settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ጥምቀት ለመዳን አስፈላጊ ነውን? ጥምቀታዊ ዳግም ልደት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


ጥምቀታዊ ዳግም ልደት አንድ ሰው ለመዳን የግድ መጠመቅ አለበት የሚል እምነት ነው። ይህም የክርክራችን ነጥብ ነው፣ ማለትም ጥምቀት ለክርስቲያን ታዛዥነት ጠቃሚ ደረጃ ነው፣ ነገር ግን በጽናት የማንቀበለው ጥምቀት ለደኅንነት አስፈላጊ ነው የሚለውን ነው። እኛ በጽናት የምናምነው እያንዳንዱ እና ሁሉም ክርስቲያን በመነከር የውኃ ጥምቀትን ማድረግ እንዳለበት ነው። ጥምቀት የአማኙን ከክርስቶስ ጋር መሞት፣ መቀበር፣ እና መነሣት ጋር ያለውን እውቅና ያሳያል። ሮሜ 6፡3-4 ይገልጻል፣ “ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።” ውኃ ውስጥ የመነከሩ ድርጊት የሚያመለክተው ከክርስቶስ ጋር ሞቶ መቀበርን ነው። ከውኃ ውስጥ መውጣትም የክርስቶስን ትንሣኤ ያሳያል።

በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው እምነት ለደኅንነት ማንኛውንም ተጨማሪ መስፈርት ማድረግ በሥራ ላይ የተመሠረተ ድኅነት/መዳን ነው። በወንጌል ላይ ማንኛውንም ነገር መጨመር፣ የኢየሱስን የመስቀል ላይ ሞት የእኛን መዳን ለመግዛት በቂ አይደለም ማለት ነው። ለመዳን ስንል የግድ መጠመቅ አለብን ማለት፣ የገዛ ራሳችንን መልካም ሥራና ታዛዥነት በክርስቶስ ሞት ላይ የግድ መጨመር አለብን ማለት ነው፣ ለደኅንነታችን በቂ እናደርገው ዘንድ። የኢየሱስ ሞት ብቻውን ነው ለኃጢአታችን የተከፈለው (ሮሜ 5፡8፤ 2 ቆሮንቶስ 5፡21)። ኢየሱስ ለኃጢአታችን የከፈለው ዋጋ ከእኛ “ተጠያቂነት” ጋር ይስማማል፣ በእምነት ብቻ (ዮሐንስ 3:16፤ ሐዋ. 16:31፤ ኤፌሶን 2:8-9)። ስለዚህ፣ ጥምቀት ከመዳን በኋላ ጠቃሚ የሆነ የመታዘዝ ደረጃ ነው፣ ነገር ግን ለደኅንነት መስፈርት ሊሆን አይችልም።

ርግጥ ነው፣ ጥምቀት ለመዳን አስፈላጊ የሆነ መስፈርት መሆኑን የሚጠቁሙ አንዳንድ ጥቅሶች አሉ። ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚነግረን ደኅንነትን የምንቀበለው በእምነት ብቻ ነው (ዮሐንስ 3:16፤ ኤፌሶን 2:8-9፤ ቲቶ 3:5)፣ ለእነዚህ ቁጥሮች የተለየ ትርጉም ሊኖራቸው ይገባል። ቅዱስ ቃሉ ከቅዱስ ቃሉ ጋር አይቃረንም። በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜያት አንድ ሰው ከአንድ ሃይማኖት ወደ ሌላው ሲቀየር ዘወትር ይጠመቃል፣ መለወጡን ለማስታወቅ። ጥምቀት በይፋ ውሳኔ ማድረግን ማስታወቂያ መንገድ ነው። ለመጠመቅ እምቢ የሚሉ በርግጠኝነት አለማመናቸውን እየገለጹ ነው። ስለዚህ፣ በሐዋርያትና በጥንት ደቀ መዛሙርት አስተሳሰብ ያልተጠመቀ አማኝ የሚለው ሐሳብ ለመስማት ያልቻለውን ነው። አንድ ሰው በክርስቶስ ማመኑን ሲገልጽ፣ እምነቱን በይፋ ለማወጅ ያፍር ነበር፣ ይኸም እውነተኛ እምነት እንደሌለው ያመለክት ነበር።

ጥምቀት ለደኅንነት አስፈላጊ ከሆነ፣ እንግዲያውስ ጳውሎስ ለምን እንዲህ ይላል፣ “በስሜ እንደ ተጠመቃችሁ ማንም እንዳይል ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ከእናንተ አንድን እንኳ ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” (1 ቆሮንቶስ 1፡14)? ለምንስ እንዲህ ይላል፣ “ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝምና፥ ወንጌልን ልሰብክ እንጂ፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም” (1 ቆሮንቶስ 1፡17)? በዚህ ምንባብ መሠረት ጳውሎስ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የተነሣውን የከፋ መከፋፈል ይሞግታል። ሆኖም፣ ጳውሎስ እንዴት እንደዚህ ሊሆን ይችላል፣ “ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ…” ወይም “ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝምና…” ጥምቀት ለደኅንነት አስፈላጊ ከሆነ? ጥምቀት ለደኅንነት አስፈላጊ ከሆነ ጳውሎስ ሊል ይችል የነበረው፣ “ስላልዳናችሁ አመሰግናለሁ…” እና “ክርስቶስ እኔን ለማዳን አልላከኝምና…” ያም ለጳውሎስ እምነት የሌለበት አስቂኝ መግለጫ በሆነው ነበር። በተጨማሪም፣ ጳውሎስ ወንጌልን ግምት ውስጥ ያስገባ ዝርዝር የፍሬ ሐሳብ ማመላከቻ በሚሰጥበት ጊዜ (1 ቆሮንቶስ 15፡1-8)፣ እንዴት ስለ ጥምቀት ሳያነሣ ችላ ይላል? ጥምቀት ለመዳን መስፈርት ከሆነ፣ እንዴት አንደኛውም የወንጌል ክፍል ጥምቀትን ሳያነሣ ይቀራል?

ጥምቀታዊ ዳግም ልደት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽንሰ-ሐሳብ አይደለም። ጥምቀት ከኃጢአት ሊያድን አይችልም፣ ለክፉ ሕሊና እንጂ። 1 ጴጥሮስ 3፡21 ላይ፣ ጴጥሮስ በግልጽ እንዳስተማረው ጥምቀት ሥጋዊ አካልን ለማንጻት የሚደረግ ትዕይንታዊ ድርጊት አይደለም፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት መልካም ሕሊና እንዲኖረን የሚያደርገን አግባብ እንጂ። ጥምቀት ክርስቶስን እንደ አዳኝ ለሚያምነው በአንዱ ልብና ሕይወት ውስጥ ቀድሞ ለተከሰተው ተምሳሌት ነው። (ሮሜ 6:3-5፤ ገላትያ 3:27፤ ቆላስያስ 2:12)። ጥምቀት አስፈላጊ የሆነ የመታዘዝ ደረጃ ነው፣ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሊወስደው የሚገባ። ጥምቀት ለደኅንነት መስፈርት ሊሆን አይችልም። እሱን እንዲህ ማድረጉ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ብቁነት ላይ ጥቃት እንደ መሰንዘር ይቆጠራል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ጥምቀት ለመዳን አስፈላጊ ነውን? ጥምቀታዊ ዳግም ልደት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries