settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በሰው ነፍስና መንፈስ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

መልስ፤


ነፍስና መንፈስ ሁለቱ ቀዳሚ ቁሳዊ ያልሆኑ የሰው ገጽታዎች ናቸው፣ ቅዱስ ቃሉ የሚገልጻቸው። በሁለቱ መካከል ያለውን ግልጽ ልዩነት ለመረዳት መሞከር ግራ የሚያጋባ ይሆናል። “መንፈስ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰውን ቁሳዊ ያልሆነ ገጽታ ብቻ ነው። የሰው ልጆች መንፈስ አላቸው፣ ግን እኛ መንፈስ አይደለንም። ሆኖም፣ በቅዱስ ቃሉ፣ አማኞች ብቻ ናቸው መንፈሳዊ ሕይወት ያላቸው (1 ቆሮንቶስ 2፡11፤ ዕብራውያን 4፡12፤ ያዕቆብ 2፡26)፣ የማያምኑ ግን በመንፈስ የሞቱ ናቸው (ኤፌሶን 2፡1-5፤ ቆላስያስ 2፡13)። በጳውሎስ ጽሑፎች መንፈሳዊው ለአማኝ ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ነው (1) ቆሮንቶስ 2:14; 3:1; ኤፌሶን 1:3; 5:19; ቆላስያስ 1:9; 3:16)። መንፈስ በሰው ውስጥ ያለ ነገር ሲሆን፣ እሱም ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ወዳጅነት እንዲኖረን የሚያደርግ ነው። መቼም ጊዜ “መንፈስ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ሲውል፣ የሚጠቅሰው ቁሳዊ ያልሆነውን የስብዕና ክፍል ነው፣ እሱም ከእግዚአብሔር ጋር “ይገናኛል”፣ እሱ ራሱ መንፈስ የሆነ (ዮሐንስ 4:24)።

“ነፍስ” የሚለው ቃል ሊያመለክት የሚችለው ሁለቱንም ቁሳዊ ያልሆኑትንና ቁሳዊ የሆኑትን የሰው ገጽታ ነው። የሰው ልጆች መንፈስ እንዳላቸው፣ የሰው ልጆች ነፍሶች ናቸው። እጅግ መሠረታዊ በሆነ መልኩ፣ “ነፍስ” የሚለው ቃል “ሕይወት” ማለት ነው። ሆኖም፣ ከዚህ ዋነኛ ትርጉም ባሻገር መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነፍስ በብዙ ዐውደ-ጽሑፎች ላይ ይናገራል። ከእነዚህ አንዱ የሰው ልጅ ለኃጢአት ያለው ጉጉት ነው (ሉቃስ 12፡26)። ሰውነት በተፈጥሮው ክፉ ነው፣ ከዚህ የተነሣም ነፍሶቻችን ተበላሽተዋል። የነፍስ ሕይወት-መርሖ በሥጋዊ ሞት ጊዜ ይወገዳል (ዘፍጥረት 35፡18፤ ኤርምያስ 15፡2)። ነፍስ እንደ መንፈስ የበርካታ መንፈሳዊ እና ስሜታዊ ልምምዶች ማዕከል ነው (ኢዮብ 30፡25፤ መዝሙር 43፡5፤ ኤርምያስ 13፡17)። “ነፍስ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ በዋለ ጊዜ ሁሉ፣ እሱ ሊወክል የሚችለው ሁለንተናዊውን ሰው ነው፣ በሕይወትም ሆነ ከሕይወት ወዲያ።

ነፍስና መንፈስ የተያያዙ ናቸው፣ ግን ሊለያዩ የሚችሉ (ዕብራውያን 4፡12)። ነፍስ የሰው ሕላዌ ዓይነተኛ ነገር ነው፤ እሱ ማንነታችን ነው። መንፈስ የሰው ገጽታ ነው ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በሰው ነፍስና መንፈስ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries