settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?

መልስ፤


ኢየሱስ ለይቶ ስለራሱ ከተናገራቸው በተጨማሪ የእርሱ ደቀ-መዛሙርቶችም የኢየሱስን አምላክነት አረጋግጠዋል፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርግ የሚችለውን ነገር፤በኃጥአት የተቆጣ እምላክ እንደመሆኑ መጠን፤ ኃጥአቶችን ይቅር የማለት መብት እንደነበረው ያን ተናግረዋል፡፡ (የሐዋሪያት ሥራ 5፤31፤ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፤13፤መዝሙረ ዳዊት 130፤4፤ትንቢተ ኤርምያስ 31፤34) ከዚህ ከመጨረሻው ንግግር ጋር በቅርበት ተያይዞ በተጨማሪ ኢየሱስ “በሕያዋንና በሙታንም የሚፈርድ” ነው ብሏል፡፡ (2ኛ ጢሞቴዎስ 4፤1) ቶማስ “ጌታዬ እና አምላኬ!” ብሎ በኢየሱስ ላይ አለቀሰ፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 20፤28) ጳውሎስ ኢየሱስን “ታላቅ አምላክ እና አዳኝ” ብሎ ይጠራዋል (ወደ ቲቶ 2፤13) እና ኢየሱስ የራሱን ሥጋ ከመልበሱ በፊት “በአግዚአብሔር መልክ” እንደነበር ያን ያመለክታል፡፡(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፤5-8) እግዚአብሔር አብ ኢየሱስን በተመለከተ “ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል።”ይላል፡፡ (ወደ ዕብራውያን ሰዎች 1፤8) ዮሐንስ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም (ኢየሱስ) እግዚአብሔር እንደነበር።” ያን ይጠቅሳል፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 1፤1) የክርስቶስን አምላክነት የሚያስተምሩ ቅዱሳት መጽሐፍት ብዙ ናቸው (የዮሐንስ ራዕይ 1፤17፤2፤8፤22፤13፤1ኛ ቆሮንቶስ 10፤4፤1ኛ ጴጥሮስ 2፤6-8፤መዝሙረ ዳዊት 18፤2፤95፤1፤1ኛጴጥሮስ 5፤4፤ወደ ዕብራውያን ሰዎች 13፤20) ነገር ግን እንዲያውም ከእነዚህ አንዱ ክርስቶስ በተከታዮቹ አምላክ ተደርጎ እንደተቆጠረ ለማሳየት በቂ ነው፡፡

በተጨማሪ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለያህዌ (መደበኛው የእግዚአብሔር ስም) ብቻ የሆኑት ማዕረጎች ተሰጥቶታል፡፡ የብሉይ ኪዳን ማዕረግ “ነጻ አውጪ” (መዝሙረ ዳዊት 130፤7፤ትንቢተ ሆሴዕ 13፤14) በአዲስ ኪዳን ውስጥ (ወደ ቲቶ 2፤13፤የዮሐንስ ራዕይ 5፤9) ለኢየሱስ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል 1 ውስጥ አማኑኤል ተብሏል “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር፡፡” በትንቢተ ዘካሪያስ 12፤10 ውስጥ “ወደ እኔ ወደ ወጉት ይመለከታሉ” ይህን የሚለው ያህዌ ነው፡፡ ነገር ግን አዲስ ኪዳን ይህንን ለኢየሱስ ስቅለት ያደርገዋል፡፡(የዮሐንስ ወንጌል 19፤37፤የዮሐንስ ራዕይ 1፤7) የተወጋው እና የታየው ያህዌ ከሆነ የተወጋው እና የታየው ኢየሱስ ከሆነ ስለዚህ ኢየሱስ ያህዌ ነው፡፡ ጳውሎስ ኢየሱስን በሚያመለክት መልኩ ትንቢተ ኢሳያስ 45፤22-23ን በፊልጵስዩስ 2፤10-11 ውስጥ ይተረጉማል፡፡ በተጨማሪ የኢየሱስ ስም ጸሎት ውስጥ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ጥቅም ላይ ውሏል፤ “ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።” (ወደ ገላቲያ ሰዎች 1፤3፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፤2) ክርስቶስ አምላክ ካልነበረ ይህ ሹፌት ይሆናል፡፡ የኢየሱስ ስም ኢየሱስ ለማጥመቅ ባዘዘው ትዕዛዝ ውስጥ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ቀርቧል “በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም (በነጠላው)፡፡” (የማቴዎስ ወንጌል 28፤19፤ በተጨማሪ 2ኛ ቆሮንቶስ 13፤4ንም ተመልከት)

በእግዚአብሔር ብቻ ሊደረጉ የሚችሉ ድርጊቶች ምስጋናው ለኢየሱስ ሆኗል፡፡ ኢየሱስ ሙታንን ብቻ አላስነሳም (የዮሐንስ ወንጌል 5፤21፤11፤38-44) ኃጥአቶችንም ይቅር ብሏል (የሐዋሪያት ሥራ 5፤31፤13፤38) ፤ዓለማትን ፈጥሯል ፤ደግፎታልም፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 1፤2፤ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፤16-17) ይህ እንዲያውም እግዚአብሔር ፤በፍጥረት ጊዜ ብቻውን ነበር፤ ያለውን አንድ ሰው በሚመለከትበት ጊዜ ግልጽ ይሆናል፡፡ (ትንቢተ ኢሳያስ 44፤24) በተጨማሪ ክርስቶስ አምላክ ብቻ ሊኖረው የሚችለውን ባህሪያት አለው፤ዘላለማዊነት (የዮሐንስ ወንጌል 5፤21)፤በሁሉም ሥፍራ የመገኘት (የማቴዎስ ወንጌል 18፤20፤28፤20)፤ሁሉን አዋቂነት (የማቴዎስ ወንጌል 16፤21)፤እና ልዕለ ኃያልነት (የዮሐንስ ወንጌል 11፤38-44)

አሁን እግዚአብሔርን ለመሆን መጠየቅ ወይም እሱን ማመን እውነት ነው ብሎ አንድን ሰው ማሞኘት አንድ ነገር ነው እና ሌላ አንድ ነገር በአጠቃላይ ያ እንደሆነ ለማረጋገጥ፡፡ ክርስቶስ ለእሱ አምላክነት ማረጋገጫ ብዙ ድንቆችን ሰጥቷል፡፡ እንዲያው ጥቂቶቹ የኢየሱስ ድንቆች የሚያጠቃልሉት ውሃን ወደ ወይን መለወጥ (የዮሐንስ ወንጌል 2፤7)፤ በውሃ ላይ መራመድ (የማቴዎስ ወንጌል 14፤25)፤የሚታዩ ነገሮችን ማባዛት (የዮሐንስ ወንጌል 6፤11)፤ዕውሩን ማብራት (የዮሐንስ ወንጌል 9፤7)፤አንካሳውን (የማርቆስ ወንጌል 2፤3) እና የታመመውን (የማቴዎስ ወንጌል 9፤35፤የማርቆስ ወንጌል 1፤40-42) እና እንዲያውም የሞቱትን ሰዎች ማስነሳት (የዮሐንስ ወንጌል 11፤43-44፤የሉቃስ ወንጌል 7፤11-15፤የማርቆስ ወንጌል 5፤35)፡፡ ከዚያም በላይ ክርስቶስ ራሱ ከሞት ተነስቷል፡፡ መሞት እና መነሳት ከሚባለው ከአረማውያን ጣኦታት አፈ-ታሪክ ጥናት በተለየ ትንሳኤን የሚመስል አንዳች ነገር በሌሎች ሃይማኖቶች በጥብቅ ጥያቄ ያነሳ የለም፤ ያን ያህል የበዛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማረጋገጫ ያለው ሌላ የለም፡፡

ስለ ኢየሱስ ክርስቲያን ያልሆኑት ዋነኛ ምሁራን እንኳን የሚቀበሏቸው ቢያንስ 12 ያህል ታሪካዊ እውነታዎች አሉ፡፡

1. ኢየሱስ በመሰቀል ሞቷል፡፡
2. ተቀብሮም ነበር፡፡
3. ሞቱ ደቀ-መዛሙርቶች እንዲፈሩ እና ተስፋን እንዲያጡ አድርጓቸው ነበር፡፡
4. ከጥቂት ቀናት በኃላ የኢየሱስ መቃብር ባዶውን ተገኝቷል (ወይም እንደተገኘ ተነግሯል)
5. ደቀ-መዛሙርቶች የተነሳውን የኢየሱስን ማንነቶች እንዳዩ አምነዋል፡፡
6. ከዚህ በኃላ ደቀ-መዛሙርቶች ከተጠራጣሪነት ወደ ደፋር አማኞች ተለወጡ፡፡
7. ይህ መልዕክት በጥንቷ ቤተክርስቲያን የስብከት አንኳር ነበር፡፡
8. ይህ መልዕክት በኢየሩሳሌም ተሰብኳል፡፡
9. በዚህ ስብከት ምክንያት ቤተክርስቲያን ተወለደች እናም አደገችም፡፡
10. እንደ መጀመሪያ ቀን አምልኮ የትንሳኤ ቀን ፤እሁድ፤ ሰንበትን (ቅዳሜን) ተክቷል፡፡
11. በተጨማሪ ተጠራጣሪው ያዕቆብም የተነሳውን ኢየሱስን እንዳየው ባመነ ጊዜ ተለውጧል፡፡
12. ጳውሎስ ፤የክርስትናው ጠላት፤ የተነሳው የኢየሱስ መልክ እንደሆነ ባመነበት ልምምድ ተለውጧል፡፡

ምንም እንኳን አንድ ሰው ይህን ውስን ዝርዝር መቃወም ከነበረበት ትንሳኤውን ለማረጋገጥ እና ወንጌልን (የኢየሱስን ሞት፤መቀበር፤መነሳት እና መልክ) ለመጀመር ጥቂቶች ብቻ ይፈለጋሉ፡፡(1ኛ ቆሮንቶስ 15፤1-5) ከላይ ያሉትን አንድ ወይም ሁለት እውነታዎችን ለማብራራት ምናልባት የተወሰኑ ጽንሰ-ሳቦች ቢኖሩም፤እነሱን በሙሉ ትንሳኤ ብቻ ሊገልጻቸው እና ምክንያት ሊሆናቸው ይችላል፡፡ ደቀ-መዛሙርቶች የተነሳውን ኢየሱስን አይተነዋል ማለታቸውን ትችቶች ያን ይቀበላሉ፡፡ ትንሳኤ እንዳደረገው ውሸቶችም ቢሆኑ ቅዥቶች ሰዎችን መለወጥ አይችሉም፡፡ በመጀመሪያ ማትረፍ ይገባቸው የነበረው ነገር ምንድነው? ክርስትና ብዙም አይታወቅም ነበር እናም በእርግጠኝነት ምንም ገንዘብ አያስገኝላቸውም ነበር፡፡ ሁለት ውሸታሞች ጥሩ ሰማዕታት አይሆኑም፡፡ የደቀ-መዛሙርቶች ለእምነታቸው አሰቃቂ ሞትን የመሞት ፈቃደኝነት ትንሳኤ ይልቅ የተሻለ ሌላ ማብራሪያ የለም፡፡ አዎ፤ ብዙ ሰዎች እውነት ነው ብለው ላሰቡት ውሸቶች ይሞታሉ፤ነገር ግን ውሸት እንደሆነ ለሚያውቁት ነገር ሰዎች አይሞቱም፡፡

በአጠቃላይ ክርስቶስ ያህዌ እንደነበር ተናግሮ ነበር ያም እሱ አምላክ ነበር (እንዲያውም “ጣኦት” አይደለም ነገር ግን አንድ እውነተኛ አምላክ) ተከታዮቹ (በጣኦት ምክንያት ሊጨነቁ ይገባቸው የነበሩ አይሁዶች) አመኑት እናም እንደ አምላክም ጠቀሱት፡፡ ክርስቶስ አምላክነቱን በድንቃ ድንቆች፤ ዓለምን በሚለውጥ ትንሳኤን ጨምሮ በኩል አረጋግጧል፡፡ እነዚህን እውነታዎች ማብራራት የሚችል ሌላ ምንም መላ-ምት የለም፡፡ አዎ፤የክርስቶስ አምላክነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries