settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ክርስቲያኖች እንዴት ነው ልጆቻቸውን መቅጣት ያለባቸው? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መልስ፤


ለጆችን በተሸለ መንገድ መቅጣትን መማር ከባድ ሃላፊነት ነው ግን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንዶች አካላዊ ቅጣት ለጅን በመቀመጫው ላይ መታ መታ ማድረግ ብቻ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ የተፈቀደው ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ለተወሰነ ጊዜ ሌላ ምንም የፈለገውን ነገር ሳያደርግ ማቆየት “time-outs” እና አካለዊ ቅጣትን የማያስከትሉ ሌሎች ቅጣቶች የተሻለ ውጤታማ ነው ይላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል; መጽሐፍ ቅዱስ አካላዊ ቅጣት ተገቢ ጠቃሚና አስፈላጊ ነው ይላል፡፡

በተሳሳተ መንገድ አንረዳ፤ በማንኛውም መንገድ የልጆችን ጉዳት አንደግፍም፡፡ ልጆች ፈጽሞ አካላዊ ጉደት እስከሚደርስባቸው ድረስ መቀጣት የለባቸውም፡፡ ቢሆንም ቅሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል ግን ተገቢና ጥብቅ አካላዊ የልጆች ቅጣት መልካም ነገር ሲሆን ለጆች በጥሩ ሁኔታ ታርመው እንዲያድጉ ይረዳል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ክፍሎች በትክክል ስለ አካላው ቅጣት ይገልጻል፡፡ ‹‹ሕፃንን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታው አይሞትምና።በበትር ትመታዋለህ፥ ነፍሱንም ትታደጋለህ።›› (ምሳ 23:13-14; እንዱሁም 13:24; 22:15; 20:30). መጽሐፍ ቅዱስ የቅጣትን አስፈላጊነት ትኩረት ይሰጣል ወጤት ሰዎች ለመሆን ለሁላችንም የሚያስፈልግ ሰሆን በወጣትነት ጊዜ ደግሞ ቢደረግ አስተማሪና ለመልመድም የተሸለ ጊዜ ይሆናል፡፡ ያልተቀጡ ልጆች ለስልጣን አክብሮት የሌላቸው አመጸኞች ሆነው ያድጋሉ በውጤቱም እግዚአብሔርን በፈቃደኝነት መታዘዝና መከተል አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርም እራሱ እኛን በማረም በትክክለኛው መንገድ ለመምራት ከስህተታችን ለመመለስ እኛን ለማበርታት ይቀጣናል፡፡ (መዝ 94:12; Proverbs 1:7; 6:23; 12:1; 13:1; 15:5; ኢሳ 38:16; ዕብ 12:9)፡፡

ቅጣትን በትክክል እንደ እግዚአብሔረ ቃል ተግባራዊ ለማድረግ ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቅጣት የሚሰጠውን ምክር ማወቅ አለባቸው፡፡ የምሳሌ መጽሐፍ ብዙ ጥበብን ልጆችን በቀና መንገድ ስለማሳደግ ይናገራል፡፡ ‹‹በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ ያልተቀጣ ብላቴና ግን እናቱን ያሳፍራል። ››(ምሳ 29:15). ይህ ጥቅስ ለጆችን አለመቅጣት ተከትሎ የሚመጣውን ጉዳት ይናገራል፤ ቤተሰብ ያፍራል፡፡ ቅጣት የራሱ የሆነ አላማ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ ለልጁ ጥቅም ሊደረግና ፈጽሞ ለጆችን መጉዳትና እነክብካቤ የጎደለውን አጓጉል ነገር ማድረግን ትክክል ነው ብለን እንድንል የሚያስችል መሆን የለበትም፡፡ ቁጠን ንዴትን ለመግለጽ ፈጽሞ መደረግ የለበትም፡፡

ቅጣት ሰዎችን ለማረምና በትክክለኛው መንገድ እንዲሄዱ ለማሰልጠን ይጠቅማል፡፡ ዕብ 12፡11፡- ‹‹ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።›› ልክ በቤተሰብና በልጆች መካከል እንደሚሆን የእግዚአብሔር ቅጣት ከፍቅር ነው፡፡ ቅጣት በመጨረሻ አካላዊ ጉዳትን ወይም ህመምን ለማድረስ የሚደረግ መሆን የለበትም፡፡ አካላዊ ቅጣት ምንጊዜም ከተደረገ በኋላ ልጁ ውይንም ልጅቷ እንደምትወደድ እርግጠኛ እንድትሆን ማበረታታት ቅጣቱን ተከትሎ መደረግ አለበት፡፡ እግዚአብሔር ስለሚወደን እንደሚቀጣን እኛም ልጆቻችንን ስለምንወዳቸው እንደምንቀጣቸው ለማስተማር ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው፡፡

እንደ ‹‹ታይም አውት›› ሌሎች የቅጣት መንገዶች በአካላዊ ቅጣት ፈንታ መጠቀም አለብን ? አንዳንድ ሰዎች ልጆቻቸው ለአካላዊ ቅጣት ትክክለኛውን ምላሽ አልሰጡም ሲሉ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ አንዳንድ ቤተሰቦች ‹‹ታይም አውት›› ከልጆች ላይ ጊዜን ነጥቆ መውሰድ የባህሪ ለውጥ እንዲያደርጉ ያበረታታል ይላሉ፡፡ ምክንያቱ እሱ ከሆነ በሚቻለው ሁሉ ቤተሰብ የተሻለውን የባህሪ ለውጥ የሚያስገኝላቸውን መጠቀም አለባቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በማይካድ መልኩ አካላዊ ጥቃትን ቢያስተዋውቅም መጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ትኩረት የሚያደርገው ወጤቱን ለማምጣት የተሻለው የቅጣት መንገድ ይህ ነው ከሚለው ይልቅ መልካም በህሪ የመገንባት አላማ ላይ ነው፡፡

ይህንን ጉዳይ ከበድ የሚያደርገው መንግስት አካላዊ ቅጣት ሁል ልጆች የሚጎዳ ነው ብሎ ሁሉንም በአንድ መመደቡ ነው፡፡ ብዙ ቤተሰብ ልጆቹን አይቀጣም መክርያቱም ለመንግስት ይናገሩብንና ለጆቻችንን ይወስዱበናል ብለው ስጋት ውስጥ ይገባሉ፡፡ መንግስት አካላዊ ቅጣትን በልጆች ላይ ማድረግ ህገ ወጥ ነው ቢል ቤተሰብ ምን ማድረግ አለበት? እንደ ሮሜ 13፡1-7 ቤተሰብ ለመንግስት መገዛት አለበት፡፡ መንግስት የእግዚአብሔርን ቃል መቃወም የለበትም አካለዊ ቅጣት ማለት እንደመጽሐፍ ቅዱስ አባባል ለልጁ ጥቅም የሚደረግ ነው፡፡ ሆኖም ግን ልጆችን ከማጣትና ለመንግስት ‹‹እንክብካቤ›› ከመስጠት ልጆችን ትንሽም ቢሆን ቅጣት በሚያገኙበት ቤተሰብ መካከል እንዲኖሩ ማድረግ ይሻላል፡፡

በኤፌ 6፡4 አባቶች ልጆቻቸውን እንዳያስቆጧቸው ተጽፎአል፡፡ ከዚያ ይልቅ ወደ እግዚአብሔር መንገድ ያምጧቸው፡፡ ልጆችን ‹‹በእግዘአብሔር ምክርና ተግሳጽ›› ማሳደግ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ማረም፤ አዎን በፍቅር የሆነ አካላዊ ቅጣትን ይጨምራል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ክርስቲያኖች እንዴት ነው ልጆቻቸውን መቅጣት ያለባቸው? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries