settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የእግዚአብሔር ልጅ?

መልስ፤


የእግዚአብሔር ልጅ መሆን በክርስቶሰ ኢየሱስ ማመንን ይጠይቃል፡፡ ‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ››(ዮሐ 1፡12)

ዳግም መወለድ አለብህ
ኢየሱስ ነቆዲሞስን በገኘው ጊዜ ወዲያውኑ የአዘለአለምን ህይወት ማግኘት እንደሚችል አላረጋገጠለትም፡፡ ይልቁንም የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን፡ (ዮሐ 3፡3) ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።››

አንድ ሰው በመጀመሪያ ሲወለድ አዳም በኤደን ገነት ያልታዘዘበትን ኃጢያተኛ መንነት ይወርሳል፡፡ አንድን ህጻን ኃጠያትን ማድረግን ማንም ሊነግረው አያስፈልገውም፡፡ በተፈጥሮወ የተሳሳተውን ከፉውን ፍላጎት ይከተላል ወደ ወሸት ማታለል እና ጥላቻ፡፡ የእግዚአብሔር የእግዚአብሔር ልጅ ከመሆን ይልቅ ያለመታዘዝና የቁጣ ልጅ ይሆናል (ኤፌ 2፡1-3)፡፡

እንደ ቁጣ ልጅ ከእግዚአብሔር ተለይተን በሲኦል መጣል ይገባናል፡፡ መልካም የሆነወ ነገር ኤፌ 2፡3-5 እንዲህ ይላል ‹‹ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥›› እንዴት ነው ከክርስቶስ ጋር ህይዋን በመሆን /ዳግም በመወለድ/ የእግዚአብሔር ልጆች የምንሆነው? ኢየሱስን በእምነት መቀበል አለብን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀበል
‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤›› (ዮሐ 1፡12) ይህ ክፍል በግልጽ እንዴት የእግዚአብሔር ልጆች መሆን አንደምንችል ይናገራል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንሱን መቀበል፡፡ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምንድን ነው ማመን ያለብን ?

አንደኛ ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ማመን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከድንግል የተወለደ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳምን ኃጢያት አልወረሰም፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ ሁለተኛው አዳም ተብሎአል (1ቆሮ 15፡22)፡፡ የአዳም አለመታዘዝ ኃጢያትን ወደ አለም ሲያመጣ የኢየሱስ ክርስቶ ፍጹም የሆነው መታዘዝ መረከትን አመጣ፡፡ የእኛ ምላሽ ንስሐ መግባት (ከኃጢያት መመለስ) በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ይቅርታ መፈለግ ነው፡፡

ሁለተኛ የእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ አዳኝነት ያምናል፡፡ የእግዚአብሔር እቅድ ፍጹም የሆነው ልጁ እኛ ልንቀበለው የሚገባንን ቅጣትን እንዲቀበል ነበር፤ ሞት፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ከኃጢያት ቅጣት እና ኃይል እንዲያድናቸው የተቀበሉትን ነጻ ያደርጋቸዋል፡፡ የእርሱ ትንሳኤ ያጸድቀናል (ሮሜ 4፡25)

በመጨረሻ የእግዚአብሔር ልጆች ኢየሱስን የህይወታቸው ጌታ አድርገው ይከተሉታል፡፡ ኢየሱስ ኃጢያትንና ሞትን ድል ካደረገ በኋላ እግዚአብሔር ሥልጣንን ሁሉ ሰጠው (ኤፌ 1፡20-23)፡፡ ኢየሱስ የተቀበሉትን ሁሉ ይመራቸዋል ያልተቀበሉትን ሁሉ ደግም ይፈርድባቸዋል፡፡ (ሥራ 10፡42)፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ ለአዲስ ህይወት እንደ እግዚአብሔር ልጆች ዳግም ተወልደናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን የተቀበሉ ብቻ እንዲሁ ስለሱ የሚያውቁ ሳይሆን ስለ ድኅነት የሚቀበሉት የሚያምኑበት ጌታ አድርገው የሚቀበሉት እና ትልቁ ኃብታቸው አድርገው የሚወዱት እነሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ መሆን
በመጀመሪያ ስንወለድ ለመወለዳችን ምንም አይነት አስተዋእጾ እንደሌለን እንዲሁ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እንድንወለድ ለማድረግ በመልካም ስራ ወይንም የራሳችንን እምነት መፍጠር አንችልም፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን ስልጣን እንደ ጸጋው ፈቃድ የሚሰጥ ይህንን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔሰረ ነው፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።››1(ዮሐ 3፡1)፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች የሚኮሩበት ምንም ነገር የላቸውም ትምክህቱ በእግዚአብሔር ነው (ኤፌ 2፡8-9)፡፡

ልጆች ወላጆቻውን በመምሰል ያድጋሉ፡፡ በተመሳሳይ እግዚአብሔርም ልጆቹ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመስሉ ይፈልጋል፡፡ ሆኖም ፍጹም መሆን ያለው በሰማይ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ያለመመለስ በኃጢያት አይኖሩም፡፡ ‹‹ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።›› (1ኛ ዮሐ 3፡7-10)

ስህተትን አለመስራት፤ የእግዚአብሔር ልጆች ኃጢያት ሊያደርጉ መቻላቸውን አይክዱም፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ክርስቶስን ከመከተል ይልቅ ያለማቋረጥ በማድረግ በኃጢያት የሚደሰት ከሆነ ቃሉ የሚነግረን ይህ ሰው ዳግም አልተወለደም፡፡ ኢየሱስ ስለእነዚህ አይነት ሰዎች ነግሮና፤ ‹‹እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ።›› (ዮሐ 8፡44) የእግዚአብሔር ለጆች በሌላው መልኩ የኃጢያትን ፍላጎት በመከተል አይኖሩም ነገር ግን አባታቸውን የበለጠ ለማወቅ በመፈለግ በፍቅር ይኖራሉ፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ትርፍ ሊለካ የማይችል ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ልጆች እኛ የእርሱ ቤተሰብ ነን (ቤተክርስቲያን)፤ በሰማይ ቤት እንዳለን ተስፋ የተገባልን ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ትክክለኛ መብት የተሰጠን (ኤፌ 2:19? 1 ጴጥ 1:3–6? ሮሜ 8:15). ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ መስጠት ከኃጢያት መመለስ እና በክርስቶስ ማመን ዛሬም የእግዚአብሔር ልጆች ያደርጋል፡፡

English


ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
የእግዚአብሔር ልጅ?
© Copyright Got Questions Ministries