settings icon
share icon
ጥያቄ፤

‹ለህይወቴ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መልስ፤


ለአንድ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ሁለት ቁልፍ ነገሮች አሉ፡፡ 1ኛ) ምን እየጠየቅህ እንዳለህ እርግጠኛ ሁን ወይም ማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ የሚከለክለው አንድ ነገር እንዳይደለ ከግምት ውስጥ ማስገባት፡፡ 2ኛ) ምን እየጠየቅህ እንዳለህ እርግጠኛ ሁን ወይም ማድረጉ እግዚአብሔርን የሚያከብር እና በመንፈሳዊ ነገርህ ለማደግ እንደሚረዳህ ከግምት ውስጥ ማስገባት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ነገሮች እውነት ከሆኑ እና እስካሁን በመጠየቅ ላይ ያለኸውን ነገር እግዚአብሔር እየሰጠህ ካልሆነ እየጠየቅህ ያለኸው ነገር እንዲኖርህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ላይሆን ይችላል፤ ወይም ምናልባት ረዘም ላለ ጊዜ መጠበቅ ያስፈልግሃል፡፡ እንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ሰዎች ምን እንደሚያደርጉ፣ የት እንዲሚሰሩ፣ የት እንዲሚኖሩ፣ ማንን እንደሚያገቡ ወ.ዘ.ተ እግዚአብሔር ለይቶ እንዲነግራቸው ይፈልጋሉ፡፡ እግዚአብሔር አልፎ አልፎ ለሰዎች ቀጥተኛ እና የተለየ መረጃን ይሰጣል፡፡ እነዚያ ነገሮች በተመለከተ እግዚአብሔር ምርጫዎችን እንድናደርግ ፈቅዶልናል፡፡

ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2 “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ከዚያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ፤መልካም የሆነውን፤የሚያስደስት እና ትክክለኛውን ፈቃድ፤ ምን እንደሆነ መሞከር እና ማረጋገጥ ትችላለህ” ብሎ ይነግረናል፡፡ እግዚአብሔር እንዳናደርገው የሚፈልገው ብቸኛው ውሳኔ ኃጢአትን የማድረግ ወይም ፈቃዱን እምቢ የማለት ውሳኔን ነው፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ፈቃድ ጋር የሚስማሙትን ምርጫዎች እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለአንተ ምን እንደሆነ እንዴት ታውቃለህ? ከጌታ ጋር በቅርበት እየተራመድህ ከሆነ እና በእውነት ለሕይወትህ የእርሱን ፈቃድ እየፈለግህ ከሆነ እግዚአብሔር መሻቱን በልብህ ላይ ያስቀምጣል፡፡ ቁልፉ የራስህን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈለግ ነው፡፡ “በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።” (መዝሙረ ዳዊት 37፡4)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በእሱ ላይ በተቃራኒ የማይናገር ከሆነ እና በእውነተኛው በመንፈሳዊው የሚጠቅምህ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚያ ውሳኔዎችን እንድታደርግና ልብህን እንድትከተል “ፈቃድ” ይሰጥሃል፡፡ እና በትሁት መንፈስ እና በተከፈተ አዕምሮ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእውነት የምትፈልግ ከሆነ እሱ ፈቃዱን ለአንተ ይገልጽልሃል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

‹ለህይወቴ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries