ጥያቄ፤
ሰው በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯል ማለት ምንድነው (ዘፍጥረት 1፡26-27)?
መልስ፤
በፍጥረት የመጨረሻ ቀን እግዚአብሔር አለ፣ “ሰውን በመልካችንና በምሳሌያችን እንፍጠር” (ዘፍጥረት 1፡26)። እንዲህም ሥራውን “በግል መንካቱ” አጠናቀቀ። እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው እና የራሱን ትንፋሽ በመስጠት ሕይወትን ሰጠው (ዘፍጥረት 2፡7)። በመሠረቱ ሰው ከእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ የተለየ ነው፣ ሁለቱም ሥጋዊ አካል እና ሥጋዊ ያልሆነ ነፍስ/መንፈስ ያለው።
የእግዚአብሔር “መልክ” ወይም “ምሳሌ” አለው ማለት በቀላል አገላለጽ፣ እግዚአብሔርን እንድንመስል ተፈጥረናል ማለት ነው። አዳም እግዚአብሔርን አይመስልም ነበር፣ እግዚአብሔር ሥጋና ደም አለው በሚል መልኩ። ቅዱስ ቃሉ የሚለው “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” (ዮሐንስ 4፡24) እናም ስለዚህ ያለ አካል ይኖራል። ሆኖም፣ የአዳም አካል የእግዚአብሔርን ሕይወት ያንጸባርቅ ነበር፣ በፍጹም ጤንነት እንደተፈጠረ፣ ለሞትም አይገዛም ነበር።
የእግዚአብሔር መልክ የሚጠቅሰው ሥጋዊ ያልሆነውን የሰው ክፍል ነው። እሱም ሰውን ከእንስሳ ዓለም ይለየዋል፣ እግዚአብሔር በምድር ላይ እንዲገዛ በሰጠው መሠረት ብቁ ያደርገዋል (ዘፍጥረት 1፡28)፣ እንዲሁም ለፈጣሪው ጋር እንዲገናኝ ያስችለዋል። እሱ በአስተሳሰብ፣ በሞራል፣ በማኅበረሰባዊነት አምሳያ መሆን ነው።
በአስተሳሰብ፣ ሰው የተፈጠረው የሚያስብ፣ ፍቃዳዊ ወኪል ሆኖ ነው። በሌላ አገላለጽ፣ ሰው ሊያስብ ይችላል እንዲሁም ሊመርጥ ይችላል። ይህም የእግዚአብሔር አሳቢነት እና ነጻነት ነጸብራቅ ነው። በሆነ ጊዜ አንዱ ማሽን ሊፈለስፍ ይችላል፣ መጽሐፍ ሊጽፍ፣ መልክዓ ምድር ሊስል፣ ሙዚቃ ሊያቀነባብር፣ ቀመሮችን ሊደምር፣ ወይም የቤት እንስሳውን ሊሰይም ይችላል፣ እሱ ወይም እሷ የሚያሳዩት ሐቅ በእግዚአብሔር መልክ መፈጠራችንን ነው።
ከሞራል አኳያ፣ ሰው የተፈጠረው በጽድቅና ፍጹም በሆነ ንጽሕና ነው፣ የእግዚአብሔር ቅድስና ነጸብራቅ። እግዚአብሔርም የፈጠረውን ሁሉ ተመለከተ (የሰው ልጅም ተካቶ) እናም “በጣም ጥሩ” ብሎ ጠራው (ዘፍጥረት 1፡31)። ንቃተ ሕሊናችን ወይም “የሞራል ልኬታችን” ያንን የዋነኛ አቋማችንን ጥላ ያሳያል። አንዱ ሕግን ሲጽፍ፣ ከክፉ ገለል ሲል፣ መልካም ጠባይን ሲያመሰግን፣ ወይም ኃጢአተኝነት ሲሰማው፣ እሱ የሚያረጋግጠው ሐቅ በእግዚአብሔር በራሱ መልክ መፈጠራችንን ነው።
በማኅበረሰባዊነት፣ ሰው የተፈጠረው ለኅብረት ነው። ይህም የእግዚአብሔርን በሦስትነቱ አንድ የሆነ ማንነቱን ያሳያል፣ እንዲሁም ፍቅሩን። በዔድን፣ የሰው ቀዳሚ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር ነበር (ዘፍጥረት 3፡8 ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ያሳያል)፣ እግዚአብሔርም የመጀመሪያዋን ሴት ያበጀው “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም” በሚል ምክንያት ነው (ዘፍጥረት 2፡18)። በየጊዜው አንዱ ሲያገባ፣ ወዳጅ ሲያበጅ፣ ልጅ ሲያቅፍ፣ ወይም ቤተ-ክርስቲያን ሲገኝ የሚያመለክተው ሐቅ በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠራችንን ነው።
በእግዚአብሔር መልክ የመፈጠር ክፋይ፣ አዳም ነጻ ምርጫ የማድረግ ችሎታ ያለው መሆኑ ነው። ምንም እንኳ ጻድቅ ተፈጥሮ ቢሰጠውም፣ አዳም ክፉ ምርጫ አደረገ፣ በፈጣሪው ላይ ለማመጽ። ይህን በማድረጉም አዳም በራሱ የእግዚአብሔርን መልክ አበላሸ፣ እናም ያንን የተጎዳ አምሳል በዝርዮቹ ሁሉ ላይ አስተላለፈ (ሮሜ 5፡12)። ዛሬ፣ የእግዚአብሔርን መልክ ገና እንደያዝን ነን (ያዕቆብ 3፡9)፣ ግን ደግሞ የኃጢአት ጠባሳ አለብን። በአስተሳሰብ፣ በሞራል፣ በማኅበረሰብ፣ እና በአካል፣ የኃጢአትን ጉዳት እናሳያለን።
መልካሙ ዜና፣ እግዚአብሔር አንድን ግለሰብ ሲዋጅ፣ ዓይነተኛውን የእግዚአብሔርን መልክ መመለስ ይጀምራል፣ “አዲስ ማንነት፣ እንደ እግዚአብሔር እንዲመስል የተፈጠረ፣ በእውነተኛ ጽድቅና እና ቅድስና” በመፍጠር (ኤፌሶን 4፡24)። ያ መቤዠት የሚገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችን በማመን፣ ከእግዚአብሔር ከለየን ኃጢአት (ኤፌሶን 2፡8-9)። በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ሆነናል፣ በእግዚአብሔር አምሳል (2 ቆሮንቶስ 5፡17)።
English
ሰው በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯል ማለት ምንድነው (ዘፍጥረት 1፡26-27)?