settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍቺ እና ዳግም ጋብቻ ምን ይላል?

መልስ፤


በመጀመሪያ ማንም በፍቺ ላይ የቱንም ዓይነት አመለካከት ቢኖረውም ፤ትንቢተ ሚልኪያስ 2፡16ን ማስታወስ ጠቃሚ ነው፤ “መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር”፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ጋብቻ የዕድሜ ልክ መሰጠት ነው፡፡ “ስለዚህ አንድ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም።” “እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው” (የማቴዎስ ወንጌል 19፤6)። ጋብቻ የሁለት ኃጥአተኛ ሰዎች ማንነት ያካተተ በመሆኑ ምክንያት ፍቺዎች ሊከሰቱ እንዳሉ እግዚአብሔር ያን ያውቀዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ለየት ባለ መልኩ የሴቶችን የፍቺ መብቶችን ለመጠበቅ የተወሰኑ ህጎችን አስቀምጧል (ኦሪት ዘዳግም 24፤1-4)፡፡ እነዚህ ህጎች የተሰጡት የእግዚአብሔር መሻቶች ሆነው ሳይሆን በሰዎች የልብ ጥንካሬ ምክንያት እንደሆነ ኢየሱስ ያን ጠቁሟል (የማቴዎስ ወንጌል 19፤8)፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ባደረገ ፍቺ እና ዳግም ጋብቻ መፈቀዳቸው ላይ የሚደረገው ክርክር በዋናነት በማቴዎስ ወንጌል 5፤32 እና 19፡9 ውስጥ ባሉት በኢየሱስ ቃላቶች ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ በመጽሐፍት ውስጥ “ያለ ዝሙት በቀር” የሚለው ለፍቺ እና ዳግም ጋብቻ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊያሰጥ የሚችል ብቸኛው ሐረግ ነው፡፡ ብዙ ተርጓሚዎች ይህንን “ገደብ የተደረገበትን ምንባብ” “በትጭጭት” ወቅት “ዝሙትን” ለማመልከት እንደሆነ ይገነዘባሉ፡፡ በአይሁዶች ባህል ወንድ እና ሴት “ተጫጭተው” ባሉበት ጊዜ እንኳን እንደተጋቡ ይቆጠሩ ነበር፡፡ በዚህ ምልከታ መሠረት በዚህ “በትጭጭት” ወቅት የሆነ ግብረ-ገብነት ማጣት ለፍቺ የሚሆን ብቸኛው ትርጉም ያለው ምክንያት በሆነ ነበር፡፡

ሆኖም ግን የግሪኩ ቃል በትዳር ”ዝሙትን” ማንኛውም ጾታዊ ግብረ ገብነት ያጣ ዓይነት ቃል ማት ሊሆን እንደሚችል ተረጉሞታል፡፡ ከጋብቻ ውጪ የሆነ ጾታዊ ግንኙነት፤ ሴተኛ አዳሪነት፤አመንዝራነት ወ.ዘ.ተ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ምናልባት ግብረ-ገብነት ያጣ ጾታዊ ግንኙነት ከተፈጸመ ፍቺ የሚፈቀድ ነው እያለ ይሆናል፡፡ ጾታዊ ግንኙነቶች የጋብቻ ትስስር ዋነኛ ክፍል ናቸው፤ “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” (ኦሪት ዘፍጥረት 2፤24፣የማቴዎስ ወንጌል 19፣5፤ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፤31)፡፡ ስለዚህ የትኛውም የዚያ ትስስር ከጋብቻ ውጪ በሆኑ ጾታዊ ግንኙነቶች መሰበር ምናልባት ለፍቺ ተቀባይነት ያለው ምክንያት ይሆን ይሆናል፡፡ ያ ከሆነ በዚህ ምንባብ ውስጥ ኢየሱስም ዳግም ጋብቻ በሀሳቡ ውስጥ አለ፡፡ “እና ሌላ ማግባት” የሚለው ሐረግ (የማቴዎስ ወንጌል 19፡9) የትኛውንም ትርጉም ቢሰጠውም ፍቺ እና እንደገና ማግባት በተከለከለ ምንባብ ሁኔታ እንደሚፈቀዱ ያን ያመለክታል፡፡ ነቀፋ ለሌለበት ወገን ብቻ ዳግመኛ ጋብቻ እንደሚፈቀድ ያን ልብ ማለቱ ጠቃሚ ነው፡፡ ምንም እንኳን በጽሑፉ ውስጥ ባይጠቀስም ከፍቺ በኃላ ለሚሆን ዳግም ጋብቻ ደመወዙ ከግብረ ገብነት ውጪ የሆነ ጾታዊ ግንኙነት በፈጸመው ሰው ላይ እንጂ በተበደለው ሰው ላይ አይደለም፡፡ ምናልባት “በደለኛው ወገን” ለዳግመኛ ጋብቻ ፈቃድ የሚያገኝበት ሁኔታዎች ይኖሩ ይሆናል፤ነገር ግን በዚህ ምንባብ ውስጥ ለማስተማሪያነት አልቀረበም፡፡

