ጥያቄ፤
እግዚአብሔር ለምን ክፉ ነገሮች በመልካም ሰዎች ላይ እንዲደርስ ይፈቅዳልን?
መልስ፤
ይህ ከሥነ-መለኮት ጥያቄዎች ሁሉ አንደኛው በጣም አስቸጋሪው ነው። እግዚአብሔር ዘላለማዊ፣ ወሰን የሌለው፣ ሁሉንም የሚያውቅ፣ በሁሉም ስፍራ የሚገኝ፣ እና ሁሉን አድራጊ ነው። እንዴት አድርገው የሰው ልጆች (ዘላለማዊ ያልሆኑ፣ የተወሰኑ፣ ሁሉን የማያውቁ፣ በሁሉም ስፍራ መገኘት የማይችሉ፣ ወይም ሁሉን ማድረግ የማይችሉ) የእግዚአብሔርን መንገዶች በሞላ እንረዳለን ብለው ይጠብቃሉ? መጽሐፈ ኢዮብ ስለዚህ የሚለው አለ። እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ ከመግደል በቀር ሁሉንም ነገር እንዲያደርግ ለሰይጣን ፈቀደለት። የኢዮብ ምላሽ ምንድን ነበር? “ቢገድለኝም እንኳ እሱን ተስፋ አደርጋለሁ” (ኢዮብ 13፡15)። “እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን” (ኢዮብ 1፡21)። ኢዮብ፣ እግዚአብሔር እነዚህ ሁሉ ነገሮች እንዲደርሱበት ለምን እንደፈቀደ አልገባውም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር መልካም መሆኑን አውቋል፤ ስለሆነም እሱን በማመን ቀጠለ። ልክ እንደዛው፣ የእኛም ምላሽ እንደዚያ ሊሆን ይገባል።
መጥፎ ነገሮች በመልካም ሰዎች ላይ ለምን ይደርሳሉ? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሹ “መልካም” ሰዎች የሉም የሚል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተብራራ መልኩ ግልጽ ያደረገው ሁላችንም በኃጢአት የተከበብንና የተበከልን መሆናችንን ነው (መክብብ 7፡20፤ ሮሜ 6፡23፤ 1ኛ ዮሐንስ 1፡8)። ሮሜ 3፡10-18 ግልጽ ያልሆነበት ስለ “መልካም” ሰዎች አለመኖር ነው፡ “ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም። ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤ አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፤እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፥ የሰላምንም መንገድ አያውቁም። በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።” እያንዳንዱ የሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ ያለው በዚች ቅጽበት ወደ ገሃነም መጣል በተገባው። እያንዳንዷን ሴከንድ በሕይወት መቆየት የቻልነው በእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት ነው። በዚህ ምድር ላይ የምናልፍበት የመጨረሻው ክፉ መከራ እንኳ ቢሆን፣ ከሚገባን ጋር ሲተያይ በምሕረት የተሞላ ነው፣ ከዘላለማዊ ገሃነም ከእሳት ባሕር አኳያ።
የተሻለ ጥያቄ የሚሆነው “እግዚአብሔር መልካም ነገሮች ለመጥፎ ሰዎች እንዲደርስ ለምን ይፈቅዳል?” የሚለው ነው። ሮሜ 5፡8 እንደሚገልጸው፣ “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።” ክፉ፣ ኩነኔኛ፣ ኃጢአተኛ የዚህ ዓለም ሰዎች ተፈጥሮ እንኳ ቢሆነንም እግዚአብሔር ይወደናል። እሱ በእጅጉን ይወደናል የኃጢአታችን ቅጣት የሆነውን ለመሸከም እስከ ሞት ድረስ (ሮሜ 6፡23)። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝ ብንቀበል (ዮሐንስ 3፡16፤ ሮሜ 10፡9)፣ ኃጢአታችን ይቅር ሊባልና በሰማይ ያለ የዘላለም ቤት ተስፋ ተደርጎልናል (ሮሜ 8፡1)። የሚገባን ገሃነም ሆኖ ሳለ። የተሰጠን ግን የዘላለም ሕይወት በሰማይ ያለ ነው፣ ወደ ኢየሱስ በእምነት ከመጣን።
እርግጥ አንዳንዴ ክፉ ነገሮች የማይገባቸው ለሚመስሉ ሰዎች ሊደርስ ይችላል። ነገር ግን፣ እግዚአብሔር በራሱ ምክንያት ነገሮች እንዲደርሱ ሊፈቅድ ይችላል፣ ብናስተውለውም ሆነ ባናስተውለው። ከሁሉም በላይ፣ ሆኖም፣ እግዚአብሔር መልካም፣ ትክክል፣ አፍቃሪ፣ እና መሐሪ መሆኑን የግድ ማስታወስ አለብን። ዘወትር የሚደርሱብንን ነገሮች በቀላሉ ያማናስተውላቸው ናቸው። ሆኖም፣ የእግዚአብሔርን መልካምነት ከመጠራጠር ይልቅ፣ ምላሻችን እሱን ማመን መሆን አለበት። “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል” (ምሳሌ 3፡5-6)።
English
እግዚአብሔር ለምን ክፉ ነገሮች በመልካም ሰዎች ላይ እንዲደርስ ይፈቅዳልን?