settings icon
share icon
ጥያቄ፤

“እግዚአብሔር የእንስሳት መሥዋዕቶችን በብሉይ ኪዳን ለምን ይጠይቃል?

መልስ፤


እግዚአብሔር የእንስሳት መሥዋዕትን የፈለገው ጊዜያዊ የኃጢአት ይቅርታን ለመስጠት እና ፍጹም ሆኖ የተጠናቀቀውን የኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕትነት በንግር/በጥላነት ለማመላከት ነው (ሌዋውያን 4:35፣ 5:10)። የእንስሳ መሥዋዕት በቅዱስ ቃሉ ውስጥ ሁሉ የሚገኝ ጠቃሚ ጭብጥ ነው፣ ምክንያቱም፣ “ደም ሳይፈስ ሥርየት የለም” እንደ ተባለ (ዕብራውያን 9፡22)። አዳምና ሔዋን ኃጢአት ሲሠሩ እንስሳት በእግዚአብሔር ተገድለዋል፣ ለእነርሱ ልብስ ለመስጠት ሲባል (ዘፍጥረት 3፡21)። ቃየንና አቤል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርበዋል። የቃየን ተቀባይነት አላገኘም፣ ምክንያቱም ከምድር ፍሬ ስላቀረበ፣ የአቤል ግን ተቀባይነትን አገኘ፣ ምክንያቱም “ከመንጋው በኵራት” ስለሆነ (ዘፍጥረት 4፡4-5)። የጥፋት ውኃ እንደቀነሰ፣ ኖኅ እንሰሳትን በመሥዋዕትነት ለእግዚአብሔር አቅርቧል (ዘፍጥረት 8:20-21)።

እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ የተለያዩ መሥዋዕቶችን እንዲያቀርቡ አዟል፣ በእግዚአብሔር በተገለጡ አንዳንድ ደንቦች መሠረት። በቀዳሚነት፣ እንሰሳው ነውር የሌለበት መሆን አለበት። ሁለተኛም፣ መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው ከእንሰሳው ጋር መገለጥ አለበት። ሦስተኛ፣ እንሰሳውን መሥዋዕት የሚያቀርበው ሰው ግድያውን መፈጸም ይኖርበታል። ይህም በእምነት በሚደረግበት ጊዜ፣ መሥዋዕቱ የኃጢአት ይቅርታን ያስገኛል። ሌለኛው መሥዋዕት፣ በበደል መሥዋዕት ቀን የሚቀርበውና ሌዋውያን 16 ላይ የተገለጸው ሲሆን፣ እሱም ይቅርታንና የኃጢአት ሥርየትን የሚያስገኝ ነው። ሊቀ ካህኑ ሁለት ወንዶች ፍየሎች ለኃጢአት መሥዋዕት ይወስዳል። አንደኛው ፍየል ለእስራኤል ሕዝቦች ለኃጢአት መሥዋዕት ይሠዋል (ሌዋውያን 16፡15)፣ ሌለኛው ፍየል ደግሞ ወደ ምድረ በዳ ይለቀቃል (ሌዋውያን 16፡20-22)። የኃጢአት መሥዋዕት ይቅርታን ሲያስገኝ፣ ሌላው ፍየል ደግሞ የኃጢአትን መወገድ ያስገኛል።

እንግዲያውስ፣ ከአሁን በኋላ ለምን የእንስሳ መሥዋዕት አይቀርብም? የእንስሳት መሥዋዕቶች አብቅተዋል፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የመዳረሻና ፍጹም መሥዋዕት በመሆኑ። መጥምቁ ዮሐንስ ለዚህ እውቅና ሰጥቷል፣ ኢየሱስ ለመጠመቅ ሲመጣ በተመለከተው ጊዜ፣ እናም አለ፣ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!” (ዮሐንስ 1፡29)። ራሳችሁን ልትጠይቁ ትችላላችሁ፣ ለምን እንስሳት? በሚል። ምን የፈጸሙት በደል አለ? ነጥቡ ያ ነው - እንስሳት ምንም ዓይነት በደል ካለመፈጸማቸው የተነሣ፣ መሥዋዕቱን በሚያቀርበው ሰው ምትክ ይሞታሉ። ኢየሱስ ክርስቶስም ደግሞ ምንም በደል አልፈጸመም፣ ነገር ግን ራሱን በፈቃደኝነት ለሰው ልጆች ኃጠአት ለመሞት አሳልፎ ሰጠ (1 ጢሞቴዎስ 2፡6) ። ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን በራሱ ላይ ወሰደ፣ በእኛም ምትክ ሞተ። 2 ቆሮንቶስ 5፡21እንደሚለው፣ “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።” ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባስገኘው የምናምን፣ እኛ ይቅርታን መቀበል እንችላለን።

ለማጠቃለልም፣ የእንስሳ መሥዋዕቶች የታዘዙት በእግዚአብሔር ነው፣ ግለሰቦች የኃጢአትን ይቅርታ ያገኙባቸው ዘንድ። በምትክነት የሚያገለግለው እንሰሳ ማለትም፣ በኃጢአተኛው ምትክ የሚሞተው እንሰሳ፣ ነገር ግን በጊዜያዊነት ብቻ ነው፣ በዚህን ምክንያት ነው መሥዋዕቱ በየጊዜው እንዲቀርብ ያስፈለገው። የእንሰሳት መሥዋዕት በኢየሱስ ክርስቶስ አቁሟል። ኢየሱስ ክርስቶስ የመዳረሻው ምትክ መሥዋዕት ነው፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ (ዕብራውያን 7፡27) እናም አሁን በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ብቸኛው መካከለኛ ነው (1 ጢሞቴዎስ 2፡5)። የእንስሳ መሥዋዕት ክርስቶስ በእኛ ምትክ ለመሠዋቱ ንግር/ጥላ ነው። የእንስሳት መሥዋዕት የኃጢአትን ሥርየት የሚያስገኝበት ብቸኛው መሠረት፣ ራሱን ስለ ኃጢአታችን መሥዋዕት ያደረገው ክርስቶስ ነው፣ እሱም የእንስሳት መሥዋዕት የሚያስገኘው ይቅርታ፣ ይኸውም ማሳያና ንግር የሆነ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

“እግዚአብሔር የእንስሳት መሥዋዕቶችን በብሉይ ኪዳን ለምን ይጠይቃል?
© Copyright Got Questions Ministries