ጥያቄ፤
መጽሐፍ ቅሱስ ስለ ሐዋሪያቱ ሞት ይናገራል? ሐዋሪያት እንዴት ሞቱ?
መልስ፤
በመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሞቱ የተጠቀሰው የሐዋሪያው ያዕቆብ ሞት ብቻ ነው ሥራ 12፡2 ንጉስ ሃሮድስ ‹‹ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።›› አንገቱን ተቀልቶ ይመስላል፡፡ የሌሎቹ ሐዋሪያት የሞት ሁኔታ ከቤተክርስትያን ባህል ጋር የተያያዘ ስለሆነ በሌሎች መረጃዎች ላይ ብዙ እምነት መጣል የለብንም፡፡ የሐዋሪያትን ሞት በተመለከተ በአብዛኛው በልምድ እንደሚያምነው ሐዋሪያው ጴጥሮስ በተዘቀዘቀ መስቀል በሮም ኢየሱስ እንደተናገረው ትንቢት ፍጻሜ ሞቶአል (ዮሐ 21፡18)፡፡ የሌሎቹን ሐዋሪያት ሞት በሚመለከት በተለምዶ የሚታመነው ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡
ማቲዎስ በሰማዕትነት መከራን ተቀብሎ በኢትዮጵያ በሰይፍ ተወግቶ ሞተ፡፡ የሐንስ በሮም ስደት በሰማዕትነት በፈላ ዘይት ውስጥ ተቀቅሎ መከራን ተቀበለ፡፡ በተአምር ከሞት የዳነ ቢሆንም፤ በፍጥሞ ደሴት ታስሮ እንዲጣል ተፈረደበት፡፡ በፍጥሞ ደሴት ሆኖ የዮሐንስ ራዕይን ጻፈ፡፡ ከዚያ በኋላ ከእስር ተፈቶ አሁን ቱርክ ወደ ሚባለው ስፍራ ተመለሰ፡፡ አርጅቶ ሞተ በቸኛው በሰላም የሞተ ሐዋሪያ ነው፡፡
ያዕቆብ የኢየሱስ ወንድም (በትክክል ሐዋሪያ ባይሆንም) በኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መሪ ነበር፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት አልክድም በማለቱ መቶ ጫማ ርዝመት ካለው በደቡብ ምስራቅ ከነበረ የመቅደስ ከፍታ ተወርውሮአል፡፡ ከተወረወረበት እንደተረፈ ባወቁ ጊዜ እስኪሞት ድረስ ጠላቶቹ በቡድን ደብድበው ገደሉት፡፡ ይህ ሃሳብ በፈተናው ወቅት ሰይጣን ወስዶት እንደነበረው ከፍታ አይነት ነው፡፡
በርተለሚዮስ በሌላው መታወቂያው ናትናኤል በእስያ ሚሽነሪ ነበር፡፡ ዛሬ ቱርክ በምትባለው ቦታ በመስበኩ በአርሜኒያ እስኪሞት ድረስ ገረፉት፡፡ እንድሪያስ በግሪክ የኤክስ ቅርጽ ባለው መስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ በሰባት ወታደሮች ከተገረፈ በኋላ ስቃዩን ለባብዛት በመስቀል ላይ በገመድ አሰሩት፡፡ ይከተሉት የነበሩ ሰዎች እንደሚመሰክሩት እንድሪያስ እንደዚህ በማለት ሰላምታን ይሰጥ ነበር፡ ‹‹ እኔ ትልቅ ናፍቆት ነበረኝ እናም ይህን አስደሳች ጊዜ ስናፍቀው ነበር፤ መስቀለም በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ተቀደሶ ነበር›› ለሚያስሩት ሰዎች እስከ ሚሞት ድረስ ለሁለት ቀን ይሰብክ ነበር፡፡ ሐዋሪያው ቶማስ በ… በህንድ ቤተክርስቲያን በመትከል ጉዞዎቹ ላይ በጩቤ ተወጋ፡፡ ሐዋሪያው ማቲያስ የይሁዳን አስቆሮቱን የተካው በድንጋይ ተወግሮ …፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ በጨቃኙ ኔሮ በ67 ዓ.ም አንገቱ ተቀልቶ ሞተ፡፡ ስለሌሎቹም ሐዋሪያት በልምድ የሚባል ነገር ቢኖርም ምንም አይነት የሚታመን ታሪክም ልማዳዊ መረጃም የላቸውም፡፡
የሐዋሪያቱ ሞት ዋና ነገር አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ሁሉም ለእምነታቸው ለመሞት መፈለጋቸው ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ያልተነሳ በሆን ደቀመዛሙርቱ ያወቁ ነበር፡፡ ሰዎች ውሸት መሆኑን ቢያውቁ ለውሸት ለመሞት አይፈቅዱም ነበር፡፡ እውነታው ደቀመዛሙርት አሰቃቃውን ሞት ለመቀበል የፈቀዱት በክርስቶስ ባላቸው እምነት ወደ ኋላ አለማለታቸው ሊኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ አስደናቂ ምስክርነት ነው፡፡
English
መጽሐፍ ቅሱስ ስለ ሐዋሪያቱ ሞት ይናገራል? ሐዋሪያት እንዴት ሞቱ? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?