settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጋብቻ ምን ይላል?

መልስ፤


የጋብቻ መፈጠር ዘፍጥረት 2፡23-24 ላይ ተመዝግቧል፣ “አዳምም አለ፣ ‘ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፣ እርሷ ከወንድ ተገኝታለችና “ሴት” ትባል።’ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል በሚስቱም ይጣበቃል፣ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ፣ ከዚያም ሴትን ፈጠረ፣ ትጎዳኘው ዘንድ። ጋብቻ እግዚአብሔር “ያበጀው” ነው፣ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ለሚለው ሐቅ፣ (ዘፍጥረት 2፡18)።

“ረዳት” የሚለው ቃል ሔዋንን ለመግለጽ ዘፍጥረት 2፡20 ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ፍችው “መክበብ፣ መከላከል ወይም ማገዝ፣ መርዳት” ነው። ሔዋን የተፈጠረችው ከአዳም ጎን እንድትሆን ነው እንደ “ግማሽ” አካሉ፣ የእርሱ ረዳትና ደጋፊ እንድትሆነው። ወንድና ሴት ሲጋቡ “አንድ ሥጋ” ይሆናሉ። ይህ አንድነት በሙላት የሚገለጸው በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ሲጎዳኙ ነው። አዲስ ኪዳን ይህን አንድነት በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ይጨምራል። “ስለዚህ ከእንግዲህ በኋላ ሁለት አይደሉም፣ አንድ እንጂ። ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው” (ማቴዎስ 19፡6)።

በሐዋርያው ጳውሎስ በርካታ መልእክቶች ተጽፈዋል፣ ጋብቻን የሚያመለክቱ እና አማኞች በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ እንዴት መመላለስ እንደሚኖርባቸው። ከዚህም አንደኛው ምንባብ 1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 7፣ እና ሌላው ኤፌሶን 5፡22-33 ነው። አንድ ላይ በሚጠኑበት ጊዜ፣ እነዚህ ሁለት ምንባቦች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖዎችን ይሰጣሉ፣ ይኸውም እግዚአብሔርን የሚያስደስተውን የጋብቻ ግንኙነት መልክ የሚያበጁ።

የኤፌሶኑ ምንባብ በተለይ የቀረበው የተሳካ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጋብቻን ለመጥቀስ ነው። “ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። (ኤፌሶን 5፡22-23)። “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ” (አፌሶን 5፡25)። “እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና። ነገር ግን፣ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል” (ኤፌሶን 5፡8-29)። “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” (ኤፌሶን 5፡31)።

የሚያምኑ ባልና ሚስት የእግዚአብሔርን መርሕ ሲከተሉ፣ ውጤቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጋብቻ ይሆናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ጋብቻ የሚያመዛዝን ነው፣ ከክርስቶስ ጋር እንደ ወንድ ራስ እና ከሚስት ጋርም አብሮ። መጽሐፍ ቅዱሳዊው የጋብቻ ጽንሰ-ሐሳብ በሁለት ግለሰቦች መካከል የሚሆን አንድነት ነው፣ ያም ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያኑ አንድ መሆናቸውን የሚያሳይ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጋብቻ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries