settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መንፈስ ቅዱስን ማሳዘን/ማጥፋት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


“ማጥፋት” የሚለው ቃል በቅዱስ ቃሉ ጥቅም ላይ ሲውል፣ የሚናገረው እሳትን ስለ ማጥፋት ነው። አማኞች የእምነትን ጋሻ ሲያነሡ፣ እንደ እግዚአብሔር የጦር ዕቃቸው (ኤፌሶን 6፡16)፣ እነርሱ የሰይጣንን የሚንበለበሉ ፍላጻዎች ኃይል ያጠፋሉ። ክርስቶስ ገሃነምን የገለጸው እሳቱ “እንደማይጠፋበት” ስፍራ ነው (ማርቆስ 9:44፣ 46፣ 48)። እንደዚያው በሆነ መልኩ፣ መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ላይ የሚያድር እሳት ነው። እሱ ራሱን ለመግለጽ ይሻል፣ በእኛ ድርጊቶችና ዝንባሌዎች። አማኞች በድርጊታችን መንፈስ ቅዱስ እንዲታይ ካልፈቀድን፣ እኛም ስህተት መሆኑን እያወቅን ስናደርግ፣ መንፈስን እንጫነዋለን ወይም እናጠፋዋለን። መንፈስ ቅዱስ ራሱን ይገልጽ ዘንድ አንፈቅድለትም፣ እሱ በሚፈልገው መንገድ።

መንፈስን ማሳዘን የሚለውን ለመረዳት፣ በቅድሚያ ይህ መንፈስ አካልን እንደሚላበስ እንደሚያመለክት መረዳት ይገባናል። አካል ያለው ነው ሊያዝን የሚችለው፤ ስለዚህ፣ መንፈስ መለኮታዊ አካል መሆን ይገባዋል፣ ይህ ስሜት እንዲኖረው። አንድ ጊዜ ይሄንን ከተረዳን፣ እንዴት እንደሚያዝን በተሻለ እንረዳለን፣ እኛም ደግሞ በዋነኛነት በማዘናችን ምክንያት። ኤፌሶን 4፡30 መንፈስን ማሳዘን እንደሌለብን ይነግረናል። መንፈስን የምሳዝነው እንደ ጣኦት አምላኪዎች ስንኖር ነው (4:17-19)፣ በመዋሸት (4:25)፣ በመናደድ (4:26-27)፣ በመስረቅ (4:28)፣ በመርገም (4:29)፣ በመራርነት (4:31)፣ምሕረት የለሽ በመሆን (4:32)፣እና አመንዝራ በመሆን (5:3-5)። መንፈስን ማሳዘን ማለት በኃጢአተኝነት መልኩ ድርጊትን መፈጸም ነው፣ በሐሳብ ብቻ ቢሆን ወይም በሁለቱም በሐሳብና በድርጊት።

ሁለቱም መንፈስን ማጥፋት እና ማሳዘን በውጤታቸው ተመሳሳይ ናቸው። ሁለቱም መልካም የሆነውን የሕይወት ስልት ይጎትታሉ። ሁለቱም የሚከሰቱት/የሚሆኑት አማኙ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሲያደርግና የገዛ ራሱን ወይም ራሷን ዓለማዊ ፍላጎቶች ሲከተሉ ነው። ለመከተል ብቸኛው ትክክለኛ መንገድ፣ አማኙን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው መንገድና ንጽሕና ነው፣ እናም በተጨማሪ ከዓለምና ከኃጢአት መራቅ ነው። እንድናዝን እንደማንፈልግ ሁሉ፣ እናም መልካም የሆነው ለማጥፋት እንደማንፈልግ ሁሉ— እንደዚሁ መንፈስ ቅዱስን ማሳዘንም ሆነ ማጥፋት አይኖርብንም፣ የእሱን አመራር ከመከተል አሻፈረኝ በማለት።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መንፈስ ቅዱስን ማሳዘን/ማጥፋት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries