settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አንድ ነገር ኃጢአት መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?

መልስ፤


በዚህ ጥያቄ ላይ ሁለት ጉዳዮች ይካተታሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ የጠቀሳቸውና ኃጢአት እንደሆኑ ያስታወቃቸው ነገሮች እና መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ያላስታወቃቸው። ቅዱስ ቃሉ የሚዘረዝራቸው የተለያዩ ኃጢአቶች የሚያካትቱት ምሳሌ 6:16-19፣ ገላትያ 5:19-21፣ እና 1 ቆሮንቶስ 6:9-10። ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ሊኖር አይችልም፣ እነዚህ ምንባቦች ድርጊቶቹን እንደ ኃጢአት ማቅረባቸው፣ እግዚአብሔር ያልተቀበላቸው ነገሮች። ግድያ፣ ዝሙት፣ ውሸት፣ ስርቆት፣ ወዘተ—ምንም ጥርጣሬ የለም መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ነገሮች ኃጢአት ለማለቱ። እጅግ አስቸጋሪው ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ያልገለጻቸውን ኃጢአቶች መወሰን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ጉዳዮችን ሳይሸፍን ሲቀር፣ ከቃሉ ላይ አጠቃላይ መርሖዎች አሉን፣ እንዲመሩን።

በቅድሚያ፣ የተወሰነ የቃሉ ማጣቀሻ ምንም ከሌለ፣ አንድ ነገር ስሕተት ነው ብሎ አለመጠየቁ ይሻላል፣ ነገር ግን፣ ይልቁንም፣ እሱ በርግጥ መልካም ከሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ ይላል፣ ለምሳሌ፣ እኛ፣ “እያንዳንዱን ዕድል በተሻለ እንድንጠቀም” (ቆላስያስ 4፡5)። በዚህ ምድር ላይ ያሉን ጥቂት ቀናት እጅግ አጭርና ውድ ናቸው፣ ከዘላለም ጋር በተያያዘ፣ እናም በግላዊ ነገሮች ጊዜያችንን እንድናሳልፍ ፈጽሞ አይገባም፣ ነገር ግን ሌሎችን እንደ መሻታቸው ለመገንባት እንድንረዳ እንጂ” (ኤፌሶን 4፡29)።

መልካሙ ሙከራና ውሳኔ፣ እኛ በታማኝነት፣ በበጎ ሕሊና፣ እግዚአብሔር እንዲባርከን መለመን ነው፣ እንዲሁም ለተወሰነ ተግባር ለገዛ ራሱ ዓላማ። “ስለዚህ ብትበሉም ሆነ ብትጠጡ፣ የምታደርጉትን ሁሉ ለእግዚአብሐር ክብር አድርጉት” (1 ቆሮንቶስ 10፡31)። ለጥርጥር ስፍራ ቢኖር፣ እግዚአብሔርን ያስደስተው/አያስደስተው እንደሆነ፣ እንግዲያውስ መተዉ ይመረጣል። “ከእምነት ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው” ሮሜ 14፡23)። ማስታወስ ያለብን ሥጋችንም ሆነ ነፍሳችን የተዋጀው ለእግዚአብሔር እንዲሆን ነው። “ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” (1 ቆሮንቶስ 6:19-20)። ይህ ታላቅ እውነት ርግጠኛ ዋጋ ሊሰጠው ይገባል፣ ምን እንደምንሠራና የት እንደምንሄድ።

በተጨማሪም፣ ድርጊቶቻችንን መገምገም ይኖርብናል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን፣ ግን ደግሞ እርሱ በቤተሰባችን፣ በወዳጆቻችን፣ እና በሌሎች ሰዎች ባጠቃላይ በሚያስከትለው ተጽዕኖ። ምንም እንኳ የተለየ ነገር በግል ባይጎዳንም፣ እሱ በጎጂ መልኩ ሌለኛው ላይ ተጽዕኖ ቢያሳድር ወይም ቢጎዳ፣ እሱ ኃጢአት ነው። “ሥጋን አለመብላት ወይም ወይን አለመጠጣት ወይም ወንድምህ የሚሰናከልበትን ምንም ነገር አለማድረግ ይሻላል… እና ብርቱዎች የሆንን የደካሞችን ድካም መሸከም ይኖርብናል፣ ራሳችንን ሳናስደስት” (ሮሜ 14፡21፤ 15፡1)።

በመጨረሻም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችንና አዳኛችን እንደሆነ አስታውሱ፣ እናም ሌላ ማንኛውም ነገር ለእሱ ፍቃድ ካለን ቀጥተኝነት ቅድሚያ እንዲወስድ ልንፈቅድ አይገባም። ማንኛውም ዓይነት ጠባይ ወይም አፈንጋጭ ነገር ወይም ጉጉት በሕይወታችን ላይ እንዲሠለጥን ሊፈቀድለት አይገባም፤ ክርስቶስ ብቻ ነው ያ ሥልጣን ያለው። “ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።” (1 ቆሮንቶስ 6፡12)። “እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።” (ቆላስይስ 3፡17)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አንድ ነገር ኃጢአት መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries