ጥያቄ፤
ተፋትቻለሁ። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ድጋሚ ላገባ እችላለሁ?
መልስ፤
ዘወትር እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎችን እንቀበላለን “በዚህ በዚህ ምክንያት ተፋትቻለሁ። ድጋሚ ላገባ እችላለሁ?” “ሁለቴ ተፋትቻለሁ— የመጀመሪያው በትዳር ጓደኛዬ አመንዝራነት ነው፣ ሁለተኛው አለመመጣጠን ነው። ሦስት ጊዜ የፈታ ሰው አፍቅሬአለሁ— የመጀመሪያው ባለመመጣጠን ነው፣ ሁለተኛው በእሱ በኩል በተፈጸመ ዝሙት፣ ሦስተኛው በሚስቱ በኩል በተፈጸመ ዝሙት ነው። እርስ በርስ ልንጋባ እንችላለን?” ይህንን የሚመስሉ ጥያቄዎች ለመመለስ እጅግ አስቸጋሪ ናቸው፣ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር ስለማይሄድባቸው፣ የተለያዩ ትዕይንቶችን በተመለከተ፣ ከፍቺ በኋላ ስለሚኖረው ጋብቻ።
በርግጠኝነት ማወቅ የምንችለው፣ የተጋቡ ጥንዶች ሁለቱም በሕይወት እስካሉ ድረስ እንደ ተጋቡ እንዲቆዩ የእግዚአብሔር ዕቅድ መሆኑን ነው (ዘፍጥረት 2፡24፤ ማቴዎስ 19፡6)። ለድጋሚ ጋብቻ ብቸኛው መተማመኛ፣ ከፍቺ በኋላ የሚሆነው ዝሙት ነው (ማቴዎስ 19፡9)፣ ይህም ቢሆን እንኳ በክርስቲያኖች መካከል አከራካሪ ነው። ሌለኛው አጋጣሚ ድጋፍን መተው ነው— የማያምን የትዳር ጓደኛ የሚያምን የትዳር ጓደኛ ጥሎ ሲሄድ (1 ቆሮንቶስ 7፡12-15)። ምንም እንኳ ይህ ምንባብ ድጋሚ ጋብቻን ለይቶ ባይገልጽም፣ በትዳር ታስሮ መቀመጥን ብቻ ያሳያል። እሱም ደግሞ አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ወይም የከፋ ስሜታዊ ጉዳት በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል፣ ለመፍታትና ድጋሚ ለማግባት። የሆነ ሆኖ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ይሄንን ለይቶ አያስተምርም።
ሁለት ነገሮችን በርግጠኝነት እናውቃለን። እግዚአብሔር መፋታትን ይጠላል (ሚልክያስ 2፡16)፣ እናም እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው። ፍቺ ሁሉ የኃጢአት ውጤት ነው፣ በአንደኛው የትዳር ጓደኛ ወይም በሁለቱም ቢሆን። እግዚአብሔር መፋታትን ይቅር ይላልን? እንዴታ! ፍቺ ከሌሎቹ ኃጢአቶች ይልቅ ይቅር የማይባል አይደለም። ለኃጢአት ሁሉ ይቅርታ ይገኛል፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለ እምነት (ማቴዎስ 26፡28፤ ኤፌሶን 1፡7)። እግዚአብሔር የፍቺ ኃጢአትን ይቅር የሚል ከሆነ፣ ያ ድጋሚ ለማግባት ነጻ ናችሁ ማለት ነውን? ሊሆን አይችልም። እግዚአብሔር አንዳንዴ ሰዎችን ሳያገቡ እንዲቀሩ ሊጠራ ይችላል (1 ቆሮንቶስ 7፡7-8)። ሳያገቡ መቅረት እንደ ርግማን ወይም ቅጣት መታየት አይኖርበትም፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ ለማገልገል እንዳለ አጋጣሚ እንጂ (1 ቆሮንቶስ 7፡32-36)። የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል፣ በስሜት ከመቃጠል ማግባት የተሻለ እንደሆነ (1 ቆሮንቶስ 7፡9)። አንዳንዴ ይህ ከፍቺ በኋላ ለድጋሚ ጋብቻ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
ስለዚህ፣ ድጋሚ ጋብቻ ማድረግ ትችላላችሁ፣ ወይስ ይኖርባችኋል? ያንን ጥያቄ መመለስ አንችልም። ባጠቃላይ፣ ያ በእናንተ እና በትዳር ጓደኛችሁ መካከል ነው፣ እናም በተለይ በእግዚአብሔር። ልንሰጥ የምንችለው ብቸኛው ምክር ስለ እናንተ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ነው፣ ለጥበብ፣ ምን እንድታደርጉ እንደሚሻ በተመለከተ (ያዕቆብ 1፡5)። ክፍት በሆነ አእምሮ ጸልዩ፣ እንዲሁም ጌታን በቅንነት ለምኑት በልባችሁ የእርሱን ፍላጎት እንዲያስቀምጥ (መዝሙር 37፡4)። የጌታን ፍቃድ እሹ (ምሳሌ 3፡5-6) የእሱንም ምሪት ተከተሉ።
English
ተፋትቻለሁ። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ድጋሚ ላገባ እችላለሁ?