settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ከጋብቻ በፊት መኖር ያለበት ተገቢ የሆነ የቅርበት ደረጃ ምንድነው?

መልስ፤


ኤፌሶን 5፡3 ይነግረናል፣ “ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ።” ማንኛውም ነገር፣ ለዝሙት “ፍንጭ” እንኳ ቢሆን ለክርስቲያን ተገቢ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ የትኞቹ ነገሮች “ፍንጭ” እንደሆኑ ዝርዝሩን አይነግረንም፣ ወይም የትኛውን አካላዊ እንቅስቃሴ ከጋብቻ በፊት ጥንዶቹ ማድረግ እንደሚችሉ አይገልጽም። ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ ጉዳዩን ባይገልጽም፣ እግዚአብሔር “ከጋብቻ በፊት የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነትን” ተቀብሎታል ማለት አይደለም። አንዱን ለግብረ-ሥጋ ግንኙነት ዝግጁ ለማድረግ የፍቅር ጨዋታ ማሳያ ይታቀዳል። ከሎጂክ አኳያ ከዚያም፣ የፍቅር ጨዋታ ለተጋቡ ጥንዶች ክልከላ አለ። ማንኛውም የፍቅር ጨዋታ መሰል ድርጊት እስከ ጋብቻ ድረስ መከልከል ይኖርበታል።

አንዳች አጠራጣሪ ነገር ካለ፣ ላልተጋቡ ጥንዶች ተገቢ መሆን አለመሆኑ ያልለየ ድርጊት፣ መወገድ ይኖርበታል (ሮሜ 14፡23)። ማናቸውምና ሁሉም ተራክቧዊ እና ቅድመ-ተራክቧዊ ድርጊቶች ለተጋቡ ጥንዶች ክልክል ናቸው። ያልተጋቡ ጥንዶች ለተራክቦ የሚፈትናቸውን ማናቸውንም ድርጊት ማስወገድ ይኖርባቸዋል፣ ያም የዝሙት ገጽታ የሚያሰጥ፣ ወይም ቅድመ-የፍቅር ጨዋታ ተደርጎ የሚወሰድ። ብዙ ፓስተሮችና የክርስቲያን አማካሪዎች በጥብቅ ይመክራሉ፣ ጥንዶች እጅ ለእጅ ከመያያዝ፣ እጅን ትከሻ ላይ ከመጣል፣ እና ከቀላል ስሞሽ ባለፈ እንዳይራመዱ፣ ከጋብቻ በፊት። የተጋቡ ጥንዶች በእጅጉ እርስ በርሳቸው ለብቻቸው ከተካፈሉ፣ ያ ትዳር ልዩና የተለየ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ይኖረዋል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ከጋብቻ በፊት መኖር ያለበት ተገቢ የሆነ የቅርበት ደረጃ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries