤13-17 የመሳሰሉት ምንባቦች አማኞች በትንሳኤ እንደሚነሱ እና የከበረ አካል እንደሚሰጣቸው ይገልጻሉ፡፡ አማኞች ከሞት በኃላ ወዲያውኑ ከክርስቶስ ጋር ለመሆን የሚሄዱ ከሆነ የዚህ ትንሳኤ ዓላማ ምንድነው? የአማኞች ነፍስ/መንፈስ ከሞት በኃላ ወዲያውኑ ከክርስቶስ ጋር ለመሆን በመሄድ ላይ ሳሉ ሥጋዊው አካል “እንደተኛ” በመቃብር የሚቀር ይመስላል፡፡ በአማኞች ትንሳኤ ሥጋዊው አካል በትንሳኤ ተነስቷል፤ከብሯል፤ እናም ከነፍስ/መንፈስ ጋር እንደገና ተዋህዷል፡፡ ይህ እንደገና የተዋኸደው እና የከበረው አካል-ነፍስ-መንፈስ በአዲሱ ሰማይ እና አዲሱ ምድር ለዘለዓለም የአማኞች ይዞታ ይሆናል (የዮሐንስ ራዕይ 21-22)፡፡

ሁለተኛ፤ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ላልተቀበሉት ሞት ማለት ዘላለማዊ ቅጣት ነው፡፡ ሆኖም ግን ከአማኞች መዳረሻ በተመሳሳይ ያላመኑትም የመጨረሻውን ትንሳኤ፤ፍርድ እና ዘላለማዊ መዳረሻቸውን ለመጠበቅ ወዲያውኑ ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ሥፍራ የሚላኩ ይመስላል፡፡ የሉቃስ ወንጌል 16፤22-23 ከሞት በኃላ ወዲያውኑ የሚሰቃይን ባለ ጠጋ የሆነን ሰው ይገልጻል፡፡ የዮሐንስ ራዕይ 20፤11-15 ሳያምኑ የሞቱት በሙሉ በትንሳኤ እንደሚነሱ፤በታላቁ ነጭ ዙፋን ፊትም እንደሚፈረድባቸው እና ከዚያም ወደ እሳት ባህር እንደሚጣሉ ይገልጻል፡፡ ከዚያ ያላመኑት ከሞት በኃላ ወዲያውኑ ወደ ገሃነም (የእሳት ባህር) አይላኩም፤ ነገር ግን ይልቅ በጊዜያዊ የፍርድ እና ወቀሳ ዓለም ውስጥ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ምንም እንኳን የማያምኑት ወዲያውኑ ወደ እሳት ባህር ባይላኩም ሳይዘገይ ከሞት በኃላ ያለው ዕጣ ፈንታቸው አስደሳች የሆነው አይደለም፡፡ ባለ ጠጋው ሰው “በዚህ ነበልባል ውስጥ እሠቃያለሁና” ሲል ጮኸ (የሉቃስ ወንጌል 16፤24)፡፡

ስለዚህ አንድ ሰው ከሞት በኃላ “በጊዜያዊ” መንግሥተ-ሰማይ ወይም በገሃነም ውስጥ ይኖራል፡፡ ከዚህ ጊዜያዊ ዓለም በኃላ በመጨረሻው ትንሳኤ የግለሰብ ዘላለማዊ መዳረሻ አይለወጥም፡፡ የሚለወጠው ነገር የዚያ የዘላለማዊው ትክክለኛ “ሥፍራ” ነው፡፡ በመጨረሻው አማኞች ወደ አዲሱ ሰማይ እና አዲሱ ምድር መግቢያ ይሰጣቸዋል (የዮሐንስ ራዕይ 21፤1)፡፡ የማያምኑትም በመጨረሻው ወደ እሳት ባህር ይላካሉ (የዮሐንስ ራዕይ 20፤11-15)፡፡ እነዚህ በጠቅላላው ለድነት ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ አምነውት እንደሆን ወይም ባለማመናቸው ላይ መሠረት አድርጎ የመጨረሻው የሰዎች ዘላለማዊ መዳረሻዎች ናቸው(የማቴዎስ ወንጌል 25፤46፤የዮሐንስ ወንጌል 3፤36)፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ከሞት በኃላ ምን ይሆናል?
© Copyright Got Questions Ministries