ጥያቄ፤
ኖስቲሲዝም ምንድን ነው?
መልስ፤
ኖስቲሲዝም የእግዚአብሔርን መኖር ማወቅ ወይም ማረጋገጥ አይቻልም የሚል አመለካከት ነው፡፡ኖስቲክ / agnostic/ የሚለው ቃል በመሰረቱ ያለእውቀት መሆን “without knowledge.” ማለት ነው፡፡ ኖስቲሲዝም በእወቀት የሆነ የእግዚአብሔር የለሾች ክህደት ነው፡፡ ክህደት /atheism/ የሚለው ሊረጋገጥ በማይችልበት መልኩ እግዚአብሔር የለም ነው የሚለው፡፡ ኖስቲሲዝም የሚከራከረው የእግዚአብሔርን መኖር ማረጋገጥ ይቻላል ውይም አይቻልም፤ ለዛም እግዚአብሔር መኖሩን ወይም አለመኖሩን ማወቅ አይቻልም በማለት ነው፡፡ በዚህ ኖስቲሲዝም ትክክል ነው፤ የእግዚአብሔርነ መኖር በተግባር በተፈተነ በተለመደ መልኩ ማረጋገጥ ወይም አለማረጋገጥ አይቻልም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት መቀበል እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ዕብ 11፡6፤- ‹‹ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።›› እግዚአብሔረ መንፈስ ነው፡፡ (ዮሐ 4:24) ስለዚህም በዓይን ሊታይ ወይም ሊዳሰስ አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጠ ካልወደደ በቀር በእኛ የስሜት ህዋስ ሊታይ አይችልም፡፡ (ሮሜ 1:20). መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የእግዚአብሔር መኖር እንዲሁ በፍጥረት ላይ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡ (መዝ 19:1-4) በተፈጥሮ ውስጥ ሊታወቅ ይችላል፡፡ (ሮሜ 1:18-22) በልባችን ደግሞ እርግጠኞች እንሆናለን፡፡ (መክ 3:11).
ኖስቲሲዝም የእግዚአብሔርን መኖር ወይም አለመኖር ማረጋገጥ አይፈልግም፡፡ እንዲሁ በአጥሩ ዙሪያ ርቆ እንደመቆም አይነት “straddling the fence” ነው፡፡ አማኒያን /Theists/ እግዚአብሔር አለ ብለው ያምናሉ፡፡ አምላክ የለሽ ካሃዲዎች /atheism/ እግኢአብሔር የለም ብለው ያምናሉ፡፡ ኖስቲስዝም/agnosticism/ እግዚአብሔር አለ ወይም የለም ብለን ማመን የለብንም ብሎ ያምናል፤ ምክንያቱም በሁለቱም መልኩ ማወቅ ስለማይቻል፡፡
ለክርክር እንዲሆነን የእግዚአብሔርን መኖር በግልጽና በማይካድ መልኩ ሊያረጋግጥልን የሚችል መረጃ እናንሳ፡፡ ሴይዝም /አማኒያን/ እና ኖስቲሲዝምን በአንድ ተርታ ብናስቀምጥ የትኛው ነው ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ የበለጠ መረዳት ሊሰጠን የሚችለው? እግዚአብሔር ከሌለ ሴይዝም /አማኒያን/ እና ኖስቲስዝም ተቀባይነት በሌለው መልኩ ከሞት በኋላ መኖር አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር ካለ ግን ኖስቲሲኮች /agnosticism/ እና በሚሞቱበት ጊዜ ምላሽ የሚሰጥላቸው ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከዚህ ሃሳብ በመነሳት ኖስቲክ/agnosticism/ ከመሆን ወይም በኖስቲስዝም ከማመን ይልቅ ሴይዝም አማንያን መሆን ትርጉም ይሰጣል፡፡ በሁለቱም ስፍራ በመሆን ሊረጋገጥ ቢችልም ባይችልም መጨረሻ በሌለው እና በዘለአለም ተገቢውን ውጤት ሊያስገኝ የሚችለውን ስፍራ በሂደት መፈተን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ጥበበኘነት ሳይሆን አይቀርም
የጥርጣሬ መኖር የተለመደ ነገር ነው፡፡ በዚህ አለም ላይ ልንረዳቸው የማንችላቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ብዙዎች የእግዚአብሔርን መኖር ይጠራጠራሉ ምክንያቱም እርሱ በሰራቸውና በፈቀዳቸው ነገሮች አይስማሙም ውይም አልተረዱትም፡፡ ሆኖም ግን እኛ ውስን የሆንን ሰዎች ወሰን የሌለውን አምላክ ልንረዳው አንችልም፡፡
ሮሜ 11:33-34፡-‹‹የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው? ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?›› በእምነት በእግዚአብሔር ልናምን ይገባል፤ መንገዱንም በእምነት ልንታመነው ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ ለሚያምኑ በአስደናቂ ሁኔታ ራሱን ለመግለጽ ፈቃደኛ እና ዝግጁ ነው፡፡ ዘዳ 4፡26 ‹‹ ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።
English
ኖስቲሲዝም ምንድን ነው?