አንዳንዶች 1ኛ ቆሮንቶስ 7፤15 ፤ያላመነ የትዳር ጓደኛ ያመነን የሚፈታ ከሆነ ዳግመኛ ጋብቻን የሚፈቅድ ሌላ “ክልከላ” እንደሆነ ይረዱታል፡፡ ሆኖም ግን ሁኔታው ዳግመኛ ጋብቻን አይጠቅስም፤ነገር ግን አንድ የማያምን የትዳር ጓደኛ መለየትን ቢወድ አማኙ በጋብቻው እንዲቀጥል አይታሰርም፡፡ ምንም እንኳን የቱንም ያህል በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጠቀሰ ቢሆንም ሌሎች (በትዳር ጓደኛ ወይም በልጅ) የሆነ አግባብነት የሌለው ድርጊት ለፍቺ ዋጋ ያለው ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ምናልባት ይሄ በጣም በጥሩ ሁኔታ ጉዳዩ ሆኖ ሳለ በእግዚአብሔር ቃል ላይ መገመት በፍጹም አዋቂነት ሆኖ አያውቅም፡፡

አንዳንድ ጊዜ እንዳይታሰቡ በተደረጉ ምንባብ ጉዳዮች ክርክር የመወሰዱ እውነታ “በዝሙት” ምንም ነገር ማለት ቢሆን የፍቺ ዋጋ ነው እንጂ ለእሱ መስፈርት አይደለም፡፡ ማመንዘር እንኳን በሚፈጸምበት ጊዜ ጥንዶች በእግዚአብሔር ጸጋ አማካይነት ይቅር ማለትን መማር እና ትዳራቸውን እንደገና መገንባት ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር በጣም በበለጠ ይቅር ብሎናል፡፡ በእርግጠኝነት የእርሱን ምሳሌ እና የማመንዘርን ኃጥአት እንኳን ይቅር ማለት እንችላለን (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤32)፡፡ ሆኖም ግን በብዙ ምሳሌ የትዳር ጓደኛ ይቅር የማይል እና ግብረ-ገባዊ ባልሆነ ወስባዊ ማንነት ይቀጥላል፡፡ ያ የማቴዎስ ወንጌል 19፤9 ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበት ሥፍራ ነው፡፡ በተጨማሪ ብዙዎችም ከፍቺ በኃላ ምናልባት እግዚአብሔር ሳያገቡ እንዲቆዩ በሚፈልግበት ጊዜ እንደገና ለማግባት ይፈጥናሉ፡፡ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሀሳባቸው የተከፋፈለ እንዳይሆን ሳያገቡ እንዲኖሩ ይጠራቸዋል (1ኛ ቆሮንቶስ 7፤32-35)፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ከፍቺ በኃላ እንደገና ማግባት አማራጭ ሊሆን ይችላል፤ ቢሆንም ያ ብቸኛው አማራጭ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡

በሚያምኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ያለው የፍቺ መጠን ከማያምነው ዓለም ጋር በተቀራረበ መልኩ ከፍ ማለቱ ያ የሚያስጨንቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር መፋታትን እንደሚጠላ (ትንቢተ ሚልክያስ 2፤16) እና ያ ዕርቅ እና ይቅርታ የአማኞች ህይወት መለያዎች (የሉቃስ ወንጌል 11፤4፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤32) ሊሆኑ እንደሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ በጣም በብዙ ያን ግልጽ ያደርጋል፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔር በልጆቹ መሐከል እንኳ ቢሆን ፍቺ እንደሚከሰት ያን ያውቃል፡፡ ምንም ፍቺ እና ወይም እንደገና ማግባት በማቴዎስ ወንጌል 19፤9 ምንባብ ውስጥ በተቀመጠው ማዕቀብ ላይታቀፍ የሚችል እንኳ ቢሆን የፈታ እና ወይም እንደገና ያገባ አማኝ በእግዚአብሔር አንዳች ባነሰ መልኩ እንደተወደደ ሊያስብ አይገባም፡፡ እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ ታላቅ በጎነትን ለማድረግ የክርስቲያኖችን በኃጥአት የተሞላ አለመታዘዝን እንኳን ይጠቀማል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍቺ እና ዳግም ጋብቻ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries