ጥያቄ፤
“ሕፃናትና ታዳጊ ልጆች ሲሞቱ ምን ይሆናሉ? የተጠያቂነት ዕድሜን ከመጽሐፍ ቅዱስ የቱጋ ነው የምናገኘው?
መልስ፤
“የተጠያቂነት ዕድሜ” የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ ማለትም ልጆች ስለ ኃጢአታቸው በእግዚአብሔር እንደማይጠየቁ ነው፣ የተወሰነ ዕድሜ ላይ እስከሚደርሱ ድረስ። ማለትም አንድ ልጅ “የተጠያቂነት ዕድሜ” ላይ ከመድረሱ በፊት ቢሞት፣ ያ ሕፃን በእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት ወደ መንግሥተ- ሰማያት እንደሚገባ ዋስትና ያገኛል፣ ለማለት ነው። የተጠያቂነት ዕድሜ ጽንሰ-ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? “የንጽሕና ዕድሜ” ብሎ ነገር አለ ወይ?
የተጠያቂነት ዕድሜን በተመለከተ፣ በውይይቱ ላይ በተደጋጋሚ የሚዘነጋው ልጆች የቱንም ያህል ታዳጊዎች ቢሆኑ ኃጢአት-የለሽ በሚለው ሐሳብ አኳያ “ንጹሕ” አለመሆናቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን አንድ ሕፃን ወይም ታዳጊ ምንም እንኳ የግል ኃጢአት ባይሠራም፣ ሰዎች ሁሉ፣ ሕፃናትንና ልጆችን ጨምሮ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኛ መሆናቸውን ነው፣ ከውርስ እና ከተያያዥ ኃጢአት የተነሣ። የውርስ ኃጢአት የሚባለው ከወላጆቻችን የተላለፈብን ነው። መዝሙር 51፡5 ላይ ዳዊት እንደጻፈው፣ “እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” ይላል። ዳዊት በፅንስ እንኳ እያለ ኃጢአተኛነቱን ተገንዝቧል። ሁነኛው አሳዛኙ ሀቅ፣ ሕፃናት አንዳንዴ ሲሞቱ የሚያመለክተው፣ ሕፃናት አንኳ በአዳም ኃጢአት ተጽዕኖ ሥር መሆናቸውን ነው፤ ሥጋዊና መንፈሳዊ ሞት የአዳም መነሻ ኃጢአት ውጤቶች ከመሆናቸው የተነሣ።
እያንዳንዱ ሰው፣ ሕፃን ወይ አዋቂ፣ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኛ ሆኖ ይቆማል፤ እያንዳንዱ ሰው የአግዚአብሔርን ቅድስና አስከፍቷል። እግዚአብሔር ጻድቅ የሚሆንበት ብቸኛው መንገድ እና በዚያው ጊዜ ግለሰቡን ጻድቅ ነው ብሎ የሚያውጅበት አገባብ፣ ያ ግለሰብ በክርስቶስ ባለው እምነት ይቅርታን ሲያገኝ ነው። ክርስቶስ ብቸኛው መንገድ ነው። ዮሐንስ 14፡6 ኢየሱስ ያለውን አስፍሮታል፡ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” ደግሞም፣ ጴጥሮስ ሐዋርያት ሥራ 4፡12 ላይ እንዳስረገጠው፣ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” ብሏል። ድኅነት/መዳን የግለሰባዊ ምርጫ ነው።
ሕፃናት እና ታዳጊ ልጆች ይሄንን ግለሰባዊ ምርጫ ለማድረግ ፈጽሞ ችሎታ የሌላቸው ምን ሊሆኑ ነው? የተጠያቂነት ዕድሜ ማለት ወደ ተጠያቂነት ዕድሜ ከመድረሳቸው በፊት ለሚሞቱት ጽንሰ-ሐሳብ ሲሆን ወዲያውኑ በእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንደሚድኑ ነው። የተጠያቂነት ዕድሜ የሚለው እምነት እግዚአብሔር ክርስቶስን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ለመወሰን ፈጽሞ ችሎታ የሌላቸውን ሁሉ እንደሚያድን ነው። ስለዚህ ጉዳይ የሚናገር አንድ ቁጥር ሮሜ 1፡20 ነው፣ “የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ።” ከዚህ አኳያ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሰው ልጆች ኃጢአት የተመሠረተው በከፊል፣ ሰዎች “በግልጽ የሚያዩትን” የእግዚአብሔርን ሕልውና፣ ዘላለማዊነቱንና ኃይሉን ባለመቀበላቸው ነው። ይህም “በግልጽ የሚታየውን” ወይም ስለ እግዚአብሔር ማሰብ የማይችሉትን ልጆች ወደ እሚለው ጥያቄ ያመራል - ጉዳዩን ለማስተዋልና ለመገንዘብ ተፈጥሯዊ አለመቻላቸው ምክንያት ሊሰጣቸው ይችላልን?
አስራ ሦስት እጅግ የተሻለ የተለመደ ዕድሜ ነው፣ ለተጠያቂነት ዕድሜ ሐሳብ የተሰነዘረው፣ በአይሁድ ልማድ መሠረት፣ ልጅ በ13 ዓመቱ አዋቂ ይሆናል ተብሎይታሰባል። ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ቀጥተኛ ድጋፍ አይሰጠንም 13 ዓመት ዘወትር የተጠያቂነት ለመሆኑ። እሱም ከልጅ ወደ ልጅ የሚለያይ ይመስላል። የተጠያቂነት ዕድሜን አንድ ጊዜ ያለፈ ልጅ እሱ ወይም እሷ የእምነት ውሳኔን ለማድረግ ብቁ ይሆናሉ፣ ክርስቶስን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል። የቻርለስ ስፑርጆን አስተያየት የሚለው፣ “የአምስት ዓመት ልጅ በርግጥ እንደ አዋቂ ሊድንና ዳግም ሊወለድ ይችላል።”
ከላይ ያለውን በመገንዘብ፣ ደግሞም ይሄንን ግምት ውስጥ እናስገባ፡ የክርስቶስ ሞት የቀረበው ለሰው ልጆች ሁሉ ብቁ ሆኖ ነው። አንደኛ ዮሐንስ 2፡ 2 ይላል፣ ኢየሱስ “እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።” ይህ ቁጥር ግልጽ ነው፣ ማለትም የኢየሱስ ሞት ለኃጢአት ሁሉ በቂ ነው፣ በተለየ ሁኔታ በእምነት ወደ እርሱ ለሚቀርቡት ኃጢአት ብቻ ሳይሆን። የክርስቶስ ሞት ለኃጢአት ሁሉ በቂ የሆነበት ሀቅ፣ እግዚአብሔር ያንን ክፍያ ማመን ፈጽሞ ለማይችሉት ተግባራዊ ለማድረግ ይፈቅዳል።
አንዳንዶች በተጠያቂነት ዕድሜ መካከልና እና በእግዚአብሔርና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ያለውን ኪዳናዊ ግንኙነት አያይዘው ይመለከቱታል፣ ይህም ማለት ወንድ ልጅ በኪዳኑ ለመካተት ከግዝረት ሥርዓት ውጭ ሌላ መስፈርት አልተቀመጠለትም፣ እሱም ከልደቱ ከስምንት ቀን በኋላ የሚፈጸም (ዘፀአት 12:48–50፤ ሌዋውያን 12:3)።
የሚነሣው ጥያቄ፣ “አጠቃላይ ተፈጥሮ ያለው ብሉይ ኪዳን በቤተ ክርስቲያን ተግባራዊ ይደረጋል?” የሚል ነው ። በበዓለ ኀምሳ ቀን ጴጥሮስ እንዳለው፣ “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና።”” (ሐዋ. 2:38–39)። እዚህጋ ልጆች የሚለው ቃል (በግሪክ teknonቴክኖን) ፍችው “ልጅ፣ ሴት ልጅ፣ ወንድ ልጅ” ማለት ነው። ሐዋ. 2፡39 የሚያመለክተው የኃጢአት ይቅርታ ለአንዱ እና ለሁሉም መገኘቱን ነው (ሐዋ. 1፡8) መጪውንም ትውልድ ጨምሮ። እሱም ቤተሰባዊ ወይም የቅርብ ዝምድናዊ መዳንን አያስተምርም። ንስሐ የገቡት ሰዎች ልጆች ንስሐ መግባት ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ ርዕሰ-ጉዳይ አኳያ ከሌሎቹ ይልቅ በተሻለ የሚጠቀሰው አንቀጽ 2 ሳሙኤል 12፡21-23 ነው። የእነዚህ ቁጥሮች ዐውደ-ጽሑፍ ንጕሥ ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ዝሙት መፈጸሙ ነው፣ ርግዝናን አስከትሎ። ነቢዩ ናታን በእግዚአብሔር ተልኮ ለዳዊት ለመንገር ሄደ፣ ማለትም በእርሱ ኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር ልጁን በሞት እንደሚወስደው። ዳዊት ለዚህ የሰጠው ምላሽ ስለ ሕፃኑ በኀዘንና በጸሎት መቅረብ ነው። ነገር ግን ሕፃኑ አንድ ጊዜ ከተወሰደ በኋላ፣ የዳዊት ኀዘን አቆመ። የዳዊት አገልጋዮች ይሄንን በመስማት ተደነቁ። እነርሱም ንጕሥ ዳዊትን አሉት፣ “ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድር ነው? በሕይወት ሳለ ስለ ሕፃኑ ጾምህና አለቀስህ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ።” የዳዊት ምላሽም፣ “ሕፃኑ ሕያው ሳለ። እግዚአብሔር ይምረኝ፥ ሕፃኑም በሕይወት ይኖር እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ብዬ ጾምሁ አለቅሰሁም። አሁን ግን ሞቶአል የምጾመው ስለ ምንድር ነው? በውኑ እንግዲህ እመልሰው ዘንድ ይቻለኛልን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም” አለ። የዳዊት ምላሽ የሚያመለክተው፣ ማመን ያልቻሉት በጌታ መዳናቸውን ነው። ዳዊት እንዳለው፣ እሱ ወደ ሕፃኑ ሊሄድ ይችላል፣ ነገር ግን ሕፃኑን መልሶ ወደ እርሱ ሊያመጣው እንደማይችል ነው። ደግሞም፣ እንደ ጠቀሜታ፣ ዳዊት ይሄንን በማወቁ የተጽናና ይመስላል። በሌላ አገላለጽ፣ ዳዊት ሕፃን ወንድ ልጁን (በመንግሥተ ሰማይ) እንደሚያየው፣ የሚል ይመስላል፣ ምንም እንኳ መልሶ ማምጣት ባይቻለውም።
ምንም እንኳ እግዚአብሔር፣ ክርስቶስ ለኃጢአት የከፈለውን ዋጋ ማመን ለማይችሉት ተግባራዊ ማድረግ ቢችልም፣ መጽሐፍ ቅዱስ በተለየ መልኩ ይሄንን እንደሚያደርግ አይገልጽም። ስለዚህ፣ ይህ ርዕሰ-ጉዳይ ግትር ወይም ቀኖናዊ የሚያደርገን አይደለም። እግዚአብሔር የክርስቶስን ሞት ማመን ለማይችሉት ተግባራዊ የሚያደርገው፣ ሊሆን የሚችለው ከፍቅሩና ከምሕረቱ ቋሚነት አኳያ ነው። እግዚአብሔር፣ ክርስቶስ ለኃጢአት የከፈለውን ዋጋ ለሕፃናትና የአዕምሮ ድኩማን ለሆኑ ተግባራዊ እንደሚያደርገው አቋማችን ነው፣ ይኸውም እነርሱ ኃጢአተኛ ተፈጥሯቸውንና አዳኝ እንደሚያስፈልጋቸው በአዕምሯቸው መረዳት ስለማይችሉ፤ ነገር ግን አሁንም በድጋሚ ቀኖናዊ መሆን አንችልም። በዚህ ላይ ርግጠኞች ነን፡ እግዚአብሔር አፍቃሪ፣ ቅዱስ፣ መሐሪ፣ ጻድቅ፣ እና ደግ ለመሆኑ። እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ዘወትር ትክክለኛና መልካም ነው፣ እናም እሱ ሕፃናትን ይወዳል፣ እኛ ከምናደርገው ይልቅ።
English
“ሕፃናትና ታዳጊ ልጆች ሲሞቱ ምን ይሆናሉ? የተጠያቂነት ዕድሜን ከመጽሐፍ ቅዱስ የቱጋ ነው የምናገኘው?