settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የክርስቲያን ጾም - መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መልስ፤


ቅዱስ ቃሉ ክርስቲያኖች እንዲጾሙ አያዝም። እግዚአብሔር አይፈልግም ወይም ክርስቲያኖችን አያዝም። በተመሳሳይ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ጾምን ይገልጻል፣ መልካም፣ አትራፊ፣ እና ጠቃሚ እንደሆነ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደመዘገበው አማኞች አስፈላጊ ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ይጾሙ ነበር (ሐዋ. 13፡2፣ 14፡23)። ጾምና ጸሎት ዘወትር አንድ ላይ ይያያዛሉ (ሉቃስ 2፡37፤ 5፡33)። በጣም አዘውትሮ፣ የጾም አትኩሮት ምግብ አለመውሰድ ነው። በአንጻሩም የጾም ዓላማ መሆን ያለበት ዓይንን ከዚህ ዓለም ነገሮች ነቅሎ ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ ነው። ጾም ለእግዚአብሔርና ለራሳችን የማቅረቢያ መንገድ ነው፣ ማለትም ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት የምር መሆኑን ያሳያል። ጾም በእግዚአብሔር ላይ አዲስ አስተሳሰብና የታደሰ እምነት እንዲኖረን ይረዳል።

ምንም እንኳ ጾም በቅዱስ ቃሉ ባመዛኙ ዘወትር ምግብ መጾም ቢሆንም፣ ሌሎችም የጾም መንገዶች አሉ። ማንኛውም ነገር ለጊዜው ከተተወ ቀልባችንን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ለማተኮር ከሆነ እንደ ጾም ይቆጠራል (1 ቆሮንቶስ 7፡1-5)። ጾም በተወሰነ ሰዓት መሆን ይኖርበታል፣ በተለይም ከምግብ መጾም ሲሆን። የተራዘመ ጊዜና ሰዓት ያለ ምግብ መሆን ሰውነትን ሊጎዳ ይችላል። ጾም ሥጋን ለመቅጣት በማሰብ አይደለም፣ ነገር ግን ቀልብን ወደ እግዚአብሔር መመለሻ እንጂ። እንዲሁም ጾም “የአመጋገብ ዘዴ” ተደርጎ መወሰድ አይኖርበትም። መጽሐፍ ቅዱሳዊው የጸሎት ዓላማ ክብደትን ለመቀነስ አይደለም፣ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር የጠለቀ ኅብረት ለማግኘት እንጂ። ማንም ሊጾም ይችላል፣ ነገር ግን አንዳንዶች ከምግብ ሊጾሙ አይችሉም (የስኳር ሕሙማን፣ ለምሳሌ)። ማንም ለጊዜው አንድን ነገር ሊተው ይችላል፣ ወደ እግዚአብሔር በተሻለ ለመቅረብ።

ከዚህ ዓለም ነገሮች ዓይኖቻችንን በመውሰድ፣ እጅግ ስኬታማ በሆነ መልኩ ቀልባችንን ወደ ክርስቶስ ማዞር እንችላለን። ጾም የፈለግነውን ያደርግልን ዘንድ እግዚአብሔርን የማግኛ መንገድ አይደለም። ጾም ይለውጠናል፣ እግዚአብሔር ሳይሆን። ጾም ከሌሎች በተሻለ መንፈሳዊ የምንሆንበት መንገድ አይደለም። ጾም መደረግ ያለበት በትሕትና መንፈስ እና ደስታ ባለው ሁኔታ ነው። ማቴዎስ 6፡16-18 ያውጃል፣ “ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።”

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የክርስቲያን ጾም - መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries