settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሞት ቅጣት ምን ይላል?

መልስ፤


በሉይ ኪዳን የሞት ለተለያዩ ምግባሮች ቅጣት ያዛል፤ ለነፍስ ግድያ (ዘጽ 21:12), አፈና (ዘጽ 21:16), ከእንስሳ ጋር የሚረክስ (ዘጸ 22:19), ምንዝርና (ዘሌ 20:10), ግብረ ሰዶማዊነት (ዘኁ 20:13), ሐሰተኛ ነብይ (ዘዳ 13:5), ሴተኛ አዳሪነት እና አስገድዶ መደፈር (ዘዳ 22:4), እና በሌሎች ብዙ ጥፋቶች፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ የሞት ፍርድ ሲፈረድ ምህረትን ያደርጋል፡፡ ዳዊት ሰው ገድሎ ዝሙት ፈጽሞል እግዚአብሔር ግን ህይወቱ እንዲነጠቅ አላደረገም ነበር፡፡ (2 ሳሙ 11:1-5, 14-17; 2 ሳሙ 12:13)፡፡ በአጠቃላይ የኃጢያት ዋጋው ሞት ስለሆነ ባደርግነው ኃጢያት ሁላችንም በሞት ቅጣት ውስጥ መሆን ነበረብን (ሮሜ 6:23). ምስጋና ይድረሰው እግዚአብሔር እኛ እዳንኮነን ፍቅሩን ገልጾልናል (ሮሜ 5:8).

ሌላው ፈሪሳዊያን ስታመነዝር የተያዘችውን ሴት ወደ ኢየሱስ አምጥተው በድንጋይ እንድትወገር ጠየቁት ኢየሱስም ሲመልስ ‹‹ ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።›› ዮሐ 8:7). ይህ ደግሞ ኢየሱስ ሁል ጊዜ የሞት ፍርድን ይቃወማል ተብሎ መወሰድ የለበትም፡፡ ኢየሱስ የፈሪሳዊያንን ግብዝነት እያጋለጠው ነበር፡፡ ፈሪሳዊያን ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን ህግ ይጥስ እንደሆን ብለው ይፈታተኑት ነበር፤ እነርሱ በትክክል ሴቲቱ እንድትወገር ፈልገው ብቻ አልነበረም (በምንዝርና የተያዘው ወንድስ የት ነበር?) የሞት ቅጣት ያዘዘው እግዚአብሔር ራሱ ነው፡‹‹የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።›› (ዘፍ 9:6). ኢየሱስም የሞት ቅጣት ፍርድን ሊደግፍ እንደሚችል በአንዳንድ ምሳሌዎች እንመለከታለን፡፡ ኢየሱስም የሞት ፍርድ በታወጀበት ጸጋውን ገልጾአል (ዮሐ 8:1-11). ጳውሎስ የሞት ፍርድ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ለማወጅ የመንግስት መኖር አስፈላጊ መሆኑን ለመንግስት ኃይል እውቅና ሰጥቶአል (ሮሜ 13:1-7).

የሞትን ቅጣት ክርስቲያኖች እንዴት ነው ማየት ያለባቸው? በመጀመሪያ ማስታወስ ያለብን የሞት ፍርድ ቅጣት በቃሉ ላይ ያስቀመጠው እግዚአብሔር ነው እንግዲያውስ እኛ የተሻለውን መለኪያ ማስቀመጥ አግባብነት የለለውም፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር የተሻለ መለኪያ አለው፤ እርሱ ፍጹም ነው፡፡ ይህ መለኪያው ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለእርሱም ነው፡፡ እንግዲያውስ እርሱ ሲወድ ያለገደብ ነው እና የማይለካ ገደብ የሌለው ምህረት አለው፡፡ እንዲሁም ገደብ የሌለው ቁጣ እንዳለውም እናያለን አና ሁለም የሚሄደው በተስተካከለ ሚዛን ነው፡፡

ሁለተኛ እግዚኣብሔር ለመንግስታት የሞት ፍርድ በሚሆንበት ጊዜ እንዲወስኑ ሥልጣን ሰጥቶአቸዋል፡፡(ዘፍ 9፡6፤ ሮሜ 13፡1-7)፡፡ በሁሉም ጉዳዩች ላይ አግዚአብሔር የሞት ፍርድ ውሳኔ እንዳይደረግ ይቃወማል ብሎ ማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ ክርስቲያኖች በምንም አይነት ሁኔታ የሞት ፍርድ ቢተላለፍ ደስተኞች መሆን የለለባቸውም፤ ግነ በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቲያኖች እጅግ በጣም ከፍተኛ ሆኑ ወንጀሎች ይህን ለመተግበር ለመንግስታት የተሰጣቸውን መብት መቃወም የለባቸውም፡፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሞት ቅጣት ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries