ጥያቄ፤
በስህተት አስተምህሮ በኑፋቄ ውስጥ ያለን ሰው እንዴት በወንጌል መድረስ ይቻላል?
መልስ፤
በኑፋቄ በስህተት ሃይማኖት ውስጥ ላሉ ልናደርግ የምንችለው ዋና ነገር ለእነርሱ መጸለይ ነው፡፡ እግዘአብሔር ለእውነት ልባቸውን እንዲከፍት እንዲለውጣቸው ልንጸልይ ያስፈልጋል፡፡ (2 ቆሮ 4:4). እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚገኘው ደኅነት እንደሚያስፈልጋቸው በልባቸው እንዲያምኑ ልንጸልይ ያሰፈልጋል(ዮሐ 3:16) ፡፡ ከእግዚአብሔር ኃይል እና መንፈስ ቅዱስም ከሚሰጠው መረዳት ውጪ ማንንም እውነቱን ለማሳመን ሊሳካልን አይችልም፡፡ (ዮሐ 16:7-11).
እንዲሁም በስህተት ኃይማኖት በኑፋቄ የታሰሩ ሰዎች እግዚአብሔር በህይወታችን ያደረገውን ለውጥ እንዲያዩ እግዚአብሔርን የመምሰል የክርስትና ህይወት መኖር አለብን (1 ጴጥ 3:1-2)፡፡ ስለ ጥበብ እንዴት በአስደናቂ ኃይል ልናገለግላቸው እንደምንችል ልንጸልይ ያስፈልጋል(ያዕ 1:5) ፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ወንጌልን በምናካፍልበት ጊዜ በድፍረት ሊሆን ይገባል፡፡ የድኅነትን መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ ማወጅ አለብን፡፡(ሮሜ 10:9-10). እምነታችንን ለማሳወቅ ሁል ጊዜም የተዘጋጀን መሆን አለብን (1 ጴጥ 3:15) ግን በጨዋነትና በአክብሮት ማድረግ አለብን፡፡ አስተመህሮአችንን በትክክል ልናስተላልፍ የቃላቱን ጦርነት ልናሸንፍ እነችላለን ግን በቁጣችንና የበላይ ለመሆን በላን ፍላጎት ላይሳካ ይችላል፡፡
በመጨረሻ የመሰከርንላቸውን ሰዎች ድኅነት ለእግዚአብሔር ልንተውለት ይገባል፡፡ የእኛ ጥረት ሳይሆን የእግዚአባሔር ኃይልና ጸጋ ነው ሰዎችን የሚያድነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ብርቱ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀት እና ስለ ሐሰተኛ አስተምሮ ማወቅ መልካምና ጥበብም ነው፤ እነዚህ ነገሮች በኑፋቄና በስህተት አስተምሮ ለተተበተበው መለወጥ ወጤት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ልናደርግላቸው የምንችለው ትልቁ ነገር መጸለይ መመስከር እና በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን ህይወት በፊታቸው መኖር፤ መንፈስ ቅዱስ እነርሱን የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ እንደሚያስረዳቸው እና እንደሚለውጣቸው መታመን ነው፡፡
English
በስህተት አስተምህሮ በኑፋቄ ውስጥ ያለን ሰው እንዴት በወንጌል መድረስ ይቻላል?