settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ቁማር መጫወት ኃጥአት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ ቁማር ስለ መጫወት ምን ይላል?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ቁማር መጫወትን፤መወራረድን ወይም ሎቶሪን ለይቶ አያወግዝም፡፡ ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን ከመውደድ እንድንርቅ ያስጠነቅቀናል (1ኛ ጢሞቴዎስ 6፤10፤ወደ ዕብራውያን ሰዎች 13፤5)፡፡ በተጨማሪም ቅዱሳን መጽሐፍትም “በአቋራጭ ፈጥኖ ከመበልጸግ” ከምናደርገው ሙከራዎች እንድንርቅ ያደፋፍረናል (መጽሐፈ ምሳሌ 13፤11, 23፤5፤መጽሐፈ መክብብ 5፤10):: ቁማር መጫወት ያለ ጥርጥር ገንዘብን በመውደድ እና ያለ ምንም ጥያቄ በአቋራጭ እና በቀላል ብልጽግና ሰዎችን ይፈትናል፡፡

ቁማር መጫወት ምን ስህተት አለው? ቁማር መጫወት አስቸጋሪ ጉዳይ ነው ምክንያቱም በመጠኑ እና አልፎ አልፎ የሚደረግ ከሆነ ገንዘብ ማባከን ነው፤የግድ ግን ክፉ አይደለም፡፡ ሰዎች በሁሉም ዓይነት ተግባሮች ላይ ገንዘብ ያባክናሉ፡፡ ቁማር መጫወት ፊልም በማየት (በብዙ መልኩ)፤ከልክ በላይ ውድ የሆኑ ምግቦችን በመብላት፤ወይም ዋጋ የማያወጡ ነገሮችን በመግዛት ከሚባክነው ገንዘብ አይተናነስም፡፡ በተመሳሳይ ገንዘብ በሌሎች ነገሮች የመባከኑ እውነታ ቁማር ለመጫወት ምክንያት አይሆንም፡፡ ገንዘብ መባከን የለበትም፡፡ ትርፍ ገንዘብ ለወደፊት ጉዳዮች መጠራቀም ወይም ለጌታ ሥራ መሠጠት ይኖርበታል እንጂ ለቁማር መሆን የለበትም፡፡

ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ቁማር መጫወትን በግልጽ ባይጠቅስም “የገድ” ወይም “የዕድል” ክስተቶችን ይጠቅሳል:: እንደ ምሳሌ በሚሰዋው ፍዮል እና በሚጣለው መካከል ለመለየት ዕጣዎችን መጣል በዘሌዋውያን ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ኢያሱ ለተለያዩ ነገዶች የመሬት ድርሻ ለመወሰን ዕጣዎችን ጥሏል፡፡ ነህምያ በኢየሩሳሌም ቅጥሮች ውስጥ ማን መኖር እንደሚገባው ለመወሰን ዕጣዎችን ጥላል፡፡ ሐዋሪያቶች የይሁዳን ምትክ ለመወሰን ዕጣ ጥለዋል፡፡ መጽሐፈ ምሳሌ 16፤33፤ “ዕጣ በጕያ ይጣላል መደብዋ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።” ይላል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ካርታዎች እና ሎቶሪዎች ምን ይላል? የቁማር ማጫዎቻ ቦታዎች በተቻላቸው መጠን በብዙ የገንዘብ መጠን ችግር ላይ ሊጥሏቸው ቁማርተኞችን ለመሳብ ሁሉንም ዓይነት የመገበያያ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ስካርን የሚያደፋፍሩ እና በዚያም በጎ የሆነውን ውሳኔ የመወሰን አቅማቸውን የሚቀንሱ ርካሽ ወይም ነጻ የሚያሰክሩ መጠጦችን ይጋብዛሉ፡፡ በቁማር ማጫዎቻ ቦታዎች ለጥቂት ጊዜ እና ባዶ ለሆኑ ፌሽታዎች በስተቀር ሁሉም ነገር ትላልቅ ድምር ያላቸውን ገንዘብ ለመውሰድ እና በምላሹ ምንም ላለመስጠት በደንብ የተመቻቸ ነው፡፡ ሎቶሪዎች ራሳቸውን ለትምህርት እና/ወይም የማህበረሰብ መርሐ-ግብሮችን መርጃ መንገድ እንደሆኑ ለማሳየት ይጥራሉ፡፡ ሆኖም ግን የሎቶሪ ተሳታፊዎች ብዙውን ጊዜ በሎቶሪ ቲኬቶች ላይ ገንዘብ ወጪ የማድረግ አቅሙ የሌላቸው ሰዎች እንደሆኑ ጥናቶች ያን ያሳያሉ፡፡ ለተጨነቁት “በአቋራጭ ፈጥኖ የመበልጸግ” ፍላጎትን መቃወም እጅግ ትልቅ ፈተና ነው፡፡ የማሸነፍ ዕድሎቻቸው እጅግ በጣም አናሳ ነው፤ያም የብዙ ሰዎችን ህይወት ለጥፋት ይዳርጋል፡፡

ሎቶ ወይም ሎቶሪ በመጫወት የሚቀጥሉት እግዚአብሔርን ሊያስደስት ይችላል? ብዙ ሰዎች ሎቶሪዎችን ወይም ቁማር በመጫወት በዚህም ለቤተክርስቲያን ወይም ለአንዳንድ በጎ ተግባራት ገንዘብ እንደሚሰጡ ይናገራሉ፡፡ ይኸ ምናልባት መልካም ምክንያት ቢሆንም እውነታው ጥቂቶች ቁማር በመጫወት ያገኙትን ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ይጠቀማሉ፡፡ እጅግ ብዙ የሆኑቱ የሎቶሪ አሸናፊዎች እንዲያውም ዕጣውን ካሸነፉ ከጥቂት ዓመታት በኃላ በፊት ከነበሩበት ይልቅ በጣም በከፋ የገንዘብ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ጥናቶች ያን ያሳያሉ፡፡ ካሉም ጥቂቶች በእውነት ገንዘቡን ለበጎ ተግባራት ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪ እግዚአብሔር በዓለም ያለውን የእርሱን ተልዕኮ እንድንደግፍ አይፈልግም፡፡ መጽሐፈ ምሳሌ 13፤11 “በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።” ይላል፡፡ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው እናም በእውነተኛ መንገድ ለቤተክርስቲያን ፍላጎቶች ይለግሳል፡፡ እግዚአብሔር የተሰጡ የዕጾች ገንዘብ ወይም በባንክ ዘራፊዎች የተሰረቀውን ገንዘብ በመቀበል ይከብራል? በእርግጥ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ከድህነት ወደ ብልጽግና በሚደረግ ፈተና “የተሰረቀውን” ገንዘብ አይፈልገውም፤አይመኘውምም፡፡

1ኛ ጢሞቴዎስ 6፤10 “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።” ብሎ ይነግረናል፡፡ ወደ ዕብራውያን ሰዎች 13፤5 “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤” ብሎ ያውጃል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 6፤24፤ “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።” ይላል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ቁማር መጫወት ኃጥአት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ ቁማር ስለ መጫወት ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries