ጥያቄ፤
ወዳጆቻችንንና የቤተሰብ አባሎቻችንን በሰማይ ማየትና ማወቅ እንችላለን?
መልስ፤
ብዙዎች ሰዎች ይላሉ፣ መንግሥተ ሰማይ ሲደርሱ የሚፈልጉት ቀዳሚ ነገር፣ ወዳጆቻቸውንና የሚወዷቸውን፣ እነርሱም ቀድመው የሞቱትን ሁሉ ማየት ነው። በዘላለማዊነት የተትረፈረፈ ጊዜ ይኖራል፣ ለመመልከት፣ ለማወቅ፣ እና ጊዜ ለማሳለፍ፣ ከወዳጆቻችንና ከቤተሰብ አባሎቻችን ጋር። ሆኖም፣ ያ ቀዳሚ ትኩረት አይሆንም፣ በመንግሥተ ሰማይ። ይልቁንም እግዚአብሔርን በማምለክና በመንግሥተ ሰማይ ድንቅ በመደሰት እንጠመዳለን። ከምንወዳቸው ጋር የሚኖረን ዳግም ኅብረት በማያጠራጥር መልኩ በእግዚአብሔር በሕይወታችን የፈጸመውን ጸጋና ክብር በመቁጠር ይዋጣል፣ የእርሱን ፍቅርና የእርሱን ድንቅ ሥራ። እጅግ አድርጎም ደስ ይለናል፣ ከሌሎች አማኞች ጋር ሆነን ጌታን ለማመስገንና ለማምለክ በመቻላችን ምክንያት፣ በተለይም በምድር ላይ የምንወዳቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል፣ ከሕይወት በኋላ ሰዎችን መገንዘብ መቻል አለመቻላችን? ንጉሥ ሳዖል ሳሙኤልን ተገንዝቦታል፣ የዓይንዶሯ ጠንቋይ ሳሙኤልን ከሙታን ዓለም በሳበችው ጊዜ (1 ሳሙኤል 28:8-17)። የዳዊት ሕፃን ልጅ ሲሞት፣ ዳዊት ብሏል፣ “እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ፣ እርሱ ወደ እኔ አይመጣም” (2 ሳሙኤል 12፡23)። ዳዊት ገምቶ የነበረው ልጁን በመንግሥተ ሰማይ አንደሚለይ ነበር፣ ሕፃን ሆኖ በመሞቱ ምክንያት። ሉቃስ 16፡19-31 ላይ፣ አብርሃም፣ አልአዛር፣ እና ሀብታሙ ሰው ሁሉ የሚታወቁ ነበሩ፣ ከሞት በኋላ። በመለወጥ ላይ፣ ሙሴ እና ኤልያስ የሚታወቁ ነበሩ (ማቴዎስ 17፡3-4)። በእነዚህ ምሳሌዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሞት በኋላ እንደምንታወቅ የሚጠቁም ይመስላል።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውጀው መንግሥተ-ሰማይ ስንደርስ፣ “እርሱን እንድንመስል እናውቃለን [ኢየሱስ]፤ እርሱን እንዳለ እናየዋለንና” (1 ዮሐንስ 3፡2)። ሥጋዊ አካላችን ከፊተኛው ሰው፣ ከአዳም እንደሆነ ሁሉ፣ የትንሣኤ አካላችን ደግሞ የክርስቶስን ይመስላል (1 ቆሮንቶስ 15፡47)። “የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን። ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።” (1 ቆሮንቶስ 15፡49፣ 53)። ብዙ ሰዎች አውቀውታል፣ ከትንሣኤው በኋላ (ዮሐንስ 20:16፣ 20፤ 21:12፤ 1 ቆሮንቶስ 15:4-7)። ኢየሱስ በከበረ አካሉ የሚታወቅ ከሆነ፣ እኛም በከበረ አካላችን እንታወቃለን። የምንወዳቸውን በመንግሥተ ሰማያት መመልከት መቻል፣ የሰማይ የከበረ ገጽታ ነው፣ ነገር ግን ባመዛኙ ስለ እግዚአብሔር ነው፣ ስለ እኛ ደግሞ ባነሰ። ምን ያህል ደስታ ይሆናል፣ ከምንወዳቸው ጋር ዳግም መገናኘትና እግዚአብሔርን ማምለክ፣ ከእነርሱ ጋር፣ ለዘላለም።
English
ወዳጆቻችንንና የቤተሰብ አባሎቻችንን በሰማይ ማየትና ማወቅ እንችላለን?