ጥያቄ፤
የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ምንድነው?
መልስ፤
ሮሜ 14፡10-12 ይላል፣ “ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና… እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።” ሁለተኛ ቆሮንቶስ 5፡10 ይነግረናል፣ “መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።” ከዐውደ-ጽሑፉ አኳያ፣ ግልጽ የሆነው፣ ሁለቱም ቅዱስ ቃላት ክርስቲያኖችን ነው የሚያመለክቱት፣ የማያምኑትን ሳይሆን። ስለዚህ፣ የክርስቶስ የፍርድ ወንበር፣ አማኞች ስለ ሕይወታቸው ለክርስቶስ ምላሽ እንደሚሰጡ ያካትታል። የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ደኅንነትን አይወስንም፤ ያ የሚወሰነው ክርስቶስ በእኛ ምትክ ባደረገው መሥዋዕትነት ነው (1 ዮሐንስ 2፡2) እንዲሁም በእርሱ ላይ ባለን አምነት (ዮሐንስ 3፡16)። ኃጢአታችን ሁሉ ይቅር ተብሏል፣ ስለ እሱም ፈጽሞ አንኮነንም (ሮሜ 8፡1)። የክርስቶስን የፍርድ ወንበር መመልከት አይኖርብንም፣ እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን እንደሚፈርድብን፣ ነገር ግን ይልቁንም እግዚአብሔር ስለ ሕይወታችን እንደሚሸልመን እንጂ ነው። አዎን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል፣ ስለ ራሳችን ምላሽ እንሰጣለን። የዚህ ክፋይ የሚሆነው በርግጥ ስለ ሠራነው ኃጢአት ምላሽ መስጠት ነው። ሆኖም፣ ያ የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ቀዳሚ ትኩረት አይሆንም።
በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ላይ፣ አማኞች ይሸለማሉ፣ እንዴት ክርስቶስን እንዳገለገሉት ላይ በመመሥረት (1 ቆሮንቶስ 9፡4-27፤ 2 ጢሞቴዎስ 2፡5)። ከሚፈረዱብን አንዳንድ ነገሮች መካከል፣ ለታላቁ ተልዕኮ ምን ያህል እንደታዘዝን ነው (ማቴዎስ 28፡18-20)፣ በኃጢአት ላይ የቱን ያህል ባለ ድሎች እንደነበርን (ሮሜ 6፡1-4)፣ እና አንደበታችንን የቱን ያህል እንደተቆጣጠርን (ያዕቆብ 3፡1-9)። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አማኞች አክሊል እንደሚቀበሉ ይናገራል፣ ስለ ተለያዩ ነገሮች፣ ክርስቶስን እንዴት በታማኝነት እንዳገለገሉት ላይ በመመርኮዝ (1 ቆሮንቶስ 9፡4-27፤ 2 ጢሞቴዎስ 2፡5)። የተለያዩ አክሊሎች ተገልጸዋል፣ 2 ጢሞቴዎስ 2:5፣ 2 ጢሞቴዎስ 4:8፣ ያዕቆብ 1:12፣ 1 ጴጥሮስ 5:4፣ እና ራዕይ 2:10 ላይ። ያዕቆብ 1:12 የተሻለ ማጠቃለያ ነው፣ ስለ ክርስቶስ የፍርድ ወንበር እንዴት ማሰብ እንደሚኖርብን፡ “በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።”
English
የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ምንድነው?