ጥያቄ፤
ስለ መልካም ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
መልስ፤
ቤተሰብ መመስረት ከባድ ትግል ያለው ድፍረት የሚጠይቅ ሊሆን ይችላል፤ ይሁን እንጂ በተመሳሳይ ሁኔታ ከምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በበለጠ መልሶ ዋጋ ሊከፍለን የሚችልና የተሻለው ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች እንዲሆኑ በትክክል ማሳደግ ስለምንችልበት መንገድ በዙ የሚለው ትልልቅ ሃሳብ አለው፡፡ ማድረግ የሚኖርብን የመጀመሪያው ትልቁ ነገር የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር ነው፡፡
እግዚአብሔርን ከመውደድ ጋርና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመጠበቅ ባለን መሰጠት ምሳሌ መሆን፤ በዘዳግም 6፡7-9 ያለውን ትኩረት በመስጠት ለጆቻችንም እንዲሁ እንዲያደርጉ ማስተማር አለብን፡፡ ይህ ከፍል ትኩረት የሚያደርገው እንደዚ ያለ መመሪያ ያለማቋረጥ ስለሚቀጥልበት ተፍጥሮአዊ ሂደት ነው፡፡ ሁል ጊዜ በቤት ውስጥ በመንግድ ላይ በምሽት በጠዋት መደረግ አለበት፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት የቤቶቻችን መሰረት መሆን አለበት፡፡ እነዚህን ትዕዛዛት መርሆች በመከተል እግዚአብሔርን ማምለክ የማይቋረጥ እሁድና የማታ ጸሎት እየጠበቅን የምናደርገው እንዳልሆነ ልጆቻችንን እናስተምራለን፡፡
እንዲሁም ለጆቻችን እኛን ቤተሰቦቻቸውን በማየት የጠለቀ እውነት በቀጥታ ይማራሉ፡፡ ለዚህም ነው በምናደርገው ሁሉ መጠንቀቅ የሚኖርብን፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላካችን መመሪያን እንደሰጠን ማመን እውቅና መስጠት ያስፈልገናል፡፡ ባልና ሚስት እርስ በእርሳችን መገዛትና መከባበር አለብን፡፡ (ኤፌ 5፤21). በተመሳሳይ ሁኔታ እግዚአብሔር የስልጣን ተወረድ ስርዓትን ሰጥቶናል፡፡ ‹‹ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።›› (1ቆር 11:3). እንደምናወቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር የፍርሃትና የዝቅተኝነት ስሜት መገዛተ የለውም፤ እንዱሁ ሚስትም ለባሏ እንዱህ አይነት የዝቅተኝነት ስሜት መገዛት ሊኖራት አያስፈልግም፡፡ በሌላ መልኩ እግዚአብሔር ለሥልጣን መገዛት ሳይኖር ስርዓት ሊመጣ እንደማይችል እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ የባል ሃላፊነት የቤቱ ራስ እንደመሆኑ ሚስቱን ኢየሱስ ክርስቶስ በተክርስቲያንን እንደወደደና እና ራሱን እንደሰጠ የራሱን ሥጋ እንደሚወድ መውደድ ነው፡፡ (ኤፌ 5፡25-29).
በፍቅር ለሚመራት ባል ሚስት ራሷን በማስግዛት ምላሽ መስጠት ከባድ አይሆንባትም (ኤፌ 5:24; ቆላ 3:18). የሚስት ቀዳሚ ሃለፊነቷ ባሏን መውደድ ማክበር በፍቅርና በንጽህና መኖር ቤቷን መንከባከብ ነው፡፡ (ቲቶ 2:4-5). ሚስቶች ከባል ይልቅ እንክብካቤን የሚፈልጉ ናቸው ምክንያቱም የልጆቻቸው ቀዳሚ ተንከባካቢ ጠባቂ እንዲሆኑ ስለተሰሩ ነው፡፡
መመሪያን መስጠት እና መቅጣት በቤተሰብ ውስጥ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ምሳ 13:24 ‹‹ እንዲህ ይላል በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጻዋል።›› ዲሲፕሊን ቅጣትን ሳይቀበሉ ያደጉ ልጆች አስፈላጊ እና ጠቃሚ እንዳልሆኑ የሚሰማቸው ይሆናሉ፡፡ ራስን መግዛትና አቅጣጫ የሌላቸው ባደጉም ጊዜ እግዚአብሔርነ ጨምሮ ለየትኛውም አይነት ስልጣን ዝቅተኛ ግምት ያላቸው ወይንም ደግሞ አመጸኞችና አክብሮት የሌላቸው ይሆናሉ፡፡ ‹‹ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፥ መሞቱንም አትሻ።››(ምሳ 19:18). በተመሳሳይ ሁኔታ ቅጣት ከፍቅር ጋር ሚዛኑን ጠብቆ መደረግ አለበት ይህ ካልሆን ልጆች መራሮች ተስፋ የቆረጡ አመጸኛ ሆነው ያድጋሉ፡፡ (ቆላ 3:21). እግዚአብሔር ቅጣት በጊዜው እንደሚያም ያውቃል(ዕብ 12:11), ግን በፍቅር ከሆነ መመሪያ ጋር ሲሆን ለልጆች አስገራሚ የሆነ ጥቅምን አለው፡፡‹‹እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።›› (ኤፌ 6:4).
ልጆች በወጣትነታቸው በቤተሰብና በቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ያለማቋረጥ በመሳተፍ በእግዚአብሔር ቃል በምታምን ቤተክርስቲያን (ዕብ 10:25), አንተ ቃሉን ስታጠና እንዲያዩ ፍቀድላቸው፤ እንዲሁም ከእነርሱ ጋርም አጥና፡፡ እነርሱ ባሉበት ቃሉን ተነጋገሩ በየቀኑ ስለ እግዚአብሔር ክብር አስተምራቸው፡፡ ‹‹ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።›› (ምሳ 22:6). መልካም ቤተሰብ ማለት ያንተን ፈለግ የሚከተሉ እግዚአብሔርን የሚያመልኩና የሚታዘዙ ልጆችን ማፍራት ነው፡፡
English
ስለ መልካም ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?