settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሊባል የሚችለው፣ የሚከናወነው ሥራ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ አማኙን ከክርስቶስ ጋር ወደሚኖር ኅብረትና ከሌሎች አማኞች ጋር ወደ አለ ኅብረት በክርስቶስ ሥጋ በኩል፣ በዳነበት ቅጽበት የሚሆን ነው። አንደኛ ቆሮንቶስ 12፡12-13 የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን በተመለከተ ማዕከላዊ አንቀጽ ነው፡ “አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል” (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13)። ሮሜ 6፡1-4 ደግሞ በአንጻሩ የእግዚአብሔርን መንፈስ ለይቶ አይጠቅስም፣ እሱ የሚገልጸው የአማኙን አቋም በእግዚአብሔር ፊት ያለውን፣ በአንደኛ ቆሮንቶስ አንቀጽ ባለው ተመሳሳይ ቋንቋ ነው፡ “እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።”

የሚከተሉት ሐቆች ስለ መንፈስ ጥምቀት ያለንን መረዳት ተጨባጭ ለማድረግ ይረዱናል፡ አንደኛ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 በግልጽ እንደሚያስቀምጠው ሁሉም ተጠምቀዋል፣ ሁሉም መንፈስን እንዲጠጡ እንደተሰጣቸው ሁሉ (የመንፈስ ማደሪያ መሆን)። ሁለተኛ፣ በቃሉ በየትኛውም ስፍራ አማኞች በመንፈስ እንዲጠመቁ አልተነገራቸውም፣ ወይም በምንም መልኩ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት እንዲፈልጉ አልተገለጸም። ይህ የሚያመለክተው ሁሉም አማኞች ይሄን ተግባር እንዳከናወኑት ነው። ሦስተኛ፣ ኤፌሶን 4፡5 የመንፈስ ጥምቀትን የሚያመላክት ይመስላል። ጉዳዩ ይህ ከሆነ፣ የመንፈስ ጥምቀት በሁሉም አማኝ ላይ ያለ ነው፣ ልክ እንደ “አንድ እምነት” እና “አንድ አባት” እንደ ሆነ።

በማጠቃለያም፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሁለት ነገሮችን ያደርጋል፣ 1) እሱ ከክርስቶስ አካል ጋር ያገናኘናል፣ እንዲሁም 2) ከክርስቶስ ጋር አብረን መሰቀላችንን እውን ያደርገዋል። በእሱ አካል ላይ መሆን ማለት ለአዲስ ሕይወት ከእሱ ጋር ተነሥተናል ማለት ነው (ሮሜ 6፡4)። እናም እኛ መንፈሳዊ ስጦታችንን በተግባር ልንለማመደው ይገባል፣ ያ አካል በትክክል እንዲሠራ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 በተቀመጠው መሠረት። የአንድ መንፈስ ጥምቀትን ማድረግ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ ያገለግላል፣ እንደ ኤፌሶን 4፡5 ሐሳብ። ከክርስቶስ ሞት፣ መቀበር፣ እና ትንሣኤ ጋር በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መተባበር፣ ካደረብን የኃጢአት ኃይል መለየትን ያደርጋል፣ እናም በታደሰ ሕይወት እንድንራመድ (ሮሜ 6፡1-10፤ ቆላስይስ 2፡12)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries