settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በፍቅር መያዜን እንዴት አውቃለሁ?

መልስ፤


ፍቅር እጅግ ኃይለኛ ስሜት ነው። እሱ አብዛኛውን ሕይወታችንን ያነቃቃል። በርካታ ጠቃሚ ውሳኔዎችን በዚህ ስሜት ላይ ተመሥርተን እናደርጋለን፣ እንዲያውም እንጋባለን “በፍቅር መያዛችን” ስለተሰማን። ይህ ምክንያት ሊሆን ይችላል፣ ግማሽ የሚሆኑት የመጀመሪያ ጋብቻዎች ለፍቺ የሚበቁት። መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፣ እውነተኛ ፍቅር የሚመጣና የሚሄድ ስሜት አለመሆኑን፣ ውሳኔ እንጂ። የሚወዱንን ብቻ እንድንወድ አይደለም፤ የሚጠሉንም መውደድ ይገባናል፣ ክርስቶስ የማይወደዱትን በወደደበት ተመሳሳይ መንገድ (ሉቃስ 6፡35)። “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል” (1 ቆሮንቶስ 13፡4-7)።

ለአንዱ “በፍቅር መውደቅ” በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን አንዳንድ ጥያቄዎች መጠየቅ ይኖርባቸዋል፣ በእውነተኛ ፍቅር የሚሰማንን ከመወሰናችን በፊት። አንደኛ፣ ይህ ሰው ክርስቲያን ነውን፣ ማለትም ሕይወቱን ለክርስቶስ ሰጥቷልን? እሱ/እሷ ለመዳን ክርስቶስን ብቻ አምነዋልን? ደግሞም፣ ልብህንና ስሜትህን ለአንድ ሰው እንደሰጠህ የምትቆጥር ከሆነ፣ ራስህን መጠየቅ ይኖርብሃል፣ ከሰዎች ሁሉ በላይ ያንን ሰው ለማስቀመጥ ፍቃደኛ መሆንህን፣ ከእግዚአብሔር ብቻ ሁለተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፣ ሁለት ሰዎች ሲጋቡ አንድ ሥጋ እንደሚሆኑ (ዘፍጥረት 2፡24፤ ማቴዎስ 19፡5)።

ሌላው ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ነገር፣ የተወደደው ግለሰብ ለፍቅር ጓደኝነት መልካም ዕጩ መሆን አለመሆኑ ነው። እሱ/እሷ ቀደም ብለው እግዚአብሔርን ከሁሉ አስቀድመዋልን፣ በሕይወታቸው? እሱ/እሷ ጊዜና ኃይላቸውን ግንኙነቱን ትዳርን ለመገንባት ያውሉታልን፣ እስከ ፍጻሜ የሚቆይ እንዲሆን? ምንም ዓይነት የመለኪያ ዘንግ የለም፣ ከአንዱ ጋር በእውነተኛ ፍቅር ለመሆናችን፣ ነገር ግን የራሳችንን ስሜት መከተላችንን ወይም እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን መከተላችንን ማስተዋል አስፈላጊ ነው። እውነተኛ ፍቅር ውሳኔ ነው፣ ስሜት ሳይሆን። እውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፍቅር አንዱን ሁልጊዜ ማፍቀር ነው፣ “በፍቅር ላይ” እንደሆንክ ሲሰማህ ብቻ ሳይሆን።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በፍቅር መያዜን እንዴት አውቃለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries