settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ወደ ሰማይ መሄድ እንዴት ስለ ዘለአለም መድረሻዬ እርግጠኛ ልሆን የምችለው?

መልስ፤


ተጋፈጠው፡፡ ወደ ዘለአለም ህይወት የምንገባበት ጊዜ ከምናስበው ይልቅ ቅርብ ነው፡፡ ከምንዘጋጅበት ጊዜ ጀምሮ ይህን እውነት ማወቅ አለብን፤ ሁሉም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ወደ ሰማይ አይሄድም፡፡ እንዴት ነው ወደ ሰማይ እንደምንሄድ እርግጠኛ ልንሆን የምንችለው? ከ2000 ዓመት በፊት ጴጥሮስና ዮሐንስ የኢየሱስን ወንጌል ለህዝብ በኢየሩሳሌም ይሰብኩ ነበር፡፡ ጴጥሮስ ትልቅ መሰረት ያለው ቃል አሁን ያለንበትን ዘመን እንኳ ሊያንቀጠቅጥ የሚችል ነገር ተናገረ፡ ‹‹ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።›› ሥራ 4፡12

አሁን እንደዚያን ጊዜ ሥረ 4፡12 በፖለቲካዊ መልኩ ትክክል አይደለም፡፡ አሁን እንዲህ ማለት የተለመደ ነወ፡ ‹‹ሁለም ሰው ወደ ሰማይ ይሄዳል›› ‹‹ሁሉም መንገዶች ወደ ሰማይ ይወስዳሉ›› በዙዎች አሉ ኢየሱስ ክርስቶ ሳይኖራቸው ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ የሚያስቡ፡፡ ክብሩን ይፈልጉታል ነገር ግን ስለ መስቀል በማሰብ መጨነቅ አይፈልጉም በዚያ ላይ የሞተውን አያከብሩትም፡፡ ብዙዎች ወደ ሰማይ የሚያደርስ ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ እንደሆነ ማመን አይፈልጉም፤ ሌላ መንገድ ለማግኘት ወስነዋል፡፡ ኢየሱስ ግን ሌላ መንገድ እንደማይኖር አስጣንቅቆናል ይህን እውነት መቃወም በሲኦል ለዘላላም ጥፋት ነው የሚያስከትለው፡፡ ነገሮናል፡- ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።›› (ዮሐ 3፡16)፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ውደ ሰማይ ለመሄድ ቁልፍ ነው፡፡

አንዳንዶች ይከራከራሉ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ለመሄድ ያዛጋጀው መንገድ አንድ ነው ብሎ ማሰብ የአዕሞሮ ጠባብነት ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ግን በግልጽ በሰው ልጆች የአመጽ እይታ ሁለምንም መንገድ እንግዚእብሔር ወደ ሰማይ እንደንገባበት አዘጋጅቶታል ማለት ለእርሱ እጅግ ጠባብነት ነው፡፡ ፍርድ ይገባናል ነገር ግን እንዳንጣፋ እግዚአብሔር አንድ ለጁን ላከና ለኃጢያታችን እንዲሞት አደረገው፡፡ ለአንዳንዶች ይን ጠባብነት በመስልም እውነት ነው፡፡ መልካሙ ዜና ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተነስቶአል፤ ወደ ሰማይ የሚሄዴ ይህን ወንጌል ባእምነት የተቀበሉ ናቸው፡፡

ብዙ ሰዎች ዛሬ ውሃ አጥቦ ሊወስደው እንደሚችል አይነት ደካማ የሆነ የንሰሐን አስፈላጊነተ የጣለ ወንጌል ይዘው ጠፍተዋል፡፡ ፍቅር የሆነ የማይፈርድ አግዚአብሔር ማምለክ ይፈልጋሉ፤ እግዚአብሔር ስለ ሃጢያት ምንም ግድ የሌለው በህይወታቸው ውስጥ ምንም አይነት ለውጥ እንዲያደርጉ የማይፈልግ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ እነደዚህ ሊሉ ይችላሉ ‹‹የኔ እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ሲኦል ሊልክ አይችልም››፡፡ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰማይ ከተናገረው በላይ ስለ ሲኦል ተናግሮአል እራሱንም ወደ ሰማይ ለመግባት ብቸኛ አዳኝ እንደሆነ ተናግሮአል፡- ‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ›› (ዮሐ 14:6)፡፡

ማን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ ይችላል? ወደ ሰማይ መግባቴን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ የሆነ ልዩነትን ዘላለማዊ ሕይወት ባላቸው እና በሌላቸው መካከል አስቀምጦአል፡ ‹‹ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።›› (1ዮሐ 5፡12)፡፡ ኢየሱስን ለኃጢያታቸው መስዋዕት አደርገው የተቀበሉ እና በትንሳኤው ያመኑ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቃወሙት አይሄዱም‹‹በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።›› (ዮሐ 3:18).

ኢየሱስ ክርስቶስነ አዳኛቸው አድርገው ለተቀበሉ ሰማይ አስደናቂ ስፍራ ይሆንላቸዋል ሲኦል ደግሞ ለተቃወሙት እጅግ የከፋ ስፍራ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን በትኩረት ደጋግሞ ማንበብ ሳይስፈልገው መስመሩ ተሰምሮአል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ሰማይ ለመግባት መንገዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ይላል፡፡ የኢየሱስን ትዕዛዝ እንከተል ‹‹በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።››(ማቲ 7:13?14).

ወደ ሰማይ መግባት የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው፡፡ ያመኑ እንደሚገቡ እርግጠኛ ነው፡፡ በኢየሱስ ታምናለህ?

English


ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
ወደ ሰማይ መሄድ እንዴት ስለ ዘለአለም መድረሻዬ እርግጠኛ ልሆን የምችለው?
© Copyright Got Questions Ministries