ጥያቄ፤
ሁለት ወይም ሦስት ክፍሎች አሉን? ሥጋ፣ ነፍስ፣ እና መንፈስ ነን - ወይስ - ሥጋ፣ ነፍስ-መንፈስ?
መልስ፤
ዘፍጥረት 1፡26-27 ሰብዓዊነትን ከሌሎቹ ፍጥረታት ሁሉ የሚለየውን ነገር ያመለክታል። የሰው ልጆች፣ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ዓላማ ተደርጓል፣ እናም እንዲህ፣ እግዚአብሔር ከቁሳዊና ቁሳዊ ካልሆኑ ክፍሎች ነው የፈጠረን። ቁሳዊው በግልጽ እንደሚታየው ተጨባጩ ነው፡ ሥጋዊ አካል፣ አጥንቶች፣ የሰውነት ብልቶች፣ ወዘተ፣ እናም ግለሰቡ በሕይወት እስካለ ድረስ ይኖራሉ። ቁሳዊ ያልሆኑት ገጽታዎች ተጨባጭ ያልሆኑት ናቸው፡ ነፍስ፣ መንፈስ፣ ማሰብ፣ ፍቃድ፣ ሕሊና፣ ወዘተ. እነዚህ ከግለሰቡ ሥጋዊ የሕይወት ጣሪያ በላይ የሚኖሩ ናቸው።
የሰው ልጆች ሁሉ ሁለቱንም ቁሳዊ እና ቁሳዊ ያልሆኑ ባሕርያት አሏቸው። ሁሉም የሰው ልጅ አካል እንዳለው ግልጽ ነው፣ ሥጋ፣ ደም፣ አጥንት፣ ብልቶች፣ እና ሕዋሳት አሉት። ሆኖም፣ ተጨባጭ ያልሆኑት የሰው ልጅ ነገሮች ናቸው ዘወትር የሚያከራክሩት። ቅዱስ ቃሉ ስለእነዚህ ምን ይላል? ዘፍጥረት 2፡7 እንደሚያመለክተው ሰው የተፈጠረው እንደ ሕያው ነፍስ ነበር። ዘኍልቁ 16፡22 እግዚአብሔርን የሚሰይመው እንደ “የመናፍስት አምላክ” ነው፣ እነርሱም በሁሉም የሰው ልጆች ዘንድ ያሉ። ምሳሌ 4፡23 እንደሚነግረን፣ “ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፣ የሕይወት ምንጭ እሱ ነውና፣” የሚያመለክተውም ልብ የሰው ፍቃድ እና ስሜቶች ማዕከል መሆኑን ነው። ሐዋ. 23፡1 እንደሚለው፣ “ጳውሎስም ሸንጎውን ትኩር ብሎ ተመልክቶ፣ ‘ወንድሞቼ ሆይ፣ እኔ እስከዚች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኖሬአለሁ’ አለ።” ጳውሎስ እዚህ የሚጠቅሰው ሕሊናን ነው፣ እሱም የአእምሮ ክፍል ሲሆን ትክክሉንና ስሕተቱን ይገልጽልናል። ሮሜ 12፡2 ይገልጻል፣ “በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” እነዚህ ቁጥሮች፣ እና ሌሎች ብዙዎች፣ የሚያመለክቱት የሰውን ቁሳዊ ያልሆነ የተለያየ ገጽታ ነው። ሁላችንም ቁሳዊ እና ቁሳዊ ያልሆኑ ይዘቶችን እንካፈላለን።
ስለዚህ፣ ቅዱስ ቃሉ ከነፍስ እና ከመንፈስ በላይ የሚዘረዝረው አለ። በአንዳንድ መልኩም፣ ነፍስ፣ መንፈስ፣ ልብ፣ ሕሊና፣ እና አእምሮ ይያያዛሉ፣ ውስጣዊ ግንኙነትም አላቸው። ሆኖም፣ ነፍስ እና መንፈስ በርግጥ ተቀዳሚ የሰው ቁሳዊ ያልሆኑ ገጽታዎች ናቸው። የሌላው ገጽታዎች ተመሳሳይ ይዘት አላቸው። ይሄንን በበሐሳብ ስንይዝ፣ ሰውነት ባለ ሁለት ምድብ ነውን (ለሁለት የሚከፈል፣ ሥጋ/ነፍስ-መንፈስ)፣ ወይስ ባለ ሦስት ምድብ (ለሦስት የሚከፈል፣ ሥጋ/ነፍስ/መንፈስ)። ቀኖናዊ መሆን አይቻልም። ለሁለቱም አተያዮች መልካም ሙግቶች አሉ። ቁልፉ ቁጥር ዕብራውያን 4፡12 ነው፡ “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፣ የሚሠራም። ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነውና፣ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፤ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል” ይህ ቁጥር ስለዚህ ክርክር ቢያንስ ሁለት ነገሮችን ይነግረናል። ነፍስና መንፈስ ሊለያዩ ይችላሉ፣ የነፍስና የመንፈስ ልዩነት እግዚአብሔር ብቻ ሊያውቀው የሚችል ነገር ነው። በርግጠኝነት ልናውቅ በማንችለው ነገር ላይ ከምናተኩር ይልቅ፣ በፈጣሪ ላይ ማተኮሩ ይሻላል፣ “ግሩምና ድንቅ አድርጎ የፈጠረንን” (መዝሙር 139፡14)።
English
ሁለት ወይም ሦስት ክፍሎች አሉን? ሥጋ፣ ነፍስ፣ እና መንፈስ ነን - ወይስ - ሥጋ፣ ነፍስ-መንፈስ?