settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በእግዚአብሔር ማመንና ሳይንስ ይጋጫልን?

መልስ፤


ሳይንስ ‹‹የመገንዘብ የመለየት የመግለጽ የመመርመር በተግባር ፈትኖ ለይቶ የማወቅና ሃሳብ ትንታኔዎችን የመስጠት ክንውን ነው፡፡ ሳይንስ ሰዎች ለተፈጥሮአዊው አለም ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ሊጠቀሙበት የሚችሉበት መንገድ ነው፡፡ በመረራመር እወቀትን መፈለግ ነው፡፡ በቅድሚያ ሳይንስ የሰውን አስተሳሰብና እውቀት የደረሰበትን የሚገልጽ ነው፡፡ ሆኖም ክርስቲያኖች በሳይንስ ላይ የሚኖራቸው እምንት በእግዚአብሔር ላይ እንዳላን እምነት ሊሆን አይችልም፡፡ ፍጹም ተክክል የሆነውንና ያልሆነውን ለይተን እስካወቅን ድረስ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ማመንና ለሳይንስም ተገቢው አመለካከት ሊኖረን ይችላል፡፡

በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት በእምነት የሆነ ማመን ነው፡፡ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የደህንነት እምነት በቃሉ መመሪያን የመቀበል በመንፈስ ቅዱስ የምንመራበት እምነት አለን፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ሙሉ እና ፍጹም ነው፡፡ እምነታችንን በእግዚአብሔር ላይ እስካደረግን ድረስ ፍጽም በሆነ ሁሉን በሚችል ሁሉን በሚያውቅ በእግዚአብሔር እንታመናለን፡፡ በሳይንስ ላይ የሚኖረን እምነት ከአይምሮ እውቀት የሚበልጥ አይደለም፡፡ በሳይንስ ብዙ ትልልቅ ነገሮች ልናገኝ እንችላለን ግን ደግሞ ብዙ ስህተቶችንም ልንሰራ እንችላለንለ፡፡ እምነታችንን በሳይንስ ላይ ካደረግን ፍጹምነት ከሌለው ኃጢያተኛ ውሱን ሟች በሆነ ሰው ላይ የተደግፍን እንሆናለን፡፡ ሳይንስ በታሪክ ለዘመናት የተሳሳተባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፤ የመሬት ቅርጽ ፤ኃይል የተሞላ በረራ፤ ክትባት የደም ስለመስጠት እንዲሁም ስለ ዘር መባዛት፡፡ እግዚአብሔር ግን ተሳስቶ አያውቅም፡፡

እውነት የሚፈራው ነገር የለም ክርስቲያንም እውነተኛ ሳይንስን ምንም የሚፈራበት ምክንያት አይኖርም፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ይህን አለም እዳዋቀረው ሲያውቅ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ውስጥ ያለውን ድንቅ ስራ ያደንቃል፡፡ እወቀታችንን ማሳደግ በሽታን እንድንከላከል ከቸልተኝነት የተሳሳተ መረዳት እንዳይኖረን ይረዳናል፡፡ ሆኖም ሳይንቲስቶች እምነታቸውን በሰራን በእግዚአብሔር ከማመን ይልቅ በሰው አስተሳሰብ ላይ ሲያደርጉ አደጋ አለ፡፡ እነዚህ ሌሎች የተለየ ሃይማኖት ካላቸው ሰዎች የተለዩ አይደሉም በሰው ማመንን የመረጡና እምነታቸውንም ለመጠበቅ መረጃ የሚፈልጉ ናቸው፡፡

በቂ አመክንዮ መክንያት ያለቸው ተመራማሪ ሳይንቲስቶቸም በእግዚአብሔር ማመንን የሚቃወሙም ቢሆኑ ይህን አለም ለመረዳት ያለንን የመረዳት ውሱንነት ይቀበላሉ፡፡ እግዚአብሔርም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በሳይንስ ሊረጋገጥ ወይም ላይረጋገጥ እነደማይችል ይቀበላሉ፤ እንደበዙዎቹ የታወቁ አመለካከቶቻቸው ሊያረጋግጡም ላያረጋግጡም አይችሉም፡፡ ሳይንስ ማለት በገለልተኛ ሥርዓት እውነትን ብቻ መፈለግ እነጂ ሌላ ያለፈ አጀንዳ አይደለም፡፡ ሳይንስ በአብዛኛው በእግዚአብሔር መኖር እንዲሁም ስራውን ይደግፋል፡፡ መዝ 19፡1 ‹‹

ዘመናዊው ሳይንስ ስለአለም ብዙ የደረሰበት ነገር ስላለ ስለ ስነ ፍጥረጥ ብዙ መረጃ ማግኘት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ውስብስብ አስደናቂ ስለሆነው ስለ ዘረመል የማባዛት ምርመራ የተራቀቀና የተጠላለፈ የቁስ አካልና የኃይል ጥናት የኬሚስቲሪ ፈጹም የሆን ውህደት በዚህ ምድር ላይ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነትነት የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ ክርስቲያን እውነትን የሚፈልገውን ሳይንስ መቀበል ግን ደግሞ የሰውን እውቀት ከእግዚአብሔር በላይ የማድረግ ‹‹የሳይንስን ሹመት›› መቃወም አለበት፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በእግዚአብሔር ማመንና ሳይንስ ይጋጫልን?
© Copyright Got Questions Ministries