settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ከሞት በኋላ ሕይወት አለ?

መልስ፤


ከሞት በኋላ ሕይወት አለ? መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር “ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወት ዘመኑ ጥቂት ቀን ነው፣ መከራም ይሞላዋል። እንደአበባ ይወጣል፣ ይረግፋልም፣ እንደጥላም ይሸሻል፣ እርሱም አይጸናም... በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሰው ይሆናልን?”

እንደ ኢዮብ አብዛኞቻችን በዚህ ጥያቄ ተፈትነናል። እኛ ከሞትን በኋላ በእርግጠኝነት ምን እንሆናለን? እንዲሁ በቀላሉ መኖር እናቋርጣለን ማለት ነው? ሕይወት ማለት ሰዎች የግል ዝናን ለማግኘት ከመሬት የሚለቁበትና የሚመለሱበት ተሽከርካሪ በር ይሆን እንዴ? ሁሉም ወደ አንድ ስፍራ ነው የሚሄደው ወይስ እኛ ወደተለያዩ ቦታዎች ነው የምንሄደው? በእርግጥ መንግስተ ሰማይና ገሃነመ እሳት የሚባል አለ ወይስ የአስተሳሰባችን ሁኔታ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ብቻ ሳይሆን በጣም አስደናቂ የሆነ የዘላለም ሕይወት አለ። “አይን ያላየችው፣ ጆሮም ያልሰማው፣ በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚሐብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው።” (1ኛ ቆሮንቶስ 2፡ 9)። ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለፀው እግዚሐብሔር ወደ ምድር የመጣው የዘላለም ሕይወት የሆነውን ስጦታ ሊሰጠን ነው። “እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ፣ ስለበደላችንም ደቀቀ፣ የደኅንነታችንም ተግሳፅ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።” ኢሳያስ 53፡ 5)

ኢየሱስ እኛ እያንዳንዳችን መቀጣት የሚገባንን ቅጣት ተቀበለልን። የራሱንም ህይወት ሰዋልን። ከሦስት ቀን በኋላ ከመቃብር በመንፈስና በስጋ በመነሳት በሞት ላይ ያለውን አሸናፊነት አረጋገጠ። ወደዘላለማዊ ቤቱ ወደመንግስተ ሰማይ ከማረጉ በፊት በመሬት ለ40 ቀናት በመቆየት ለብዙ ሺህ ሰዎች ታይቷል። ሮሜ 4፡ 25 እንዲህ ይላል “ስለበደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለማፅደቅም የተነሳውን ጌታችንን…።”

የክርስቶስ ትንሳኤ በሚገባ የተዘገበ ዜና ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለእርግጠኝነቱ የአይን ምስክሮችን እንዲጠይቁ ከሰዎች ጋር ተወራርዷል። ማንም ደግሞ ሃቁን ሊክድ የቻለ የለም። ትንሳኤ የክርስትና እምነት የማዕዘን ድንጋይ ነው። ምክንያቱም ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ እኛም በበኩላችን ከሞት እንደምንነሳ እምነት እንዲኖረን ነው።

ይህንን ያላመኑትን ጥቂት ቀደምት ክርስቲያኖችን እንዲህ ሲል ይመክራቸዋል። “ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሳ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ፦ ትንሳኤ ሙታን የለም ለምን ይላሉ? ትንሳኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሳማ።” (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡ 12-13)

እንደገና በሕይወት ለሚነሱት ክርስቶስ የመጀመሪያው ታላቅ መኸር ብቻ ነው። ሁላችንም በምንዛመደው በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት የስጋ ሞት መጣብን። ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመናቸው ወደ እግዚሐብሔር ቤተሰብነት የተጨመሩት ሁሉ አዲስ ሕይወት ይሰጣቸዋለ። (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡ 20-22) እግዚሐብሔር የኢየሱስን አካል እንዳስነሳው ሁሉ የኛን አካሎች ኢየሱስ ሲመለስ በትንሳኤ ይነሳሉ’ (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡ 14)

ምንም እንኳ ሁላችንም በትንሳኤ የምንነሳ ቢሆንም፣ ሁሉም በአንድነት ወደ መንግስተ ሰማይ ይገባል ማለት አይደለም። እያንዳንዱ ሰው በዚህ ሕይወት እያለ ለዘላለም የት እንደሚሄድ ምርጫ ማድረግ አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን አንድ ጊዜ እንደምንሞት ተወስኗል። ከዚያ በኋላ ግን ፍርድ ይመጣል (ዕብራውያን 9. 27)። እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፣ ፃድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ። (ማቴዎስ 25፡46)።

ገሐነም እሳት እንደ መንግስተ ሰማይ የሕይወት ገፅታ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ተጨባጭ እውን ስፍራ ነው። ይህ ቦታ ኃጥአን የሆኑት ማለቂያ የሌለው ዘላለማዊ ቁጣ ከእግዚሐብሔር የሚያገኙበት ነው። ከሐፍረት፣ ፀፀትና ንቀት የተነሳ እየታወቃቸው ስሜታዊ፣ አዕምሮአዊና አካላዊ ስቃይ የሚጋፈጡበት ነው።

ገሐነም እሳት ጥልቅ የሆነ ጉድጓድ ነው ። (ሉቃስ 8፡ 31, ራዕይ 9፡ 1)። ነዋሪዎች ቀንና ሌሊት ለዘላለም የሚሰቃዩበት በድኝ የሚቃጠል የእሳት ባህር ነው።(ራዕይ 20፡10)። በገሐነም እሳት ጥልቅ ሐዘንና ቁጣ በዋይታና ጥርስ በማፏጨት የሚገለፅበት ቦታ ነው። (ማቴዎስ 13፡ 42) ይህ ቦታ ትሉ ፈፅሞ የማይሞትበትና እሳቱም የማይጠፋበት ነው። (ማርቆስ 9፡ 48)

እግዚሐብሔር በኃጥአን ሞት ደስ አይለውም፣ ነገር ግን ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ይፈልጋል። (ሕዝቅኤል 33፡ 11)። ነገር ግን እሱ አስገድዶ እጅ እንድንሰጥ አይፈልግም። እሱን ባንቀበለው ሌላ ምርጫ የለውም፤ ከእርሱ ተለይተን ለመኖር እስከፈለግን ድረስ የፈለግነውን ይሰጠናል።

ሕይወት በምድር ፈተና ሲሆን ለሚመጣው የምንዘጋጅበት ነው። ለአማኞች በእግዚሐብሔር የቅርብ መገኘት ይህ የዘላለም ሕይወት ነው። ስለዚህ እንዴት ነው እኛ ፃድቃን ሆነን ይህንን ዘላለማዊ ህይወት የምንቀዳጀው? አንድ ብቸኛ መንገድ ብቻ አለ፦ በኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚሐብሔር ልጅ ማመንና መደገፍ ነው። ኢየሱስ እንደዚህ አለ “ ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፣ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፣ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም…” (ዮሐንስ 11፡ 25-26)።

የዘላለም ሕይወት ነፃ ስጦታ ለሁሉም የተፈቀደ ነው። ነገር ግን ከአንዳንድ ዓለማዊ ደስታዎች ራሳችንን ማቀብና እኛነታችንን ለእግዚሐብሔር መስዋዕት አድርገን እንድናቀርብ ከኛ የሚፈለግ ጉዳይ ነው። “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ በልጁ የማያምን ግን የእግዚሐብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም” (ዮሐንስ 3፡ 36)። ከሞት በኋላ ኃጢያታችንን እንድንናዘዝ ዕድል አይሰጠንም፣ ምክንያቱም አንዴ እግዚሐብሔርን ፊትለፊት ካየነው ማመን ካልሆነ ምርጫ አይኖረንም። እርሱ አሁን በእምነትና በፍቅር እንድንጠጋው ይፈልጋል። የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በእግዚሐብሔር ላይ ላደረግነው የኃጢያት አመፅ የተከፈለ ዋጋ አድርገን ከተቀበልን ትርጉም ያለው ሕይወት በምድር ላይ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በክርስቶስ ፊትም የዘላለም ሕይወት ዋስትና ተሰጥቶናል። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ ልትቀበለው የምትፈልግ ከሆነ አንድ የናሙና ፀሎት አቅርበንልሃል። አስታውስ ይህንን ፀሎት ወይም ሌላ ፀሎት ማቅረብ አያድንህም። በክርስቶስ ብቻ ማመን ነው ከኃጢያት የሚያድንህ። ይህንን ፀሎት የምታቀርበው በእግዚሐብሔር ላይ ያለህን እምነት ለመግለፅና ድነትን ስላስገኘልህ ምስጋና የምታቀርብበት መንገድ ነው። “እግዚሐብሔር ሆይ በአንተ ፊት ኃጢያት ፈፅሜያአለሁ። ስለሆነም ቅጣት ይገባኛል። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔ የሚገባውን ቅጣት ስለከፈለልኝ በርሱ በማመኔ ይቅርታ ተደርጎልኛል። ለድነቴ እምነቴን በርሱ ላይ እጥላለሁ። ስለአስደናቂው ፀጋህና ይቅርታህ እንዲሁም ስለየዘላለም ሕይወት ስጦታህ አመሰግንሐለሁ! አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ከሞት በኋላ ሕይወት አለ?
© Copyright Got Questions Ministries