settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ሃይማኖታዊ ሥርዓተኝነት ምንድነው፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?

መልስ፤


ሃይማኖታዊ ሥርዓተኝነት የሥነ-መለኮት ሥርዓት ሲሆን ሁለት ዋነኛ ግልጽ መለያዎች አሉት። 1) ቋሚነት ያለው እማሬያዊ የቅዱስ ቃሉ ፍቺ፣ በተለይም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት። 2) በእስራኤልና በቤተ-ክርስቲያን መካከል ያለ የእግዚአብሔር ፕሮግራም ልዩነት።

ሃይማኖታዊ ሥርዓተኞች የሚሉት የእነርሱ ሥነ-ትርጓሜ መርሖ እማሬያዊ ትርጉም የሚባለው ነው፣ ማለትም ለእያንዳንዱ ቃል በዕለት ተዕለት አጠቃቀሙ የተለመደውን ፍቺ መስጠት ነው። ተምሳሌቶች፣ ዘይቤዎች እና የመሳሰሉት ሁሉ በዚህ ዘዴ በጥሬው ይተረጎማሉ፣ ይህም በምንም መንገድ ከእማሬያዊ ፍቺ ጋር አይቃረንም። ተምሳሌቶችና ዘይቤያዊ አነጋገሮች እንኳ እማሬያዊ ፍች በጀርባቸው አላቸው።

ቅዱስ ቃሉን ለመመልከት ይህ የተሻለ መንገድ ለመሆኑ ቢያንስ ሦስት ምክንያቶች አሉ። አንደኛ፣ ከፍልስፍና አኳያ፣ የራሱ የቋንቋ ዓላማ የሚጠይቀው በጥሬው እንድንተረጉም ነው። ቋንቋ በእግዚአብሔር የተሰጠ ነው፣ ከሰው ጋር ለመገናኘት ይቻል ዘንድ። ሁለተኛው ምክንያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። በብሉይ ኪዳን እያንዳንዱ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለ ትንቢት በጥሬው ነው የተፈጸመው። የኢየሱስ ልደት፣ የኢየሱስ አገልግሎት፣ የኢየሱስ ሞት፣ እና የኢየሱስ ትንሣኤ ሁሉም የተከሰቱት በጥሬው ነው፣ ልክ በብሉይ ኪዳን እንደተተነበየው። አንዳችም ጥሬያዊ ያልሆነ የእነዚህ ትንቢቶች ፍጻሜ በአዲስ ኪዳን የለም። ይህ የሚሞግተው እጅጉን ለእማሬያዊ ዘዴ ነው። ቅዱስ ቃሉን በማጥናት እማሬያዊ ፍቺ ጥቅም ላይ ካልዋለ፣ ምንም ዓይነት ተጨባጭ መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት አይኖርም። እያንዳንዱ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን መተርጎም እንዲችል ነው፣ ይሰማማዋል ብሎ በተመለከተው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ፣ “ይህ ምንባብ ለእኔ ምን ይላል…” እየሆነ መጥቷል፣ “መጽሐፍ ቅዱስ ይላል…” በማለት ፈንታ። በአሳዛኝ መልኩ፣ ይህ በአሁኑ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የሚባለው አብዛኛው ጉዳይ ነው።

የሃይማኖታዊ ሥርዓተኝነት ሥነ-መለኮት የሚያስተምረው ሁለት የተለዩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች መኖራቸውን ነው፡ እስራኤልና ቤተ-ክርስቲያን። ሃይማኖታዊ ሥርዓተኞች ደኅንነት ዘወትር የሚሆነው በእምነት ነው ብለው ያምናሉ— በእግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን እና በተለይም በእግዚአብሔር ወልድ በአዲስ ኪዳን። ሃይማኖታዊ ሥርዓተኞች የሚይዙት ቤተ-ክርስቲያን እስራኤልን በእግዚአብሔር ፕሮግራም እንዳልተካች ነው፣ እንዲሁም ለእስራኤል የሆኑት የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች ወደ ቤተ-ክርስቲያን እንዳልተላለፉ። እነርሱ የሚያምኑት እግዚአብሔር ለእስራኤል የገባው ቃል ኪዳን (ለመሬት፣ ብዙ ትውልዶች፣ እና ባርኮቶች) በብሉይ ኪዳን፣ ተጠቃሎ የሚፈጸመው ራዕይ 20 ላይ በተነገረው የ1000 ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው። ሃይማኖታዊ ሥርዓተኞች የሚያምኑት፣ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን አትኩሮቱን በቤተ ክርስቲያን ላይ እንዳደረገ፣ እሱም ወደፊት አትኩሮቱን በእስራኤል ላይ ያደርጋል (ሮሜ 9-11)።

ይህን ሥርዓት እንደ መሠረት በመውሰድ፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓተኞች መጽሐፍ ቅዱስን የሚረዱት በሰባት ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው፡ ንጽሕና (ዘፍጥረት 1፡1-3፡7)፣ ሕሊና (ዘፍጥረት 3፡8፡22)፣ የሰዎች መንግሥት (ዘፍጥረት 9፡1-11፡32)፣ ቃል ኪዳን (ዘፍጥረት 12፡1- ዘጸአት 19፡25)፣ ሕግ (ዘጸአት 20፡1-ሐዋ. 2፡4)፣ ጸጋ (ሐዋ. 2፡4- ራዕይ 20፡3)፣ እና የሚሊኒየም መንግሥት (ራዕይ 20፡4-6)። እንደገናም፣ እነዚህ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ለደኅንነት መንገዶች አይደሉም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰው ጋር የሚዛመድበት ጠባያት እንጂ። ሃይማኖታዊ ሥርዓተኝነት፣ እንደ ሥርዓት ውጤቱ ቅድመ ሚሊኒየማዊ ትርጉምን ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ይሰጣል፣ እንዲሁም ዘወትር ቅድመ-ታላቁ መከራ ትርጉምን ለመነጠቅ። ለማጠቃለል፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓተኝነት፣ ሥነ-መለኮታዊ ሥርዓት ሲሆን አጽንዖት የሚሰጠውም ለመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እማሬያዊ (ጥሬ) ትርጉም በመስጠት ነው፣ በእስራኤልና በቤተ-ክርስቲያን መካከል ግልጽ ለሆነ ልዩነት እውቅና ይሰጣል፣ መጽሐፍ ቅዱስንም ወደ ተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ያደራጃል፣ እንደሚያቀርባቸው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ሃይማኖታዊ ሥርዓተኝነት ምንድነው፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries