ጥያቄ፤
የምድር እድሜ ምንድን ነው? የምድር ዕድሜ ስንት ነው?
መልስ፤
በአንዳንድ ርዕሰ ጉዳዮች መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ስለሚኖረን የሞራል ስነምግባሮች፤ ደህንነትን ስለምናገኝበት መንገድ፡፡ በሌሎች ጉዳዮች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በቂ መረጃን ላይሰጥ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ስናነብ በጣም አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ጉዳዩን ይዳስሳል፡፡ በሌላ አባል ‹‹ ዋና ዋና ጉዳዩች ግልጽ ናቸው›› በመጽሐፍ ቅዱስ ተለይቶ ካልተቀመጡ ጉዳዮች አንዱ የምድር ዕድሜ ዘመን ነው፡፡ የምድርን ዘመን ለመገመት የሚሞከርበት የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ እያንዳንዱ መንገድ የሚጠቀምባቸው ምናልባት ትክክል ሊሆኑ ወይንም ላይሆኑ የሚችሉ አስተሳሰቦች አሏቸው፡፡ ሁሉም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወይንም ሳይንሳዊ በሆነ ቀጥተኛ ተርጓሜ ዙሪያ አጠንጥነው ከሁለቱ በአንዱ መካከል ይወድቃሉ፡፡
አንዱ የምድርን እድሜ ዘመንን ለመገመት የሚታሰብበት መንገድ በዘፍጥረት 1 የምናገኛው ስድስት ቀናት በትክክል አንድ በአንድ 24 ሰዓት ነው የሚያመለክተው እንዲሁም በዘመን ቅደመ ተከተልም ሆነ በሰው ዘር ግንድ ጥናት ምንም ክፍተት አልነበርም ብሎ ማሰብ ነው፡፡
በዘፍጥረት የምናገኘው የሰው ዘር ግንድ አመታት ዝርዝር ከፍጥረት ስራ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ተወሰኑ ብሉይ ኪዳን የተጠቀሱ ክስተቶች ግምታዊ ጊዜን ለማስቀመጥ የሚረዱ ናቸው፡፡ ይህንን መንገድ በመጠቀም የምድር ዘመን ዕድሜ 6000 ዓመት ይሆናል፡፡ ይህን ማስታወስ ያስፈልጋል፤ በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የተቀመጠ የመድር ዘመን ዕድሜ ቁጥር የለም፤ ይህ በቁጥር ስሌት ቀመር የተገኘ ነው፡፡
Radiometric:- Radiometer that is extremely sensitive. Carbon:- በእንቁና በእርሳስ ማዕድን ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ /A chemical analysis used to determine the age of organic materials based on their content of the radioisotope carbon-14; believed to be reliable up to 40,000 years/ ሌላኛው የምድርን ዘመን ለማወቅ ያለው መንገድ በማዕድናት ውስጥ የሚገኘውን የካርበን ይዘት መሰረት በሚደረግ ጥናት (radiometric (carbon) dating)፤ የሰው ዘር ኡደት እና እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የተለያዩ መንገዶችን በማነጻጸር እና ይስማሙ እንደሆነ በማየት ተመራማሪዎች የምድርን እድሜ ለመገመት ይሞክራሉ፡፡ ይህ የምድርን ዕድሜ 4 እስከ 5 በሊዩን የሚያደርሰው ነው፡፡ የምድርን ዘመን ለመለካት ምንም አይነት ቀጥተኛ መንገድ እንደሌለ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡
ሁለቱም መንገዶች የምድርን ዘመን ለመናገር ወደ ኋላ የመጎተት አቅም አላቸው፡፡ የፍጥረት ቀናት የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተለመደው 24 ሰዓት እንደሆነ የማያምኑ የስነመኮት አዋቂዎች አሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የዘፍጥረት የሰው ዘር ግንድ ብንመልከት የሚጠቅሰው የተወሰኑ ሰዎች የዘር ግንድ ብቻ በመሆኑ በግልጽ የሚታወቅ ክፍተት አለበት፡፡ ተጨባጭ በሆነ መለኪያ የምድር ዘመን ዕድሜ 6000 ዓመት ያልበለጠው ወጣት ነው ብሎ የሚስማማ አይመስልም እናም እንደዚህ ያለውን መረጃ አለመቀመበልም እግዚአብሔር አሁን የምንመለከተውን አለም ምድርን ሲሰራ ልክ እንደ አረጀ አድረጎ እንደ ሰራው ማሰብን በተወሰነ መልኩ ይጠይቃል፡፡ ምንም እንኳ በተጻራሪ መልኩ ማለት እንደሚቻለው ምድር ያረጀ ረጅም ዕድሜ አላት የሚል አመለካከት ባላቸው ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ስህተት የሌለበት እስትንፋሰ እግዚአብሔር ያለበት እንደሆነ ይቀበላሉ ግን በተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ትክክለኛ ተርጓሜ ይለያሉ፡፡
በሌላ መልኩ የካርበን ይዘት መሰረት የሚደረግ ጥናት (ራዲዮሜትሪክ) ጠቃሚና ትክክል ሊሆን የሚችለው እስከተወሰነ ድረስ ብቻ ነው የምድርን ዘመን በሚመለከት ከተቀመጠው የመለኪያ መስፈርት ያነሰ ነው፡፡ የምድር ጥናት የጊዜ የመለኪያ መስፈርት የቅሪተ አካል መረጃዎች እና የመሳሰሉት በአብዛኛው በገምታዊ አስተሳሰብ እና የታወቁ ስህተቶች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ በትልቁ ስነፍጥረት ወስጥ ያለው ላይ ያለን ምልከታም ተመሳሳይ ነው፤ ማየት የምንችለው ካለው አለም ላይ ጥቂቱን ክፋይ ነው በአብዛኛው የምናውቀው በቃል እውቀት ብቻ ነው፡፡ በአጭሩ በአለም ላይ ያለው የምድር ዕድሜ ዘመን ግምት ትክክል እንዳልሆነም ለማመን ከበቂ በላይ የሆኑ ምክንያቶች አሉ፡፡ ሳይንሳዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ በሳይንስ ላይ መደገፍ ምንም አይደለም ነገር ግን ሳይንስን ምንም ስህተት የማይገኝበት አድርጎ መቀበልም አይቻልም፡፡
በመጨረሻ የምድር ዕድሜ ዘመን ቅድመ ተከተል ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ ባልተጠበቀ መልኩ በሳይንስም ሆነ በስነመለኮት በጉዳዩ ላይ በሁለቱም በኩል አንድ ሊሆን የሚችል ብቸኛ የሆነ ትርጓሜ አለ የሚሉ ድምጾች አሉ፡፡ ስለእውነቱ በክርስትና እና ረጅም የምድር ዕድሜ ባላት ምድር አመለካከት መካከል ሊታረቅ የማይችል ስነመለኮታዊ ግጭት የለም እንደ ወጣትነት ዕድሜ በሚቆጠር አጭር እድሜ ባላት ምድር እና በእውነተኛ ሳይንስ መካከልም እንዲሁ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ አይሆንም በለው የሚሉ የማያስፈልግ ክፍፍል ይፈጥራሉ፡፡ የትኛውንም አመለካከት አንድ ሰው ቢይዝ ዋናው ነገር ቢቀበለውም ባይቀበለውም የእግዚአብሔር ቃል እውነተኛና ስልጣን ያለው ነው፡፡
የምድርን ዕድሜ ዘመን ቅርብ ወጣት በሚያደርገው (young earth perspective) አመለካከት ለሚቀበሉ አግልግሎት ክፍሎች ጥያቄዎች አሉ፡፡ ዘፍ 1-2 ያለውን ቃል በቃል ቀጥተኛ ትርጉም እንዳለው ነው የምናምነው፤ የምድር ዕድሜ ዘመን ቅርብ ወጣት በሚያደርገው (young earth perspective) አመለካከትም በንባብ የሚያቀርበው እንደዚሁ ነው፡፡ በተመሳሳይ ደግሞ ምድር ረጅም ዕድሜ አላት የሚለው አመለካከትም የስህተት ትምህርት ነው አንልም፡፡ የምድርን ዕድሜ ዘመን በሚመለከት ከእኛ አመለካከት ጋር የማይስስማሙ ወንድሞቻችንን እምነት ጥያቄ ውስጥ አናስገባም፡፡ አንድ ሰው ምድር ረጅም ዕድሜ እዳላት የሚያምን አመለካከት በኖረውም የክርስትና እምነት ዋና ዋና አስተምህሮዎች ሊኖረው ይችላል፡፡
እንደ ምድር ዕድሜ ዘመን ያሉ ርዕሶች ናቸው ጳውሎስ በመጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር ባልተቀመጡ ጉዳዩች ከሚገባው በላይ እንዳይጨነቁ የሚለምናቸው፡፡(ሮሜ 14:1–10; ቲቶ 3:9). በመጽሐፍ ቅዱስ የምድር ዕድሜ ዘመን ግልጽ አይደለም፡፡ ዋና ነገርም አይደለም፡፡ አንድ ሰው በምድር ዘመን ዕድሜ ላይ የሚኖረው አመለካከት በኃጢያት በድህነት በስነ ምግባር ስለ ሰማይና ሲኦል የሚኖረው አመለካከት ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ የለውም፡፡ ምድርን ማን እንደፈጠረ ለምን እንደፈጠረ ለእርሱ እኛ አስቀድሞ ማን እንደሆንን የተነገረውን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ በግልጽ ምድርመቼ እንደፈጠረ አይነግረንም፡፡
English
የምድር እድሜ ምንድን ነው? የምድር ዕድሜ ስንት ነው?