settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር አለ? ለመኖሩስ ምን ማስረጃ አለ?

መልስ፤


እግዚአብሔር አለ? ለዚህ የክርክር ሐሳብ ብዙ ትኩረት መሰጠቱ የሚስብ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያመለክተው ከዓለም ሕዝብ ዘጠና ከመቶ የሚሆነው በእግዚአብሔር ወይም በሌላ አንድ ልዑል ሀይል ያምናል። እንዲህም ሆኖ ግን የእግዚአብሔርን መኖር የማረጋገጥ ሀላፊነት የወደቀው በነዚሁ አማኞች ላይ ነው። እንደኔ ግን ሁኔታው የተገላቢጦሽ መሆን ነበረበት።

ቢሆንም የእግዚአብሔር መኖር ማረጋገጥም አለማረጋገጥም አይቻልም። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሕልውና በእምነት መቀበል እንዳለብን ይነግረናል፣ “ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት” (ዕብራውያን ፲፩፥፮)። የእግዚአብሔር ፍላጎት ቢሆን ኖሮ ህልውናውን ለዓለም ለማረጋገጥ በቀላሉ ወርዶ ይታየን ነበር። ይህን ቢያረግ ግን እምነት ቦታ ባልኖረው ነበር። “ኢየሱስም፣ ‘አንተ ስላየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብፁዓን ናቸው’ አለው” (ዮሐንስ ፳፥፳፱)።

ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ለመኖሩ ማሰረጃዎች የሉንም ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያውጀው፣ “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ። ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤ ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቻው በጀሮ የሚሰማ አይደለም። ያም ሆኖ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፣ ቃላቸውም እስከ አለም ዳርቻ ይወጣል” (መዝሙር ፳፥፳፱)። ከዋክብትን ስናይ፣ የህዋን ስፋት ስናስብ፣ የተፈጥሮን ተአምራት ስናደንቅ፣ የጀንበር ጥልቀት ውበት ስናይ - ይህ ሁሉ ትዕይንት ወደ ፈጣሪ አመላክ ያመለክታል። ይህ ካልበቃም ስለእግዚአብሔር መኖር በልባችን ውስጥ ማስረጃ አለ። መክብብ ፫፥፲፩ እንደሚነግረን፣ “…በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ..።” ከዚህ ሕይወት ውጭ ሌላ፣ ከዚህ ዓለም ውጭ ሌላ እነዳለ በውስጣችን ይሰማናል። ይህንን ስሜት አእምሮአችን ላይቀበለው ይችላል፤ የእግዚአብሔር ህልውና ግን በኛ ላይ ይኖራል። እነዲህም ሆኖ ግን እግዚአብሔር መኖሩን የሚክዱ እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ያስጠነቅቀናል፣ “ሞኝ በልቡ ‘እግዚአብሔር የለም’ ይላል” (መዝሙር ፲፬፥፩)። በታሪክ ከሁሉም ባህሎች፣ ስልጣኔዎችና አህጉሮች ከሚኖሩት ሰዎች ዘጠና ስምንት ከመቶ የሚሆኑት ባንድ ልዑላዊ ሀይል ያምናሉ። ስለዚህም ይህንን እምነት በሰዎች ዘንድ ያሳደረ የሆነ ነገር (ወይም ሰው) አለ።

ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ሌላ ስለ እግዚአብሔር ህልውና ሥነ አመክንዮአዊ የሆኑ ነጥቦችን ማስቀመጥ ይቻላል። በመጀመሪያ አንቶሎጂካዊ የሆነ መከራከሪያ ማቅረብ ይቻላል። በጣም ተወዳጅ የሆነው አነቶሎጂካዊ መከራከሪያ የእግዚአብሔርን መኖር ለማረጋገጥ የእግዚአብሔርን ጽንሰ ሓስብ ይጠቀማል። ሲጀምርም እግዚአብሔርን “ከሱ የሚበልጥ ነገር ማሰብ የማይቻለውን” በማለት ያስቀምጠዋል። ቀጥሎም መኖር ካለመኖር ስለሚበልጥ ከሁሉም የሚልቅ አካል መኖር አለበት። እግዚአብሔር የለም ካልን ግን እግዚአብሔር ከሁሉም የሚልቅ ሁለንተና አይሆንም ማለት ነው፤ ይህ ግን የእግዚአብሔርን መግለጫ የሚቃረን ይሆናል። ሁለተኛው የመከራከሪያ ነጥብ ቴሎሎጂካዊ ነው። ይህ መከራከሪያ እንደሚለው ፍጥረት ሁሉ የተዋጣለት የአፈጣጠር ጥበብ ስለሚያሳይ ይህንን ድንቅ ጥበብ የተካነ ፈጣሪ መኖር አለበት። ለምሳሌ ያህል የምንኖርባት ዓለም ከፀሐይ በትንሽ መቶ ኪሎሜትሮች ብትቀርብ ወይም ብትርቅ ኖሮ ህይወት ያለው ነገር ማኖር ባልቻለች ነበር። በዓለም ሽፋን ያሉ ንጥረ ነገሮች ውህዳቸው በትንሽ ነጥብ ዝቅ ወይም ከፍ ብሎ ቢሆን ኖሮ ህይወት ያለው ሁሉ ይሞት ነበር። የአንድ የፕሮቲን ውህድ ባጋጣሚ የመፈጠር ዕድሉ ከኢምንት ያነሰ ነው። እንግዲህ አንድ ሴል ደግሞ በሚልዮን በሚቆጠሩ ውህዶች የተሠራ ነው።

ሦስተኛው መከራከሪያ ደገሞ ኮስሞሎጂካዊ ነው። ማንኛውም ክትለት መንስኤ አለው። ጠፈርና በውስጧ ያለው ሁሉ ክትለት ነው። ይህንን ሁሉ ክትለት እንዲፈጠር ያደረገ አካል መኖር አለበት። ስለዚህም ይህንን ክትለት የፈጠረ አንድ የሆነ “ያልተፈጠረ” ነገር መኖር አለበት። ይህ “ያልተፈጠረ” ነገር እግዚአብሔር ነው። አራተኛው መከራከሪያ ገብነታዊ ነው። በታሪክ ውስጥ ያሉት ባህሎች የተለያዩ ህጎች አሉዋቸው። ሁሉም ሰው ትክክልና ስህተትን የሚለይበት ስሜት ተሰጥቶታል። መግደል፣ መዋሸት፣ መስረቅና ግብረገባዊ ያልሆኑ ስራዎች በሁሉም የተፀየፉ ናቸው። ታድያ ይህ ትክክል ከስህተት የመለየት ስሜት ካንድ ቅዱስ እግዚአብሔር ካልሆነ ከምን መጣ ሊባል ነው?

ሆኖም ግን ይህንን ግልጽና የማያወላዳ የእግዚአብሔር ህልውና ሰዎች እነደሚክዱና በሐሰትም እንደሚያምኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ሮሜ ፩፥፳፭ እንደሚገልፀው፣ “የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ለወጡ፤ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡር አመለኩ፤ አገለገሉም፤ ፈጣሪም ለዘላለም የተመሰገነ ነው፤ አሜን።” ሰዎች በእግዚአብሔር ላለማመን ሰበብ ሊፈልጉ እነደማይችሉ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያውጃል፣ “ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ከፍጥረቱ በግልጽ ይታያል፤ ስለዚህ ሰዎች ማመካኛ የላቸውም” (ሮሜ ፩፥፳)።

ሰዎች በእግዚአብሔር የማያምኑበት ምክንያት “ኢሳይንሳዊ” ስለሆነ ወይም “ማስረጃ” ስለሌለ ነው ይላሉ። እውነተኛው ምክንያታቸው ግን አንዴ በእግዚአብሔር ማመን ከጀመሩ በሱ ሐላፊነት እንዳለባቸውና ከሱ ይቅርታ መሻት እነደሚኖርባቸው ሰለሚታያቸው ነው (ሮሜ ፫፥ ፳፫፣ ፮፥፳፫)። እግዚአብሔር ከሌለ ግን የፈለግነውን ብናረግ ይፈረድብናል የሚል ስጋት አየኖረንም። በዚህ ምክንያት ይመስለኛል የኢቮሉሸን ጽንሰ ሐሳብ በብዙዎቹ የሚታመንበት - በእግዚአብሔር ከማመን ሌላ አማራጭ ለማግኘት። እግዚአብሔር አለ፣ ለመኖሩም ሁሉም ያውቀዋል። አነዳነዶቹ እግዚአብሔር እንደሌለ ለማሳመን በሀይለኛው መሟገታቸው ለህልውናው በቂ ማስረጃ ነው።

አንድ የመጨረሻ መከራከሪያ ለማቅረብ ይፈቀድልኝ። እግዚአብሔር እነዳለ እንዴት አውቃለሁ? እግዚአብሔር እንዳለ የማውቀው በየቀኑ ስለማናግረው ነው። በእርግጥ መልሶ ሲናገረኝ ድምፅ አያሰማም፣ ቢሆንም ህልውናውንና መሪነቱን ይሰማኛል፤ ፍቅሩ ይታወቀኛል፤ ጸጋውንም ይናፍቀኝል። በህይወቴ ውስጥ ለተከሰቱት አንዳንድ ነገሮች ካለእግዚአብሔር በቀር ሌላ ምክንያት ሊኖረኝ አይችልም። እግዚአብሔር በተአምራቱ አድኖኛል፤ ሕይወቴንም ቀይሮታል። ስለዚህም ህልውናውን ማመንና ማመስገን ሲያንሰኝ ነው እላለሁ። እነዚህን ሁሉ ያቀረብኳቸው መከራከሪያዎች በራሳቸው ብቻ ኢአማኙን ለማሳመን በቂ ናቸው አልልም። የኋላ ኋላ የእግዚአብሔር ህልውና በእምነት ብቻ መቀበል አለብን (ዕብራውያን ፲፩፥፮)። በእግዚአብሔር ማመን በጨለማ ላይ መዝለል ማለት አይደለም፤ በብርሀን በተሞላና ዘጠና ከመቶ የአለም ሕዝብ ከቆመበት ክፍል ውስጥ መቀላቀል እነጂ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር አለ? ለመኖሩስ ምን ማስረጃ አለ?
© Copyright Got Questions Ministries