settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ፊሎኲ ሐረግ ምንድነው?

መልስ፤


ፊሎኲ ሐረግ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በተያያዘ በቤተ ክርስቲያን አወዛጋቢ ነበር አሁንም ነው። ጥያቄው “መንፈስ ቅዱስ የሚሰርጸው ከማነው፣ ከአብ ወይስ ከአብና ከወልድ?” filioque የሚለው ቃል ፍችው “እና ወልድ” ማለት ነው፣ በላቲን። እሱም የሚጠቀሰው “ፊሎኲ ሐረግ” በሚል ነው፣ ምክንያቱም “እና ወልድ” የሚለው ሐረግ፣ በኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ ላይ በመታከሉ፣ እሱም መንፈስ ቅዱስ ከአብ “እና ከወልድ” የሚሰርጽ መሆኑን የሚያመለክት። በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ውዝግብ ነበር፣ እሱም በሮማን ካቶሊክ እና በምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናት መካከል ወደ መከፋፈል ያደረሰ፣ በ1054 ዓ.ም። ሁለቱ አብያተ-ክርስቲያናት አሁንም ቢሆን በፊሎኲ ሐረግ ላይ ስምምነት የላቸውም።

ዮሐንስ 14፡26 ይነግረናል፣ “አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ …” ዮሐንስ 15፡26 ይነግረናል፣ “ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።” ደግሞም ዮሐንስ 14፡16 እና ፊሊጵስዩስ 1፡19 ተመልከቱ። እነዚህ ቅዱስ ቃሎች የሚያመለክቱት መንፈስ ከሁለቱም ከአብ እና ከወልድ ወጥቶ መላኩን ነው። የፊሎኲ ሐረግ ዋነኛ ጉዳይ የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት የማስከበር ፍላጎት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን ነው (ሐዋ. 5፡3-4)። ፊሎኲ ሐረግን አካልነት የሚቃወሙት እነርሱ የሚያምኑት መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ የሚወጣ በመሆኑ፣ ይህም መንፈስ ቅዱስ አብ እና ወልድን ”የሚያገለግል” ነው በሚል ነው። የፊሎኲ ሐረግን በዚህ አቋም የሚረዱ የሚያምኑት መንፈስ ቅዱስ ከሁለቱም ከአብ እና ከወልድ የሚወጣ መሆኑ መንፈስን ከአምላክ ጋር አያስተካክለውም፣ ከአብ እና ከወልድ ጋር በሚል ነው።

የፊሎኲ ሐረግ ውዝግብ በተመሳሳይ መልኩ የአምላክን አካላዊነት ገጽታም ያካትታል፣ ይሄውም ሙሉ ለሙሉ ፈጽሞ መረዳት የማንችለው። አምላክ የማይወሰነው ሕላዌ፣ ባጠቃላይ ውስን በሆነው የእኛ የሰው አእምሮ ሊደረስበት አይችልም። መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው፣ እሱም በእግዚአብሔር የኢየሱስ “ተተኪ” ይሆን ዘንድ ወደዚህ ዓለም ተልኳል። መንፈስ ቅዱስ በአብ ወይም በአብ እና በወልድ በየትኛው ነው የተላከው የሚለው ጥያቄ በሚያስት መልኩ ምላሽ ሊገኝ አይችልም፣ አልያም ፍጹም መሆን እንዳለበት። የፊሎኲ ሐረግ ውዝግብ አወዛጋቢ ሆኖ መቀጠሉ አይቀርም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ፊሎኲ ሐረግ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries