ጥያቄ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አጋንንት ምን ይላል?
መልስ፤
ራዕይ 12፡9 ስለ አጋንንት ማንነት ግልጽ የሆነ ቅዱስ ቃል ነው፣ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።” የሰይጣን ከሰማይ ወደ ምድር መውደቅ በተምሳሌትነት ኢሳይያስ 14:12-15 እና ሕዝቅኤል 28:12-15 ላይ ተገልጧል። ራዕይ 12:4 የሚያመለክት የሚመስለው ሰይጣን ኃጢአት ሲሠራ አንድ ሦስተኛውን መላእክት ከእሱ ጋር መውሰዱን ነው። ይሁዳ 6 ኃጢአት የሠሩትን መላእክት ጠቅሷል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አጋንንት የወደቁ መላእክት መሆናቸውን ይጠቁማል፣ ከሰይጣን ጋር ሆነው በእግዚአብሔር ላይ ያመጹ።
ሰይጣንና የሱው አጋንንት አሁን ለማጥፋትና ለማሳት እየሠሩ ነው፣ እግዚአብሔርን የሚከተሉትንና የሚያመልኩትን ሁሉ (1 ጴጥሮስ 5:8፤ 2 ቆሮንቶስ 11:14-15)። አጋንንት እንደ ክፉ መናፍስት ነው የሚገለጹት (ማቴዎስ 10፡1)፣ ርኵሳን መናፍስት (ማርቆስ 1፡27)፣ እና የሰይጣን መላእክት (ራዕይ 12፡9)። ሰይጣንና አጋንንቱ ዓለምን ያስታሉ (2 ቆሮንቶስ 4፡4)፣ ክርስቲያኖችን ያጠቃሉ (2 ቆሮንቶስ 12፡7፤ 1 ጴጥሮስ 5፡8)፣ እና ቅዱሳን መላእክትን ይዋጋሉ (ራዕይ 12፡4-9)። አጋንንት መንፈሳዊ ሕላዌ ናቸው፣ ነገር ግን በሥጋዊ አካል ሊከሰቱ ይችላሉ (2 ቆሮንቶስ 11፡14-15)። አጋንንት/ የወደቁ መላእክት የእግዚአብሔር ጠላት ናቸው፣ ነገር ግን የተሸነፉ ጠላቶች ናቸው። ከእኛ ጋር ያለው ይበልጣል፣ በዓለም ካሉት ይልቅ (1 ዮሐንስ 4፡4)።
English
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አጋንንት ምን ይላል?