settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ቤተ-ክርስቲያን መገኘት ለምን ይጠቅማል?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ-ክርስቲያን መገኘት እንደሚኖርብን ይነግረናል፣ ከሌሎች አማኞች ጋር እግዚአብሔርን ማምለክ እንድንችልና ለመንፈሳዊ እድገታችን ቃሉን መማር እንድንችል (ሐዋርያት ሥራ 2፡42፤ ዕብራውያን 10፡25)። ቤተ-ክርስቲያን አማኞች እርስ በርሳቸው የሚፋቀሩበት ስፍራ ነው (1 ዮሐንስ 4፡12)፣ እርስ በርሳቸው የሚበረታቱበት (ዕብራውያን 3፡13)፣ እርስ በርስ የ“ሚነሳሡበት” (ዕብራውያን 10፡24)፣ እርስ በርሳቸው የሚያገለግሉበት (ገላትያ 5፡13)፣ እርስ በርሳቸው የሚገሠጹበት (ሮሜ 15፡14)፣ እርስ በርሳቸው የሚከባበሩበት (ሮሜ 12፡10)፣ እርስ በርሳቸውም በደግነትና በኀዘኔታ የሚመላለሱበት ነው (ኤፌሶን 4፡32)።

አንድ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን ለደኅንነት ሲያምን፣ እሱ ወይም እሷ የክርስቶስ አካል ብልት ይሆናሉ (1 ቆሮንቶስ 12:27)። የቤተ-ክርስቲያን አካል ባግባቡ አንዲሠራ ሁሉም የእሱ “አካል ብልቶች” መገኘት ይኖርባቸዋል (1 ቆሮንቶስ 12:14-20)። ልክ እንደዚያው፣ አንድ አማኝ ወደ ሙሉ መንፈሳዊ ብስለት ፈጽሞ ሊደርስ አይችልም፣ ካለ ሌሎች አማኞች ድጋፍና ማበረታቻ (1 ቆሮንቶስ 12:21-26)። በዚህ ምክንያት፣ ቤተ-ክርስቲያን መገኘት፣ መሳተፍ፣ እና ኅብረት በአማኝ ሕይወት ላይ መደበኛ ገጽታ ሊሆን ይገባል። ሳምንታዊ ቤተ-ክርስቲያን መገኘት ለአማኞች ትርጉም ያለው “አስፈላጊ” ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን የክርስቶስ የሆነ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣ ቃሉን ለመቀበል፣ እና ከሌሎች ጋር ኅብረት ለማድረግ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ቤተ-ክርስቲያን መገኘት ለምን ይጠቅማል?
© Copyright Got Questions Ministries