settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዳይኖሰሮች ምን ይላል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዳይኖሰሮች አሉ?

መልስ፤


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዳይኖሰሮች ርዕስ ፤ ተገቢው የዘፍጥረት ትርጓሜ፤ እና በዙሪያችን የምናገኛቸውን ቁሳዊ ማስረጃዎችን እንዴት እንደምንተረጉማቸው፤ በምድር ዕድሜ ሁሉ በክርስቲያኑ ማህበረሰብ መሐከል በክርክር ላይ ያለ አንድ ትልቅ ክፍል ነው፡፡ እነዚያ ምድር ረጅም ዕድሜ እንዳላት የሚያምኑ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ዳይኖሰሮችን እንደማይጠቅስ ወደ መስማማቱ ያዘነብላሉ፤ ምክንያቱም በእነርሱ ምሳሌ መሠረት ዳይኖሰሮች የመጀመሪያው ሰው ምድር ላይ ከረገጠበት ከሚሊዮኖች ዓመታት በፊት ሞተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች በህይወት ያሉ ዳይኖሰሮች ማየት አልቻሉም፡፡

ምድር ጥቂት ዕድሜ እንዳላት የሚያምኑ ሰዎች ምንም እንኳን ፈጽሞ “ዳይኖሰር” የሚለውን ቃል በትክክለኛው ባይጠቀምም መጽሐፍ ቅዱስ ዳይኖሰሮችን እንደሚጠቅስ ወደ መስማማቱ ያዘነብላሉ፡፡ በምትኩ በእኛ የእንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱሶች ጥቂት በተለዩ መንገዶች የተተረጎመ የዕብራይስጥ ቃል የሆነውን “ታኒን” የሚለውን ይጠቀማል፡፡ አንዳንድ ጊዜ “የባህር አካል” ነው፤እና አንዳንድ ጊዜ “እጅግ ትልቅ እባብ” ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ “ድራጎን” ተብሎ ተተርጓሟል፡፡ ታኒን አንድ በጣም ትልቅ አጥቢ እንስሳ እንደሆነ ይቀርባል፡፡ እነዚህ ፍጥረታት በብሉይ ኪዳን በግምት ከሰላሳ ጊዜያት በላይ ተጠቅሰዋል እናም በየብስ እና በውሃ አካል ውስጥ ይገኙም ነበር፡፡

እነዚህን በጣም ትልቅ የሆኑትን አጥቢ እንስሳቶችን ከመጥቀሱ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰኑ ፍጥረታትን ይገልጻል፤ በዚያ መልኩም የተወሰኑ ምሁራን ጸሐፊዎች ምናልባት ዳይኖሰሮችን በመግለጽ ላይ እንደሆኑ ያምኑ ይሆናል፡፡ ቤሄሞዝ የሚባለው እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ትልቁ እንደሆነም ተነግሯል፤እጅግ ግዙፍ የሆነ ጅራቱ ልክ እንደ አኻያ ዛፍ የሆነ ነው (መጽሐፈ ኢዮብ 40፤15)፡፡ አንዳንድ ምሁራን ቤሄሞዝን ከዝሆን ወይም ከጉማሬ ጋርም ለማመሳሰል ሞክረዋል፡፡ ሌሎች ዝሆኖች እና ጉማሬዎች ከአኻያ ዛፍ ጋር በምንም የማይወዳደሩ በጣም ቀጫጭን ጅራቶች እንዳሏቸው ጠቁመዋል፡፡ ዳይኖሰሮች ልክ እንደ ብራክዎሰርስ እና ዳይፕሎኮኮስ በሌላ መልኩ በቀላሉ ከአኻያ ዛፍ ጋር ሊወዳደሩ የሚችሉ ጅራቶች ነበሯቸው፡፡

በግምት እያንዳንዱ የጥንት ሥልጣኔ በጣም ትልቅ የሆኑትን የአጥቢ እንስሳቶችን ፍጥረቶች የሚያሳይ የተወሰነ ጥበብ አለው፡፡ ፔትሮግሊፍስ፤ቁርጥራጮች፤እና እንዲያውም በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ጥቂት የሸክላ ሥሪቶች የዘመናዊውን ዳይኖሰሮች ገላጭ ይመስላል፡፡ በደቡብ አሜሪካ ያሉት የአለት ሥሪቶች ዳይፕሎኮኮስ የሚመስሉ ፍጥረቶችን የሚጋልቡ ሰዎችን ያሳያል፤እና በሚያስደንቅ ሁኔታ ትራይሴራቶፕስ የሚመስሉትን፤ ፔትሮዳክታይል የሚመስሉትን፤ እና ትራይኖሳርስ-ሬክስ የሚመስሉትን ፍጥረታት የተለመደውን ምስሎች ይዟል፡፡ የሮማ ሞሳይኮች፤የማያኖች የሸክላ ሥራ እና የባቢሎናውያን ከተማ ግድግዳዎች በሙሉ የሰውን የባህል ውህደት፤በእነዚህ ፍጥረቶች በድንበር ያልተገደበውን ውበት ይመሰክራሉ፡፡ በዕውቀት የተሞሉ ልክ ማርኮ ፖሎን የመሳሰሉት የሚደነቁ እጅግ ዋጋ ካላቸው ድቦች ጋር ይደባለቃሉ፡፡ ትልቅ መጠን ካለው አንትሮፊክ እና ታሪካዊ ማስረጃዎች በተጨማሪ ለዳይኖሰሮች እና ለሰው ልጆች አብሮ መኖር ልክ እንደ ሰዎች እና የዳይኖሰሮች ቅሪተ-አካል ዱካዎች በሰሜን አሜሪካ እና ምዕራባዊ-መሐል እስያ ቦታዎች አንድ ላይ የተገኙ ቁሳዊ ማስረጃዎች አሉ፡፡

ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዳይኖሰሮች አሉ ? ጉዳዩ ከመጠናቀቅ የራቀ ነው፡፡ አንተ ያሉትን ማስረጃዎች እንዴት እንደምትተረጉም እና በዙሪያህ ያለውን ዓለም እንዴት በምትመለከት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል ከተተረጎመ የወጣቷ ምድር ትርጓሜ የሚሆን እና ዳይኖሰሮች እና የሰዎች ልጆች አንድ ላይ የመሆናቸው ሀሳብ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ዳይኖሰሮች እና ሰዎች አንድ ላይ ከኖሩ ዳይኖሰሮችን ምን ነካቸው ? መጽሐፍ ቅዱስ ጉዳዩን የማያነሳ ሆኖ ሳለ ምናልባት ዳይኖሰሮች ፍጹም ከማይጠበቅ አካባቢያዊ ለውጥ እና በተደጋጋሚ እስኪጠፉ ድረስ በሰዎች ከመታደናቸው እውነታ የተነሳ ከጥፋት ውኃው የተወሰኑ ጊዜያት በፊት ሞተዋል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዳይኖሰሮች ምን ይላል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዳይኖሰሮች አሉ?
© Copyright Got Questions Ministries