settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኅብረት ጸሎት ጠቃሚ ነውን? የኅብረት ጸሎት፣ ብቻውን ከሚጸልይ ከአንድ ግለሰብ ጸሎት ይልቅ ኃይለኛ ነውን?

መልስ፤


የኅብረት ጸሎት የቤተ-ክርስቲያን ሕይወት ጠቃሚ ክፍል ነው፣ ከአምልኮ ጋር፣ ሁነኛ ዶክትሪን፣ የአብሮነት ጊዜ፣ እና ኅብረት። የጥንቷ ቤተ-ክርስቲያን በመደበኛንት ትገናኝ ነበር፣ የሐዋርያትን ዶክትሪን ለመማር፣ ለቅዱስ ቍርባን፣ እና አብሮ ለመጸለይ (ሐዋ. 2፡42)። ከሌሎች አማኞች ጋር አብረን በምንጸልይበት ሰዓት፣ ውጤቱ እጅግ ጥሩ ይሆናል። የኅብረት ጸሎት ያንጸናል አንድም ያደርገናል እምነታችንን በምንካፈልበት ሰዓት። ያው መንፈስ ቅዱስ፣ እሱም በእያንዳንዱ አማኝ ላይ የሚያድረው ልባችን እንዲደሰት ያደርጋል፣ ለጌታ አዳኛችን ምስጋና ሲቀርብ ስንሰማ፣ አንድ ላይ አብረን በመሆናችን፣ በሕይወት ውስጥ የትም ስፍራ በማይገኘው የተለየ ወዳጃዊ መተሳሰር።

ከሕይወት ሸክም ጋር ለብቻቸው ለሚታገሉ ለእነርሱ፣ ሌሎችን ማዳመጥ ወደ ጸጋው ዙፋን ከፍ ሊያደርጋቸው ይችላል፣ ታላቅ ማበረታቻ ይሆናቸዋልም። እሱም ደግሞ በውስጣችን ፍቅርንና ለሌሎች ማሰብን ሊያዳብር ይችላል፣ ስለ እነርሱ ስንማልድ። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የኅብረት ጸሎት የግለሰቦች የልብ ነጸብራቅ ብቻ ይሆናል፣ ለሚሳተፉት። ወደ እግዚአብሔር መምጣት ያለብን በትሕትና ነው (ያዕቆብ 4፡10)፣ በእውነት (መዝሙር 145፡18)፣ በመታዘዝ (1 ዮሐንስ 3፡21-22)፣ በምስጋና (ፊሊጵስዩስ 4፡6) እና በመተማመን (ዕብራውያን 4፡16)። በሚያሳዝን መልኩ፣ የኅብረት ጸሎት፣ ቃላቸው ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ሳይሆን ለሚያደምጧቸው የሆነ ሰዎች መድረክ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ይህንን አመል አስጠንቅቋል፣ ማቴዎስ 6፡5-8 ላይ፣ እኛን የታይታ፣ የጸሎት ርዝማኔ፣ ወይም በጸሎታችን ግብዝ እንዳንሆን፣ ግን በገዛ ራሳችን ክፍል በምሥጢር እንድንጸልይ፣ የግብዝነት ጸሎትን ፈተና ለማስወገድ።

በቅዱስ ቃሉ የኅብረት ጸሎት ከግል ጸሎት ይልቅ “የተሻለ ኃይለኛ” መሆኑን የሚያሳይ ምንም ሐሳብ የለም፣ የእግዚአብሔርን እጅ በማንቀሳቀስ ረገድ። ከዚህም ባለፈ በርካታ ክርስቲያኖች ጸሎትን የሚያስተያዩት “ከእግዚአብሔር ነገሮችን ማግኘት” እና የቡድን ጸሎት ደግሞ ባመዛኙ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ዝርዝር ማሰሚያ አጋጣሚዎች ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ጸሎት፣ ሆኖም፣ ባለብዙ ገጽታ ነው፣ መሻትን ሁሉ አጠቃሎ በማምጣት፣ ወደ ቅዱሱ፣ ፍጹሙ፣ እና ጻድቁ አምላክ የቀረበ ግንኙነት መግባት ነው። እንዲህ ያለው አምላክ ጆሮውን ወደ ፍጡራኑ ሲያዘነብል፣ ለምስጋናና አምልኮ ምክንያት ይሆናል፣ ተትረፍርፎ እንዲገኝ (መዝሙር 27፡4፤ 63፡1-8)፣ ከልብ የሆነ መመለስንና መናዘዝን ይፈጥራል (መዝሙር 51፤ ሉቃስ 18፡9-14)፣ የተጥለቀለቀ አድናቆትንና ምስጋና ማቅረብን ያመነጫል (ፊሊጵስዩስ 4፡6፤ ቆላስይስ 1፡12)፣ ለሌሎች የሚሆን ትሕትናን የተላበሰ ጥያቄ ማቅረብን ይፈጥራል (2 ተሰሎንቄ 1፡11፤ 2፡16)።

እንግዲያውስ ጸሎት፣ የእሱን ዕቅድ ለማምጣት ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር ነው፣ እሱን ወደ እኛ ፍቃድ ለማዘንበል መሞከር ሳይሆን። የገዛ ራሳችንን ፍቃድ ትተን፣ እኛ ከምናውቀው በላይ በላቀ ሁኔታ የእኛን ሁኔታ ለሚያውቀው ለአንዱ በመገዛት፣ እንዲሁም እሱ “ከመጠየቃችሁ በፊት የሚያስፈልጋችሁን የሚያውቅ” (ማቴዎስ 6፡8)፣ ጸሎታችን እጅግ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ይደርሳል። ለመለኮታዊ ፍቃድ በመገዛት የሚቀርብ ጸሎት፣ ዘወትር በመልካም ሁኔታ ይመለሳል፣ በአንድ ሰውም ሆነ በሺህ ሰው ቢቀርብ።

የኅብረት ጸሎት የእግዚአብሔርን እጅ ለማንቀሳቀስ የተሻለ ነው የሚለው ሐሳብ ባመዛኙ የመጣው ማቴዎስ 18፡19-20ን አላግባብ በመተርጎም ነው፣ “ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።” እነዚህ ቁጥሮች የሚመጡት ከትልቅ ምንባብ ነው፣ ኃጢአት የሠራ አባልን ቤተ-ክርስቲያን በምን መልኩ ሥርዓት እንደምታስይዝ የሚገልጸው ደንብ። እሱንም የሚተረጉሙት ለአማኞች ክፍት የሆነ የባንክ ማዘዣ ሰጥቶ፣ እግዚአብሔርን የፈቀዱትን ነገር ለመጠየቅ እንደተስማሙ፣ ምንም ያህል ኃጠአተኛ ወይም በስንፍና የተሞላ ቢሆንም፣ ለቤተ-ክርስቲያን ዐውድ ተግሣጽ የማይመጥን እንኳ ሆኖ እያለ፣ ግን ቀሪውን ቅዱስ ቃል የካደ ሆኖ፣ በተለይም የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት።

በተጨማሪም፣ ያንን ለማመን፣ “ሁለት ወይም ሦስት ሆነው የተሰበሰቡት” ለጸሎት፣ አንድ ዓይነት ምትኀታዊ ኃይል ገፍቶ ወዲያውኑ በጸሎታችን እንደሚተገበር ማሰብ ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ ድጋፍ የለውም። ርግጥ ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ሲጸልዩ ኢየሱስ ይኖራል፣ ግን አንድ አማኝ ለብቻው ሲጸልይም በተመሳሳይ ይኖራል፣ ያ ግለሰብ ከሌሎቹ በሺህ ማይል ርቀት ላይ ቢሆንም። የኅብረት ጸሎት ጠቃሚ ነው፣ ኅብረትን ስለሚፈጥር (ዮሐንስ 17፡22-23)፣ እንዲሁም የአማኞች ቁልፍ ገጽታ ነው፣ እርስ በርስ ለመበረታታት (1 ተሰሎንቄ 5፡11) እና እርስ በርስ በማነሣሣት፣ ለፍቅርና ለመልካም ሥራ (ዕብራውያን 10፡24)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኅብረት ጸሎት ጠቃሚ ነውን? የኅብረት ጸሎት፣ ብቻውን ከሚጸልይ ከአንድ ግለሰብ ጸሎት ይልቅ ኃይለኛ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries