settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኖህ የጥፋት ውሃ በአንድ ቦታ የተከናወነ ወይስ አለማቀፋዊ?

መልስ፤


የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የጥፋት ውሃው አለማቀፋዊ እንደነበር በግልጽ ያስነብባሉ፡፡ ዘፍ 7:11 እንደህ ይላል ‹‹በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፥ የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ›› ዘፍ 1:6-7 እና 2፡6 የሚነግረን ከጥፋት ውሃው የነበረው የአየር ሁኔታ እኛ ዛሬ ከምናውቀው ፈጽሞ የተለየ እንደነበረ ነው፡፡ በዚህ ቃል መሰረት እና ሌሎች የሚጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንዲሚገልጹልን በምክንያታዊነት ልንሰጥ የምንችለው መላምት በአንድ ወቅት ምድር በውሃ ተሸፍና እንደነበር ነው፡፡ ይህ ሽፋን ተኖ ሊሆን ይችላል ወይንም እንደ ሳተርን የበረዶ ቀለበት የተሱሩ ቀለበቶች ሊኖረው ይችላል፡፡ ይህ በስር የሚያልፍ የውሃ ሽፋን ጋር የተቀላቀለ ወደ ምድር የተለቀቀ (ዘፍ 2:6) አለም አቀፍ የውሃ መላትን አምጥቶ ይሆናል፡፡

የውሃውን መጠን በጣም በግልጽ የሚያሳዩ ክፍሎች ዘፍ 7:19-23. ወሃውን በሚመለከት ‹‹ ውኃውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሸነፈ ከሰማይም በታች ያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ።ውኃው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ።በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቀሰው ሁሉ፥ ወፉም፥ እንስሳውም፥ አራዊቱም፥ በምድር ላይ የሚርመሰመሰው ተንቀሳቃሹም ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ።በየብስ የነበረው በአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ።በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።››

ከላይ ባየነው ክፍል ሀሉም የሚል ቃል ብቻ አይደለም በመደጋገም የምናገኘው ግን ‹‹ውኃውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሸነፈ ከሰማይም በታች ያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ›› ‹‹ውኃው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ።›› ይህ አገላለጽ በግልጽ የሚያስቀምጥልን አለም አቀፋዊ ውሃ ምድርን ሁሉ ሸፍኖአል፡፡ እንዲሁም ውሃው በአንድ አካባቢ ብቻ ከነበረ እግዚአብሔር ለኖህ መርከብ እንዲሰራ ከሚነግረው ይልቅ ለምን በቀላሉ እንዲሰደድ አልነገረውም፡፡ ለምን መርከቡ በጣም ተልቅ ሁሉንም በምድር ላይ ያሉ የእንስሶቸች ዘር ሁሉ የሚይዝ እንዲሆን አዘዘው፡፡ ወሃው አለም አቀፋዊ ባይሆን መርከቡ አያስፈልግም ነበር፡፡

ጴጥሮስ የጥፋት ውሃውን አለማቀፋዊነት ገልጾአል 2 ጴጥ 3፡6-7፣ ሲገልጽም ‹‹በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ፤አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።›› ጴጥሮስ በዚህ ክፍል በዓለም ሁሉ ላይ ሊሆን ያለውን ፍርድ በኖህ ዘመን ጋር ከነበረው የጥፋት ውሃ ጋር ያነጻጽርና በዚያን ጊዜ የነበረው አለም በውሃ ጠፋ ይለናል፡፡ (ኢሳ 54:9; 1 ጴጥ 3:20; 2 ጴጥ 2:5; ዕብ 11:7).

በመጨረሻ ኢየሱስ ክርስቶስ በአለም አቀፋዊ የውሃ ጠፋት በማመን ወደ ፊት እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በዓለም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ምሳሌ አድርጎ ወስዶታል፡፡ (ማቲ 24:37-39; ሉቃ 17:26-27).

ሌሎች ብዙ ተጨማሪ ከመጸሐፍ ቅዱስ ውጪ እንደ ጥፋቱ ውሃ ያሉ አለማቀፋዊ አደጋዎች ማረጋገጫ የሚሰጡን አሉ፡፡ እጅግ ሰፊ የሆኑ ቅሪተ አካል መቃብሮች በለተያዩ አህጉሮችና እጅግ ብዙ የማዕድን ከምችት በተራራ ጫፍ ላይ በዓለም ዙሪያ ተገኝተዋል፡፡ አንዳን በአለም ዙሪያ ያሉ ባህሎች በተወሰነ መልኩ የጥፋት ውሃ መግለጫ አላቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ መረጃዎች እና ከእነዚህም ወጪ የሆኑ ሌሎች ብዙ መረጃዎች የጠፋት ውሃ አለማቀፋዊነት ማረጋገጫ ናቸው፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኖህ የጥፋት ውሃ በአንድ ቦታ የተከናወነ ወይስ አለማቀፋዊ?
© Copyright Got Questions Ministries