ጥያቄ፤
የደኅንነቴ ዋስትና እንዴት ሊኖረኝ ይችላል?
መልስ፤
መዳናችሁን እንዴት በርግጠኝነት ልታውቁ ትችላላችሁ? 1ኛ ዮሐንስ 5፡11-13ን ተመልከቱ፡ “እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።” ልጁ ያለው ማን ነው? እነሱ በእሱ የሚያምኑና የተቀበሉት ናቸው (ዮሐንስ 1፡12)። ኢየሱስ ካላችሁ ሕይወት አላችሁ። ጊዜያዊ ሕይወት አይደለም፣ ዘላለማዊ እንጂ።
እግዚአብሔር የደኅንነታችን ዋስትና እንዲኖረን ይፈልጋል። የክርስትና ሕይወታችን በየዕለቱ የመንከራተትና የመጨነቅ እንዲሆን አይፈልግም፣ በርግጠኝነት ለመዳናችን ወይም ላለመዳናችን። በዚህን ምክንያት ነው መጽሐፍ ቅዱስ የደኅንነትን እቅድ በጣም ግልጽ ያደረገው። በኢየሱስ ክርስቶስ እመን ትድናለህ (ዮሐንስ 3፡16፤ ሐዋርያት ሥራ 16፡31)። ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን ታምናለህን፣ እሱም የኃጢአትህን ቅጣት ሊከፍል (ሮሜ 5፡8፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)? ለደኅንነትህ እሱን ብቻ ታምናለህን? መልስህ አዎን ከሆነ፣ ድነሃል! ዋስትና ማለት “ከሁሉም ጥርጣሬ ነጻ መሆን ማለት ነው።” የእግዚአብሔርን ቃል ከልብ በመቀበል፣ “ከሁሉም ጥርጣሬ ነጻ” መሆን ትችላለህ፣ ይህም የዘላለማዊ ደኅንነትህ ሐቅና እውነታ ነው።
ኢየሱስ ራሱ ይሄንን አጽንቶታል፣ በእሱ የሚያምኑትን በተመለከተ፡ “እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም” (ዮሐንስ 10፡28-29)። የዘላለም ሕይወት፣ ዘላለማዊ ነው። ማንም ቢሆን፣ ራሳችሁም ጭምር ከእግዚአብሔር በክርስቶስ የተሰጣችሁን የደኅንነት ጸጋ ከእናንተ መውስድ አይችልም።
የእግዚአብሔርን ቃል በልባችን ሸሽገን እናስቀምጣለን፣ በእሱ ላይ ኃጢአት እንዳንሠራ (መዝሙር 119፡11)፣ ይህም የጥርጥር ኃጢአትን ይጨምራል። የእግዚአብሔር ቃል ለእናንተ በሚለው ተደሰቱ፣ ይህም ከመጠራጠር ይልቅ በመተማመን መኖር እንችላለን! ከክርስቶስ ከራሱ ቃል ዋስትና ሊኖረን ይችላል፣ መዳናችን አጠያያቂ እንዳልሆነ። ዋስትናችን የተመሠረተው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ባለው በእግዚአብሔር ፍቅር ነው።
English
የደኅንነቴ ዋስትና እንዴት ሊኖረኝ ይችላል?