settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሰክር መጠጥ ወይንም ወይን ስለ መጠጣት ምን ይላል? ለክርስቲያን የሚያሰክር መጠጥ ወይም ወይንን መጠጣት ኃጥአት ነውን?

መልስ፤


መጠጥ መጠጣትን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ብዙ የሚለው አለው (ኦሪት ዘሌዋውያን 10፤9፤ ኦሪት ዘኁልቁ 6፤3፤ ኦሪት ዘዳግም 29፤6፤ መጽሐፈ መሳፍንት 13፤4,7,14፤ መጽሐፈ ምሳሌ 20፤1፤31፤4፤ትንቢተ ኢሳይያስ 5፤11,22፤24፤9,28፤7, 29፤9, 56፤12)፡፡ ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች የግድ ቢራ፤ወይን፤ወይም የሚያሰክር ነገር ያለውን ማንኛውንም መጠጥ አይከለክልም፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ቅዱሳን መጽሐፍቶች የሚያሰክር መጠጥን በአዎንታዊ መልኩ ያነሱታል፡፡ መጽሐፈ መክብብ 9፤7 “የወይን ጠጅህን በተድላ ጠጣው” ብሎ ያዛል፡፡ መዝሙረ ዳዊት 104፤14-15 እግዚአብሔር “የሰዎችን ልጆች ልብ ደስ የሚያሰኝን ወይን እንደሚሰጥ” ይጠቅሳል፡፡ ትንቢተ አሞጽ 9፤14 እንደ እግዚአብሔር ባርኮት ምልክት ከወይን ተክል እርሻዎችህ ወይን መጠጣትን ያነሳል፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስ 55፤1፤አዎ፤ኑ፤የወይን ጠጅን እና ወተትን ግዙ…” እያለ ያደፋፍራል፡፡

እግዚአብሔር የሚያሰክር መጠጥን በተመለከተ ክርስቲያኖችን የሚያዘው ስካር ማስወገድን ነው (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፤18)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስካርን እና ተጽዕኖውን ይነቅፋል (መጽሐፈ ምሳሌ 23፤29-35)፡፡ በተጨማሪም ክርስቲያኖች አካሎቻቸው ለአንዳች ነገር “መገዛትን” እንዳይፈቅዱ ታዘዋል (1ኛ ቆሮንቶስ 6፤12፤ 2ኛ ጴጥሮስ 2፤19)፡፡ አብዝቶ የሚያሰክርን መጠጥ መጠጣት ያለ ጥርጥር ሱሰኝነት ነው፡፡ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ምናልባት ሌሎች ክርስቲያኖችን የማያስደስተውን ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወይም በህሊናቸው ላይ ኃጥአት ማድረግን ይከለክላል (1ኛ ቆሮንቶስ 8፤9-13)፡፡ በእነዚህ መርሆች ምልከታ ለማንኛውም ክርስቲያን እሱ ለእግዚአብሔር ክብር አብዝቶ የሚያሰክር መጠጥ እየጠጣ ነው ማለት በጣም አስቸጋሪ ይሆናል(1ኛ ቆሮንቶስ 10፤31)፡፡

ኢየሱስ ውሃን ወደ ወይን ለወጠ፡፡ እንዲያውም ኢየሱስ በሥርዓቱ ላይ የወይን ጠጅ የጠጣ ይመስላል (የዮሐንስ ወንጌል 2፤1-11፤የማቴዎስ ወንጌል 26፤29)፡፡ በአዲሱ ኪዳን ዘመናት ውሃው በጣም ንጹህ አልነበረም፡፡ ያለ ዘመናዊ ንጽህና ውሃው በተደጋጋሚ በረቂቅ ነፍሳት (በባክቴሪያዎች)፤በቫይረሶች እና በሁሉም ዓይነት በካይ ነገሮች ተሞልቶ ነበር፡፡ ዛሬ በብዙ የሦስተኛ ዓለም ሀገሮችም አንደዚያው ነው፡፡ ስለሆነም ሰዎች ብዙውን ጊዜ የወይን ጠጅ (ወይም የወይን ጭማቂ) ይጠጡ ነበር ምክንያቱም የመበከል ዕድሉ እጅግ አናሳ ነበር፡፡ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 5፤23 ጳውሎስ ጢሞቴዎስ ውሃ መጠጣትን እንዲያቆም (ምናልባት የሆድ ህመሙን ያመጣበትን) እና በምትኩ የወይን ጠጅን እንዲጠጣ እያዘዘው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን የወይን ጠጅ የፈላ (የሚያሰክርን ነገር ያለው) ነበር፤ የግድ ዛሬ ባለው መጠን መሆን ግን የለበትም፡፡ የወይን ጭማቂ ነበር ማለት ትክክል አይደለም፤በተጨማሪም ግን ዛሬ በግልጋሎት ላይ እንዳለው ዓይነት የወይን ጠጅ ተመሳሳይ ነገር ነበር ማለት ትክክል አይደለም፡፡ እንደገና ቅዱሳት መጽሐፍት ክርስቲያኖች ቢራ፤ ወይን፤ወይም የሚያሰክር ነገር ያለበትን ማንኛውንም ሌላ መጠጥ እንዳይጠጡ አይከለክልም፡፡ የሚያሰክር መጠጥ በውስጡ እና በራሱ በኃጥአት አልተበከለም፡፡ ክርስቲያን የግድ ሙሉ ለሙሉ ራሱን መጠበቅ ያለበት ለሚያሰክር መጠጥ ከስካር እና ከሱሰኝነት መሆን አለበት (ወደ ኤፈሶን ሰዎች 5፤18፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፤12)፡፡

በጥቂት መጠን የተወሰደ የሚያሰክር መጠጥ የሚጎዳም ሱሰኛም አያደርግም፡፡ በእርግጥ የተወሰኑ ሐኪሞች ለጤንነት ጥቅሙ ሳይበዛ ቀይ የወይን ጠጅን መጠጣት በተለይም ለልብ እንደሚጠቅም አጥብቀው ያውጃሉ፡፡ የተወሰነ መጠን ያለው መጠጥ መጠጣት የክርስትና ነጻነት ጉዳይ ነው፡፡ ስካር እና ሱሰኝነት ኃጥአት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሚያሰክርን መጠጥ እና ተጽዕኖውን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆኑ ጉዳዮች ምክንያት፤የሚያሰክርን መጠጥ ያለ ልክ ለመጠጣት በቀላሉ ለመወሰድ ባለው ፈተና ምክንያት፤ሌሎችን ሊያስቀይም የሚችል ዕድል ያለው በመሆኑ ምክንያት፤ለክርስቲያን የሚያሰክርን መጠጥ ከመጠጣት ሙሉ ለሙሉ መታቀቡ ብዙውን ጊዜ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሰክር መጠጥ ወይንም ወይን ስለ መጠጣት ምን ይላል? ለክርስቲያን የሚያሰክር መጠጥ ወይም ወይንን መጠጣት ኃጥአት ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries