settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ባልንጀሮቼንና የቤተሰቤን አባላት በወንጌል እንዴት ልደርስ እችላለሁ፣ ሳላስቀይማቸውና ሳልገፋቸው?

መልስ፤


ምንም ቢሆን እያንዳንዱ ክርስቲያን የቤተሰብ አባላት፣ ባልንጀራ፣ የሥራ ባልደረባ፣ ወይም ትውውቅ ያለው ሰው፣ እሱም ክርስቲያን ያልሆነ ይኖረዋል። ወንጌልን ከሌሎች ጋር መካፈል አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ እንዲሁም በስሜት የቅርብ ትስስር ያለህን የሚያካትት ከሆነ እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን አንዳንድ ሰዎች በወንጌል ደስ አይሰኙም (ሉቃስ 12፡51-53)። ሆኖም፣ ወንጌልን እንድንካፈል ታዘናል፣ ይህን ላለማድረግም ምንም ሰበብ አይኖርም (ማቴዎስ 28:19-20; ሐዋ. 1:8; 1 ጴጥ. 3:15)።

ስለዚህ፣ የቤተሰብ አባሎቻችንን፣ ባልንጀራዎቻችንን፣ የሥራ ባልደረቦቻችንን፣ እና የምናውቃቸውን ሰዎች እንዴት በወንጌል መድረስ እንችላለን? ማድረግ የምንችለው በጣም አስፈላጊ ነገር ስለ እነርሱ መጸለይ ነው። እግዚአብሔር ልባቸውን እንዲቀይርና ዓይናቸውን እንዲከፍት መጸለይ (2 ቆሮንቶስ 4፡4) ለወንጌል እውነት። እግዚአብሔር ለእነርሱ ባለው ፍቅር እንዲያሳምናቸው መጸለይ፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው መዳን መሻት እንዲሆናቸው (ዮሐንስ 3፡16)። እንዴት እንደምታገለግላቸው ጥበብን እንዲሰጥህ መጸለይ (ያዕቆብ 1፡5)። ከመጸለይ በተጨማሪ፣ በእነርሱ ፊት መልካም የክርስትና ሕይወት መኖር ይገባናል፣ በገዛ ራሳችን ሕይወት እግዚአብሔር ያደረገውን ለውጥ ይመለከቱ ዘንድ (1 ጴጥ. 3፡1-2)። የአሲሲው ቅዱስ ፍራንሲስ አንድ ጊዜ እንዳለው፣ “በሁሉም ጊዜ ወንጌልን ስበኩ፣ አስፈላጊ ሲሆን ቃል ተጠቀሙ።”

በመጨረሻም፣ በምናካፍለው ወንጌል ፍቃደኛና ግልጽ መሆን አለብን። በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የደኅንነት መልእክት ለባልንጀሮቻችሁና ለቤተሰባችሁ አውጁ (ሮሜ 10፡9-10)። ዘወትር እምነታችሁን ለመናገር ዝግጁ ሁኑ (1 ጴጥ. 3፡15)፣ በጨዋነትና ባክብሮት እንዲህ በማድረግ። በመዳረሻም፣ የምንወዳቸውን ደኅንነት ለእግዚአብሔር መተው ይኖርብናል። ሰዎችን ማዳን የሚችለው የእግዚአብሔር ኃይልና ጸጋ ነው እንጂ የእኛ ጥረት አይደለም። የተሻለውና በይበልጥ ልናደርገው የምንችለው ለእነርሱ መጸለይ ነው፣ ለእነርሱ መመስከር፣ በፊት ለፊታቸውም ክርስቲያናዊ ሕይወት መኖር።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ባልንጀሮቼንና የቤተሰቤን አባላት በወንጌል እንዴት ልደርስ እችላለሁ፣ ሳላስቀይማቸውና ሳልገፋቸው?
© Copyright Got Questions Ministries