ጥያቄ፤
መዳን በእምነት ብቻ ነው ወይስ በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ነው?
መልስ፤
ይሄ ምናልባት በሁሉም የክርስቲያን ሥነ-መለኮት ውስጥ በጣም ጠቃሚ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ የመታደስ፤ በፕሮቴስታንት አቢያተ-ክርስቲያናት እና በካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን መካከል የመከፋፈል ምክንያት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስትና እና በብዙዎቹ የክርስቲያን አምልኮቶች መካከል አቢይ ልዩነት ነው፡፡ መዳን በእምነት ብቻ ነውን ወይስ በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ነው? በኢየሱስ በማመን ብቻ ነው የዳንኩት ወይስ በኢየሱስ ማመን እና የተወሰኑ ነገሮችን ማድረግ አለብኝ?
የእምነት ብቻውን ወይስ በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ጥያቄ ለማስታረቅ ከባድ በሆኑ ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ወደ ሮሜ ሰዎች 3፤28፤5፤1 እና ወደ ገላቲያ ሰዎች 3፤24ን ከያዕቆብ መልዕክት 2፤24 አወዳድር፡፡ የተወሰኑቱ በጳውሎስ (መዳን በእምነት ብቻ ነው) እና በያዕቆብ (መዳን በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ነው) መካከል ልዩነት ያያሉ፡፡ ጳውሎስ መጽደቅ በእምነት ብቻ እንደሆነ አጥብቆ ይናገራል (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፤8-9) ያዕቆብ ደግሞ መጽደቅ በእምነት እና በሥራም ጭምር ነው እያለ ነው፡፡ ይህ ግልጽ ችግር ያዕቆብ በትከክክል ስለ ምን እየተናገረ እንዳለ በመመርመር ተመልሷል፡፡ ያዕቆብ አንድ ሰው ምንም ዓይነት በጎ ሥራዎችን ሳያደርግ እምነት ሊኖረው ይችላል የሚለውን እምነት እያፈረሰ ነው (የያዕቆብ መልዕክት 2፤17-18)፡፡ ያዕቆብ በክርሰቶስ የሆነ እውነተኛ እምነት የተለወጠን ህይወት እና በጎ ሥራዎችን ይፈጥራል የሚለውን ነጥብ እያጎላ ነው(የያዕቆብ መልዕክት 2፤20-26)፡፡ ያዕቆብ መጽደቅ በእምነት እና በሥራም ጭምር ነው እያለ አይደለም ነገር ግን በእውነት በእምነት የጸደቀ ያ ሰው ይልቅ በህይወቱ/በህይወቷ በጎ ሥራዎች ይኖረዋል/ይኖራታል፡፡ አንድ ሰው አማኝ እንደሆነ ቢናገር ነገር ግን በህይወቱ/በህይወቷ በጎ ሥራዎች ከሌሉ እሱ/እሷ በክርስቶስ እውነተኛ እምነት የላቸውም ይሆናል፡፡ (የያዕቆብ መልዕክት 2፤14፤17፤20፤26)
ጳውሎስ በጽሑፎቹ ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ይናገራል፡፡ የመልካም ፍሬ አማኞች በህይወታቸው በገላቲያ 5፤22-23 ውስጥ የተዘረዘሩትን ሊኖራቸው ይገባቸዋል፡፡ ጳውሎስ ወዲያውኑ እኛ በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደዳንን ከነገረን በኃላ መልካም ሥራዎችን ለማድረግ እንደተፈጠርን ይነግረናል፡፡ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፤10) ልክ ያዕቆብ ባዳረገው የህይወት ለውጥ ያህል ጳውሎስ ይጠብቃል፤”ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤አሮጌው ነገር አልፏል፤እነሆ አዲስ ሆኖአል” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፤17) ድነትን በተመለከተ ያዕቆብ እና ጳውሎስ በትምህርታቸው አይቀዋወሙም፡፡ ተመሳሳይ ጉዳዮችን በተለያዩ አመለካከቶች ያያሉ፡፡ ጳውሎስ መጽደቅ በእምነት ብቻ እንደሆነ በቀላሉ ያን ሲያጎላ ያዕቆብ ደግሞ በክርስቶስ የሆነ እውነተኛ እምነት በጎ ሥራዎችን በመፍጠሩ እውነታ ላይ ያጠብቃል፡፡
English
መዳን በእምነት ብቻ ነው ወይስ በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ነው?