settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አንዴ ከዳንክ ሁሌም ድነሃል?

መልስ፤


መልስ፤ አንድ ሰው አንድ ጊዜ ከዳነ ሁሌም ድነዋል? ሰዎች ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ወደ ማወቅ ሲመጡ የዘላለማዊ ዋስትናቸውን አስተማማኛ ወደሚያደርግ ከእግዚአብሔር ጋር ወደሆነ ህብረት መጥቷል፡፡ የብዙ ቅዱሳን መጽሐፍት ምንባቦች ይህንን እውነታ ያውጃሉ፡፡ (ሀ) ወደ ሮሜ ሰዎች 8፤30፤ “አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።” ያውጃል፡፡ ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር እኛን ከመረጠበት ጊዜ አንስቶ እሱ ባለበት በሰማያዊ ሥፍራ እንደከበርን ነው፡፡ አማኝን አንድ ቀን ከመክበር ሊከለክል የሚችል አንድም ነገር የለም፤ምክንያቱም እግዚአብሔር አስቀድሞ በሰማይ ወስኖታልና፡፡ አንድ ሰው አንዴ ከጸደቀ ድነቱ አስተማማኝ ነው፤በሰማይ አስቀድሞ እንደ ከበረ ያህል ከሥጋት የነጻ ነው፡፡

(ለ) ጳውሎስ በሮሜ 8፤33-34 ውስጥ ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ይጠይቃል፤“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በእግዚአብሔር ምርጦች ላይ ክስን ማን ያመጣል? ማንም ሰው አያመጣም ምክንያቱም ክርስቶስ የእኛ ጠበቃ ነው፡፡ የሚኰንነን ማን ነው? ማንም አይኰንነንም ምክንያቱም ለእኛ የሞተው ክርስቶስ የሚኰንነን እሱ ነው፡፡ እንደ እኛ አዳኝ ሁለቱንም ጠበቃ እና ፈራጅ አለን፡፡

(ሐ) አማኞች ሲያምኑ ዳግም የተወለዱ (እንደገና የታደሱ) ናቸው (የዮሐንስ ወንጌል 3፤3፤ወደ ቲቶ 3፤5)፡፡ ለክርስቲያን ድነቱን ለማጣት እንደገና ያልታደሰ መሆን ይኖርበታል፡፡ አዲስ ልደት ሊወሰድ እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ዓይነት ማስረጃ አይሰጥም፡፡ (መ) መንፈስ ቅዱስ በሁሉም አማኞች ውስጥ ይሆናል (የዮሐንስ ወንጌል14፤17፤ወደ ሮሜ ሰዎች 8፤9) እና ለክርስቶስ አካል ሁሉንም አማኞች ያጠምቃል(1ኛ ቆሮንቶስ 12፤13)፡፡ ለአማኝ ያልዳነ ለመሆን በክርስቶስ አካል ውስጥ የሌለ እና የተለየ መሆን አለበት፡፡

(ሠ) የዮሐንስ ወንጌል 3፤15 ማንም በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምን “የዘላለም ህይወት እንዳለው” ያን ይጠቅሳል፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ብታምን እና የዘላለም ህይወት ቢኖርህ ነገር ግን ነገ ብታጣው ከዚያ ፈጽሞ “ዘላለማዊ” አልነበረም፡፡ ስለዚህ ድነትህን ብታጣው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው የዘላለም ህይወት ተስፋዎች በስህተት ውስጥ ይሆናሉ፡፡ (ረ) በጣም ወደ ድምዳሜ ለሚያመጣው ክርክር ራሱ ቅዱስ መጽሐፍ በተሻለ እንደሚል አስባለሁ፤ “ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።” (ወደ ሮሜ ሰዎች 8፤38-39)፡፡ አስታውስ ያዳነህ ያው እግዚአብሔር የሚጠብቅህም ያው እግዚአብሔር ነው፡፡ አንድ ጊዜ ከዳንን ሁሌም ድነናል፡፡ ድነታችን በጣም በእርግጠኝነት በዘላለማዊው ሥጋት የሌለበት ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አንዴ ከዳንክ ሁሌም ድነሃል?
© Copyright Got Questions Ministries