ጥያቄ፤
“ደኅንነታችን ዘላለማዊነቱ የተረጋገጠ ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ክህደትን ለምን በብርቱ ተቃርኖ ያስጠነቅቃል?
መልስ፤
መጽሐፍ ቅዱስ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዳግም የተወለደ ሁሉ ለዘላለም እንደ ዳነ ያስተምረናል። እኛ የዘላለም ሕይወት ስጦታን ተቀብለናል (ዮሐንስ 10፡28)፣ ጊዜያዊ ሕይወት ሳይሆን። ዳግም የተወለደ አንዱ (ዮሐንስ 3፡3) “ያልተወለደ” ሊሆን አይችልም። ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብ ልጅነት ከገባን በኋላ (ሮሜ 8፡15)፣ ልንወጣ አንችልም። እግዚአብሔር ሥራ ሲጀምር፣ እሱ ይጨርሰዋል (ፊሊጵስዩስ 1፡6)። ስለዚህ፣ የእግዚአብሔር ልጅ- በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን - በዘላለማዊነት ደኅንነቱ ይጠበቃል።
ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ክህደትን በተመለከተ አንዳንድ ጠንከር ያሉ የተቃውሞ ማስጠንቀቂያዎችን ይዟል። እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች አንዳንዶችን የዘላለም ደኅንነት ዶክትሪንን እንዲጠራጠሩ እየመራቸው ነው። ከሁሉም በላይ፣ ደኅንነታችንን የማናጣ ካልሆነ፣ ከጌታ ዘንድ ርቆ ስለመውደቅ ለምን ማስጠንቂያ ይሰጠናል? ይህ መልካም ጥያቄ ነው። በቅድሚያ፣ “ክህደት/ሃይማኖትን መተው” ምን ማለት እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል።
ከሀዲ ማለት ሃይማኖታዊ እምነቱን የተወ ሰው ማለት ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ እንደሆነው፣ ከሀዲዎች ሙያዊ እምነታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያደረጉ ሰዎች መሆናቸው ይታወቃል፣ ነገር ግን ፈጽሞ በቅንነት እሱን እንደ አዳኝ አድርገው አልተቀበሉትም። እነርሱ አስመሳይ አማኞች ነበሩ። ከክርስቶስ ተለይተው የሚሄዱ እነርሱ፣ በርግጥ ከመነሻቸውም፣ ፈጽሞ አላመኑትም፣ 1 ዮሐንስ 2፡19 እንደሚለው፣ “ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።” ሃይማኖትን የሚተዉ እነርሱ፣ እንዲያው እውነተኛ አማኝ አለመሆናቸውን ያሳያሉ፣ እናም ፈጽሞ አልነበሩም።
የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ (ማቴዎስ 13፡24-30) ስለ ከሀዲነት ቀላል ገለጻ ይሰጣል። በተመሳሳይ ማሳ ላይ ስንዴ እና “የውሸት ስንዴ” (እንክርዳድ ውይም አረም) በቅሏል። በቅድሚያ፣ በሁለቱ ዕጽዋት መካከል ያለው ልዩነት አልለየም፣ ነገር ግን ጊዜ እየጨመረ ሲሄድ፣ አረሙ በነበረበት ሁኔታ ታየ። በተመሳሳይ መንገድ፣ ዛሬ በአንዱ ቤተ ክርስቲያን፣ እውነተኛ፣ ዳግም የተወለዱ አማኞች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ከአስመሳዮች በትይዩ - እነርሱም በመልዕክቶቹ፣ በዝማሬው፣ እና በኅብረቱ የሚደሰቱ፣ ነገር ግን ስለ ኃጢአታቸው ንስሐ ያልገቡና ክርስቶስን በእምነት ያልተቀበሉ ናቸው። ለማንኛውም ተመልካች ሰው፣ እውነተኛው አማኝና አስመሳዩ መንታ ይመስሉታል። እግዚአብሔር ብቻ ነው ልብን ማየት የሚችለው። ማቴዎስ 13፡1-9 (የዘሪው ምሳሌ) ሌላኛው በተግባር ላይ ላለው ክህደት መግለጫ ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ማስጠንቀቂያዎች ክህደትን ተቃርነው ይኖራሉ፣ ምክንያቱም ሁለት ዓይነት ሃይማኖታዊ ሰዎች ስለሚኖሩ፡ አማኞች እና የማያምኑ። በማንኛውም ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን በእውነት የሚያውቁ እና በመለዋወጥ ውስጥ የሚጓዙ ይኖራሉ። “ክርስቲያን” የሚለውን መታወቂያ ማድረግ ለልብ መለወጥ ዋስትና አይሆንም። ቃሉን መስማት ይቻላል፣ ብሎም ከእሱ እውነት ጋር መስማማት፣ እሱን ወደ ልብ ሳያስገቡ። በቤተ ክርስቲያን መገኘት ይቻላል፣ በአገልግሎትም መሳተፍ፣ ብሎም ራስን ክርስቲያን ብሎ መጥራት - እናም ገና ያልዳኑ መሆን (ማቴዎስ 7:21–23)። ነቢዩ እንዳለው፣ “ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈርቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና“ (ኢሳይያስ 29:13፤ ማርቆስ 7:6)።
እግዚአብሔር አስመሳይን ያስጠነቅቃል፣ በአግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጦ ወንጌልን እሑድ እሑድ የሚያደምጠውን፣ በእሳት እየተጫወተ እንደሆነ። ዞሮ ዞሮ፣ አስመሳይ ይክዳል - እሱም “ወድቆ ይቀራል”፣ በአንድ ወቅት ከመሰከረለት እምነት - ንስሐ እስካልገባ ድረስ። ልክ በስንዴ መሐል እንዳለ እንክርዳድ እውነተኛ ማንነቱ ይጋለጣል።
ክህደትን በመቃወም የሚያስጠነቅቁት ምንባቦች ለሁለት ቀዳሚ ዓላማዎች ይጠቅማሉ። በቅድሚያ፣ እያንዳንዱ ስለ መዳኑ ርግጠኛ እንዲሆን ያበረታታሉ። የአንዱ ዘላለማዊ መዳረሻ ችላ የሚባል ነገር አይደለም። ጳውሎስ 2 ቆሮንቶስ 13፡5 ላይ ራሳችንን እንድንመረምር ይነግረናል፣ “በእምነት” ስለ መሆናችን።
አንደኛው የእውነተኛ እምነት መፈተሻ ለሌሎች ያለ ፍቅር ነው (1 ዮሐንስ 4፡7-8)። ሌላው ደግሞ መልካም ሥራ ነው። ማንም ክርስቲያን እንደሆነ ሊገልጽ ይችላል፣ ነገር ግን እነርሱ በርግጥ የዳኑ “ፍሬ” ያፈራሉ። እውነተኛ ክርስቲያን በቃላት በኩል፣ በድርጊት፣ እና በዶክትሪን ጌታን እንደሚከተል ያሳያል። ክርስቲያኖች በተለያየ መጠን ፍሬ ያፈራሉ፣ በመታዘዛቸው ደረጃና በመንፈሳዊ ስጦታዎቻቸው ላይ በመመሥረት፣ ነገር ግን ሁሉም ክርስቲያኖች ፍሬ ያፈራሉ፣ መንፈስ በውስጣቸው እንደሚያፈራው መጠን (ገላትያ 5፡22-23)። እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች የደኅንነታቸውን ማስረጃ እንደሚመለከቱ ሁሉ (1 ዮሐንስ 4፡13 ተመልከት)፣ እንዲሁ ከሀዲዎችም በግልጽ በፍሬአቸው ይታወቃሉ (ማቴዎስ 7፡16-20) ወይም በሌላው መልኩ አይገኝባቸውም (ዮሐንስ 15፡2)።
መጽሐፍ ቅዱስ ክህደትን በመቃወም የሚያስጠነቅቅበት ሁለተኛው ዓላማ፣ ቤተ ክርስቲያን ከሀዲዎችን እንድትለይ ለማብቃት ነው። እነርሱ ክርስቶስን በመተዋቸው ሊታወቁ ይችላሉ፣ መናፍቅነትን ይቀበላሉ፣ ብሎም ሥጋዊ ባሕርይ አላቸው (2 ጴጥሮስ 2፡1-3)።
ስለዚህ፣ ክህደትን በመቃወም የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስጠንቀቂያዎች፣ በ“እምነት” ጥላ ሥር ሆነው፣ ነገር ግን በእውነት ተግባራዊ የሆነ እምነት የሌላቸውን ለማስጠንቀቅ ነው። ቅዱስ ቃሉ፣ እንደ ዕብራውያን 6፡4-6 እና ዕብራውያን 10፡26-29 የመሳሰሉት “ለአስመሳይ” አማኞች ማስጠንቀቂያዎች ናቸው፣ ማለትም በጣም ሳይዘገይባቸው ራሳቸውን መመርመር እንደሚገባቸው። ማቴዎስ 7፡22-23 የሚያመለክተው፣ “አስመሳይ አማኞች” እነርሱም ጌታ ለፍርድ ቀን የተዋቸው፣ የተተዉት “እምነታቸውን በማጣታቸው” ምክንያት አይደለም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ፈጽሞ ስለማያውቃቸው ነው። እነርሱ ከእርሱ ጋር ፈጽሞ ግንኙነት አልነበራቸውም።
ብዙ ሰዎች አሉ፣ ለሃይማኖት ሲባል ሃይማኖትን የሚወዱ፣ ብሎም ራሳቸውን ከኢየሱስ እና ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንደሆኑ ለመግለጽ ፍቃደኛ የሆኑ። ማነው የዘላለም ሕይወትና በረከትን የማይፈልግ? ሆኖም፣ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርትነት “ዋጋችንን እንድንቆጥር” አስጠንቅቆናል (ሉቃስ 9:23–26፤ 14:25–33)። እውነተኛ አማኞች ዋጋቸውን/ከሳራቸውን ይቆጥራሉ፣ ከዚያም ውሳኔ ያደርጋሉ፤ ከሀዲዎች ግን እንዲህ ማድረግ አይችሉም። ከሀዲዎች በአንድ ወቅት ሙያዊ እምነት ነበራቸው፣ ነገር ግን የእምነት ውርስ ሳይሆን። አንደበታቸው አንድ ነገር ይናገራል፣ ልባቸው ከሚያምነው በተለየ። ክህደት ደኅንነትን ማጣት አይደለም፣ ነገር ግን ያለፈው አስመሳይነት ማስረጃ እንጂ።
English
“ደኅንነታችን ዘላለማዊነቱ የተረጋገጠ ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ክህደትን ለምን በብርቱ ተቃርኖ ያስጠነቅቃል?