ጥያቄ፤
ገሃነም ርግጥ ነውን? ገሃነም ዘላለማዊ ነውን?
መልስ፤
በጣም ብዙ መቶኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በመንግሥተ ሰማያት መኖር ያምናሉ፣ ከገሃነም መኖር ይልቅ። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከሆነ፣ ገሃነም እንደ መንግሥተ ሰማያት እውን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽና ለይቶ ያስተምራል፣ ገሃነም ርግጠኛ ስፍራ መሆኑን፣ ኃጢአተኞች/የማያምኑ ከሞት በኋላ የሚላኩበት። ሁላችንም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ሠርተናል (ሮሜ 3፡23)። ለዛ ኃጢአትም ፍትሐዊው ቅጣት ሞት ነው (ሮሜ 6፡23)። ኃጢአታችን ሁሉ ባጠቃላይ በእግዚአብሔር ላይ በመሆኑ (መዝሙር 51፡4)፣ እግዚአብሔርም ወሰን የሌለውና ዘላለማዊ ሕላዌ በመሆኑ፣ የኃጢአት ቅጣት ሞት ደግሞ ወሰን የሌለውና ዘላለማዊ መሆን አለበት። ገሃነም ይህ ወሰን የሌለውና ዘላለማዊ ሞት ነው፣ እሱም በኃጢአታችን ሳቢያ የተከፈለን።
ኃጢአተኛ ሙታን በገሃነም እንደሚፈረድባቸው በቅዱስ ቃሉ ሁሉ ላይ ተገልጿል፣ እንደ “ዘላለማዊ እሳት” (ማቴዎስ 25፡41)፣ “የማይጠፋ እሳት” (ማቴዎስ 3፡12)፣ “ኀፍረት እና ዘላለማዊ ውርደት” (ዳንኤል 12፡2)፣ እዚያም “እሳቱ የማይጠፋ” ስፍራ ነው (ማርቆስ 9፡44-49)፣ “የመከራ” እና “እሳት” ስፍራ (ሉቃስ 16፡23-24)፣ “ዘላለማዊ ጥፋት” (2 ተሰሎንቄ 1፡9)፣ “የመከራውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም የማይጠፋበት” ስፍራ (ራዕይ 14፡10-11)፣ እና “የሚነድ ድኚ ባሕር” ኃጢአተኞች የሚሆኑበት ስፍራ “ቀንና ሌሊት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሣቀያሉ” (ራዕይ 20፡10)።
በገሃነም የኃጢአተኞች ቅጣት፣ ጻድቃን በሰማይ እንደሚያገኙት ፍጹም የሆነ ደስታ ፈጽሞ የሚያበቃ አይደለም። ኢየሱስ ራሱ እንዳመለከተው በገሃነም የሚሆነው ቅጣት በመንግሥተ ሰማይ እንደሚሆነው ዘላለማዊ ሕይወት ያለ ነው (ማቴዎስ 25፡46)። ኃጢአተኞች ለዘላለም በእግዚአብሔር ቁጣና መዓት ሥር ናቸው። በገሃነም የሚሆኑት እነርሱ የእግዚአብሔር ፍርድ ፍጹም መሆኑን ይገነዘባሉ (መዝሙር 76፡10)። በገሃነም የሚሆኑት እነርሱ ቅጣታቸው ትክክልና እነርሱ ብቻ እንደሚወቀሱ ያውቃሉ (ዘዳግም 32፡3-5)። አዎን፣ ገሃነም እውን ነው። አዎን፣ ገሃነም የመከራና የቅጣት ስፍራ ነው፣ እሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም የማያበቃ፣ ፍጻሜ የሌለው። እግዚአብሔር ይመስገን፣ በኢየሱስ ይህንን ዘላለማዊ ዕጣ ማምለጥ ስለቻልን (ዮሐንስ 3፡16፣ 18፣ 36)።
English
ገሃነም ርግጥ ነውን? ገሃነም ዘላለማዊ ነውን?