ጥያቄ፤
የእግዚአብሔር ባህሪያት ምንድን ናቸው ? እግዚአብሔር ምን ይመስላል ?
መልስ፤
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ስንሞክር መልካሙ ዜና ስለ እግዚአብሔር የሚታወቅ ብዙ ነገር አለ ! ይህንን መግለጫ የሚመረምሩ ሰዎች መጀመሪያ ጹሑፉን በሙሉ ማንበብ ይረዳቸዋል ። የበለጠ ማብራሪያ ለማግኘት ተመልሰው የተመረጡ ጥቅሶችን መመልከት ይኖርባቸዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ማጣቀሻዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው። ካለ መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን የቃላቶች ጥርቅም የሰው ሐሳብ ከመሆኑ አያልፉም ። ይህ ደግሞ በራሱ እግዚአብሔርን ለመረዳት መልካም መንገድ አይደለም (ኢዮብ 42 ፡ 7) ። እግዚአብሔር ምን ይመስላል ብለን መመራመር ነገሩን ማቅለል ነው ። ጉዳዩን ችላ ማለት ከእግዚአብሔር ሐሳብ ውጪ ሐሰተኛ ጣኦታትን እንድንቀርፅ ፣ እንድንከተልና እንድናመልክ ሊያደርገን ይችላል (ዘፀአት 20 ፡ 3-5) ።
እግዚአብሔር ስለራሱ እንዲታወቅ የፈለገው ብቻ ተገልጦ ይታያል ። የእግዚአብሔር አንዱ ባሕርይ ወይም መለያ “ብርሃን” ነው ትርጉሙም ራሱን የሚመለከት ጉዳይ ራሱ ይገልጠዋል (ኢሳያስ 60 ፡ 19, ያዕቆብ 1 ፡ 17) እግዚአብሔር ለራሱ የገለጠው እውነታ መዘንጋት የለበትም። አለበለዚያ አንዳችን ወደ እርሱ ዕረፍት ከመግባት እንዳንሰናከል (ዕብ 4፡1)ፍጥረት ፣ መጽሐፍ ቅዱስና ሥጋ የሆነው ቃሉ (ኢየሱስክርስቶስ) እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ግንዛቤ እንድንጨብጥ ይረዳናል።
እግዚአብሔር ፈጣሪያችን ነው እኛም የፍጥረቱ አንድ አካል ነን ከሚለው ግንዛቤ እንነሳ ። (ዘፍጥረት 1፡1, መዝሙር 24 ፡ 1) ።
ሰው በእርሱ መልክ እንደተፈጠረ እግዚአብሔር ተናግሯል ። ሰው ከሌሎች ፍጥረታት በላይ ከመሆኑም ባሻገር እንዲገዛቸውም ሥልጣን ተሰጥቶታል ። (ዘፍጥረት 1፡26 – 28)። ፍጥረት “በውድቀት” ብዙ ጎድሏል ነገር ግን የሥራውን ምሥል በጥቂቱም ቢሆን ያንፀባርቃል።(ዘፀአት3 ፡17–18,ሮሜ 1፡19–20)። የፍጥረትን ግዙፍነት ፣ ውጥንቅጥነት፣ ውበትና ስርዓት በመገንዘብ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ምን ሊመስል እንደሚችል እንረዳለን ። እግዚአብሔርን ለማወቅ በምናደርገው ፍለጋ አንዳንድ የእግዚአብሔርን መጠሪያዎች ማንበብ በእጅጉ ሊረዳን ይችላል ።
ኤሎሒም- ኃይለኛ ቅዱስ (ዘፍጥረት 1 ፡ 1)
አዶናይ -ጌታ የአዛዥና የታዛዥ ግንኙነት ያመለክታል (ዘፀአት 4 ፡ 10, 13)
ኤል ኤሊኦን- እጅግ የተከበረው ብርቱ የሆነ (ዘፀአት 14 ፡ 20)
ኤል ሮይ- ኃይለኛና የሚመለከት (ዘፀአት 16 ፡ 13)
ኤል ሻዳይ- ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር (ዘፀአት 17 ፡ 1)
ኤል ኦላም- የዘለአለም እግዚአብሔር (ኢሳያስ 40 ፡ 28)
ያህዌ- “ጌታ እኔ ነኝ” ትርጉሙ ዘላለማዊ በራሱ የሚኖር እግዚአብሔር (ዘፀአት 3 ፡ 13,14)
አሁን ደግሞ የእግዚአብሔር ባህሪያት መመርመር እንቀጥላለን። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው ማለትም ጅማሬ የለውም። ለህልውናውም ፍጻሜ የለውም ለዘላለም ነዋሪ ነው ፍጻሜ የለውም። (ዘዳግም 33 ፡ 27, መዝሙር 90 ፡2,1ኛ ጢሞ 1፡ 17)። እግዚአብሔር አይቀየርም እርሱ አይለወጥም ማለትም እግዚአብሔር አስተማማኝና ሊታመኑበት የሚገባ ነው። (ሚልክያስ 3 ፡ 6 ,ዘኁልቁ 23 ፡ 19,መዝሙር 102 ፡ 26,27)
እግዚአብሔር ተወዳዳሪ የለውም ማለትም በፍጥረቱ ወይም በሥራው እርሱን የሚመስለው የለውም። እርሱ ተወዳዳሪ የለውም ፍፁም ነው። (2ኛ ሳሙኤል 7፡22, መዝሙር 86 ፡8, ኢሳያስ 40 ፡ 25, ማቴዎስ 5 ፡ 48) እግዚአብሔር ሊመረመር አይችልም ማለትም ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ በምርምር ሊደረስበት አዳጋች ነው። (ኢሳያስ 40 ፡ 28, መዝሙር 145 ፡ 3, ሮሜ 11 ፡ 33 , 34) እግዚአብሔር ሐቀኛ ነው ሰው አይቶ አያዳላም። (ዘዳግም 32፡ 4, መዝሙር 18 ፡ 30) እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለትም ሁሉን ያሸንፋል ። ደስ ያለውን ያደርጋል። ድርጊቶቹ ግን ሁልጊዜ ከሌላው ጠባዩ ጋር አምሳያነት አላቸው። (ራዕይ 19፡ 6, ኤርሚያስ 32፡ 17- 27) እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ አለ ማለትም የትም ይገኛል። ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር ሁሉም ነገር ነው ማለት አይደለም። (መዝሙር 139 ፡ 7 – 13, ኤርሚያስ 23 ፡ 23) እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፣ ይህም ሲባል ያለፈውን የአሁኑንና የወደፊቱን ያውቃል። በሆነ ጊዜ የምናስበውን ያውቃል። ሁሉንም ነገር ስለሚያውቅ ፍርዱን ያለማዳላት ይፈፀማል። (ምሳሌ139፡1–5,ምሳሌ5፡21) እግዚአብሔር አንድ ነው ማለትም እርሱ ብቻውን ነው። በልባችን ውስጥ ያለውን ጥልቅ ፍላጐት እርሱ ብቻውን ነው ማሟላት የሚችለውና አምልኮአችንና መሰጠታችንን ሊቀበል የሚገባው እሱ ብቻ ነው። (ዘዳግም6፡4) እግዚአብሔር ጻድቅ ነው ይህም ሲባል ጥፋታችንን አይቶ አያልፍም ማለት ነው። የኛ ኃጢያት በእርሱ ላይ እንደ ተጫነ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ፍርድ መለማመድ ነበረበት። በእርሱም ጽድቅና ፍትህ ምክንያት የኃጢያት ይቅርታ አግኝተናል። (ዘፀአት 9፡27, ማቴዎስ 27፡45–46, ሮሜ 3 ፡ 2-26)
እግዚአብሔር ሉአላዊ ነው ማለትም የሁሉ የበላይ ነው። ፍጥረታት ሁሉ በአንድ ላይ ተዳምረው አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የእርሱን ዓላማ ሊያደናቅፉት አይችሉም። (መዝሙር 93፡1,95፡3, ኤርሚያስ 23፡20) የእግዚአብሔር መንፈስ ነው ማለትም በዓይን ሊታይ አይችልም ። (ዮሐንስ 1 ፡ 18,4 ፡24) እግዚአብሔር ሥላሴ ነው ማለትም ሦስት በአንድ ነው በይዘት በስልጣንና በክብር ተመሳሳይ ነው ። አንድ ልታስታውሰው የሚገባ ነገር በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው ጥቅስ ውስጥ “ስም” የሚለው ቃል ነጠላ ነው ምንም እንኳን ለሦስት የተለያዩ አካላት “ ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ” የሚያመላክት ቢሆንም (ማቴዎስ 28 ፡ 19, ማርቆስ 1 ፡ 9–11) እግዚአብሔር እውነት ነው ከራሱ ማንነት ጋር ይስማማል ፍፁም አይደለልም ሊዋሽም አይችልም (ምሳሌ 117 ፡ 2, 1ኛ ሳሙኤል 13፡29)
እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ከሁሉም የሞራል ዝቅጠት የተለየና ፍፁም የሚጠላው ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ክፋት ያያል ይህም ያስቆጣዋል። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ እሳት በቅድስና ጐን ሲጠቀስ ይታያል። እግዚአብሔር እንደሚባላ እሳት ተደርጐ ይጠቀሳል። (ኢሳያስ 6 ፡ 3, ዕንባቆም 1 ፡ 13, ዘፀአት 3 ፡2,4,5, ዕብራውያን 12 ፡ 29)
እግዚአብሔር መሐሪ ነው። ይህም መልካምነቱን ደግነቱን ምህረቱንና ፍቅሩን ያጠቃልላል። እነዚህ ቃላት ለመልካምነቱ ትርጉም የሚፈነጥቁ ናቸው። የእግዚአብሔር ፀጋ ባይኖር ኖሮ ሌሎቹ የእርሱ ባሕርያት ከእርሱ ይነጥሉን ነበር። ምስጋና ለእርሱ ይሁን ይህ አልሆነብንም። ምክንያቱም እርሱ እያንዳንዳችንን በግል ሊያውቀን ይፈልጋል። (ዘፀአት 34 ፡ 6, መዝሙር 31፡19 1ኛ, ጴጥሮስ 1 ፡ 3, ዮሐንስ 3 ፡ 16, ዮሐንስ 17፡3)።
ይህ የእግዚአብሔር አከል የሆነን ጥያቄ ለመመለስ የተደረገ መለስተኛ ሙከራ ነው። እባክህን እርሱን ለማወቅ እንድትጥር እናበረታታሐለን (ኤርምያስ 29 ፡ 13)።
English
የእግዚአብሔር ባህሪያት ምንድን ናቸው ? እግዚአብሔር ምን ይመስላል ?