ጥያቄ፤
በእኔ ላይ ኃጢአት የሠሩትን እንዴት ይቅር ማለት እችላለሁ?
መልስ፤
እያንዳንዱ ስሕተት ሠርቷል፣ አስቀይሟል፣ እንዲሁም በተወሰነ ነጥብ ኃጢአት ሠርቷል። እነዚህን የመሳሰሉ መተላለፎች ሲኖሩ ክርስቲያኖች እንዴት ነው ምላሽ መስጠት የሚኖርባቸው? እንደ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይቅር ማለት አለብን። ኤፌሶን 4፡32 ያውጃል፣ “እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።” በተመሳሳይም፣ ቆላስይስ 3፡13 ያውጃል፣ “እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።” በሁለቱም ቅዱስ ቃሎች ላይ ቁልፉ፣ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለን እኛም ሌሎችን ይቅር ማለት እንዳለብን ነው። ለምን ይቅር እንላለን? ይቅር ስለተባልን!
ይቅርታ ማድረግ ቀላል የሚሆነው በኀዘንና በንስሐ እሱን ለመፈለግ ለጥየቃ ለሚመጡት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፣ ይቅር እንድንል፣ ያለ ምንም ሁኔታ፣ በእኛ ላይ በደል የፈጸሙትን። ሰውን ከልብ ይቅር አለማለት የሚያሳየው ክፉ ፍቃድን፣ ምሬትን፣ እና ቁጣን ሲሆን፣ ከእነዚህ አንዳቸውም የእውነተኛ ክርስቲያን ጠባይ አይደሉም። በጌታ ጸሎት፣ እግዚአብሔር በደላችንን ይቅር እንዲለን እንለምናለን፣ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል (ማቴዎስ 6፡12)። ኢየሱስ፣ ማቴዎስ 6፡14-15 ላይ ብሏል፣ “እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ካላችሁ፣ የሰማይ አባታችሁ ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን ሌሎችን ይቅር ለማለት እምቢ ብትሉ፣ አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።” በሌሎች የቅዱስ ቃሉ ክፍሎች ብርሃን፣ እነርሱም ስለ እግዚአብሔር ይቅርታ የሚናገሩ፣ ማቴዎስ 6፡14-15 በተሻለ መረዳት ያገኘው፣ የሚለው፣ ሌሎችን ይቅር ለማለት እምቢ የሚሉ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ይቅርታ በእውነት ያልተለማመዱ ናቸው።
ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት አንዱን ሳናከብር፣ በእርሱ ላይ ኃጢአት እንሠራለን። በሌላ ሰው ላይ በደል ስንፈጽም፣ ያንን ሰው ብቻ አይደለም የበደልነው፣ ግን ደግሞ እግዚአብሔርን እንጂ። እግዚአብሔር በደላችንን ሁሉ የቱን ያህል ይቅር እንዳለን ብንገነዘብ፣ ይሄንን ጸጋ ሌሎችን ለመከልከል መብት እንደሌለን እንገነዘባለን። እኛ በእግዚአብሔር ላይ በማይቆጠር መጠን በድለኛል፣ ማንም ሰው እኛ ላይ ከፈጸመው በደል ይልቅ። እግዚአብሔር ይህን ያህል ይቅር ካለን፣ ሌሎችን በጥቂቱ ይቅር ለማለት እንዴት እምቢ እንላለን? የኢየሱስ ምሳሌ ማቴዎስ 18፡23-35 ላይ የዚህ እውነት ኃይለኛ መግለጫ ነው። እግዚአብሔር ተስፋ ሰጥቶናል፣ ይቅርታን ለመጠየቅ ወደ እርሱ ስንመጣ፣ እሱ በነጻ ይሰጠናል (1 ዮሐንስ 1፡9)። ይቅርታ የምናደርግበት ስፋቱ ወሰን የለውም፣ በተመሳሳይ መንገድ የእግዚአብሔር ይቅርታ ወሰን የለውም (ሉቃስ 17፡3-4)።
English
በእኔ ላይ ኃጢአት የሠሩትን እንዴት ይቅር ማለት እችላለሁ?